
በ2011 በጀት ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች የ1 ሺህ 229 ሰዎች ህይወት አልፏል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንዳስታወቀው በ2011 በጀት ዓመት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ የ1 ሺህ 229 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤በ1 ሺህ 393 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስ በ19 ሰዎች ላይም የግድያ ሙከራ ተፈጽሞባቸዋል።
በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት በተጠቀሰው ዓመት በተፈጠሩ ግጭቶች ላይ በተሳተፉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡
በነዚሁ ግጭቶች ሳቢያም ከሁለት ቢሊየን በላይ ብር የሚገመት የዜጎች ንብረት የወደመ ሲሆን፤1 ነጥብ 2 ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸውና ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል።
በዚህ ግጭት የተሳተፉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቶ ከእነዚህ መካከል 645 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ሲሆን 667 ተጠርጣሪዎች እንዳልተያዙ ተገልጿል።
መረጃው የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ነው – ETHIO FM 107.8