September 27, 2019

Source: https://fanabc.com/2019/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሩዋንዳ የመጀመሪዎቹን 66 የሊቢያ ስደተኞች ተቀበለች፡፡

ሩዋንዳ በሊቢያ የሚገኙ ስደተኞችን ለመቀበል ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት እና ከአፍሪካ ህብርት ጋር በደረሰችው ስምምነት መሰረት የመጀመሪያዎቹን 66 የሊቢያ ስደተኞች ትናት መቀበሏ ተነግሯል፡፡

በስምምነቱ መሰረት በሊቢያ ወደ አውሮፓ ለማቋረት ህይወታቸው በአስጊ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ ከ500 በላይ ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኛ መሆኗን ነው ዘገባው የሚያመላክተው፡፡

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት የሩዋንዳ ህዝብ ለስደተኞቹ ላደረገው ደማቅ አቀባበልም ያለውን አድናቆት በትዊተር ገጹ አስፍሯል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ሩዋንዳ ከገቡት 66 ስደተኞች ውስጥ የሁለት ወር ህፃን ጨምሮ ብቸኛ እናቶችን ያከተተ የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ይገኙበታል ነው የተባለው፡፡

ስደተኞቹ በፈቃደኝነት ከሊቢያ ወደ ሩዋንዳ የተዛወሩ ሲሆን÷ ከመዲናዋ ኪጋሊ 55 ኪሎሜ ትር  ርቀት በሚገኘው ጋሹራ የስደተኞች መሸጋገሪያ ጣቢያ ይቆያሉ ተብሏል፡፡

በሊቢያ የእርስ በእርስ ጦርነት ደህንነትቸው አደጋ ላይ ያለ እና በአስቸኳይ ወደ ሌሎች የስደተኛ ጣቢያዎች መዛወር ያለባቸው 4 ሺህ 500 ያህል ስደተኞች በሊቢያ እስርቤቶች ውስጥ መኖራቸውንም ዘገባው ያስረዳል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ