የመስቀል አከባበር በዓል

በዛሬው የመስቀል ደመራ በአል አከባበር ላይ 55 የበዓሉ ታዳሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት እና ጉዳይ አስፈፃሚ መላከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ ለቢቢሲ ገለፁ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ሁለት ፓትሪያርክ ይኖራታል

መላከ ህይወት አባ ወልደየሱስ እንደገለፁት 33ቱ ምእመናን በቁጥጥር ስር የዋሉት ቤተክርስትያኗ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት እንዲቆም የሚያወግዝ ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለብሰው በመገኘታቸው ነበር።ምእመናኑ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆኑት ቲሸርቶች ‘የቤተክርስትያን ጉዳይ ያገባኛል’፣ የቤተክርስትያን መቃጠልና ጥቃት ይቁም’ የሚሉ ፅሁፎች ያለባቸው እንደነበሩ አባ ወልደየሱስ አስረድተዋል።

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሄዱ

አራቱ ደግሞ የሌላ ሰው ባጅ አድርገው በመገኘታቸው በቁጥጥር ሲውሉ ቀሪዎቹ 12 የሚሆኑት ደግሞ ስለት ይዘው ተገኝተዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስረዳሉ።

ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የጠራውን መግለጫ መንግሥት እንዲያስቆም ጠየቀ

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የተወሰዱት ካዛንችዝ ከሚገኘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደነበርና በኋላ እሳቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሃላፊዎች ከነጋገሩ በኋላ 37 በዋስ መለቀቃቸውን መላከሕይወት አባ ወልደየሱስ ተናግረዋል።