
የኖርዌይ ስደኞች ጉዳይ ፖሊስ (The National police Immigration Service) እንዳስታወቀው እኤአ በ2019 ብቻ 31 ኢትዮጵያውያን ኖርዌይን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርጓል።ከእነዚህ መካከል 12ቱ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ የተወሰዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ሊቀበላቸው ወደሚችል ሶስተኛ
የትኞቹ ሀገራት እንደተቀበሏቸው ግን ቢሮው ከመግለፅ ተቆጥበዋል።
እኤአ በ2019 ብቻ ከኖርዌይ እንዲወጡ ከተደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች መካከል 47 ኤርትራውያንም ይገኙበታል።
ከእነዚህ ኤርትራውያን መካከል ግን ወደ ሀገራቸው በቀጥታ የተወሰዱት ሁለት ብቻ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በኤርትራ የብሔራዊ አገልግሎት የተጀመረበትን 25ኛ ዓመት ክብረ በዓል በኖርዌይ ኤርትራ ኢምባሲ ሲከበር ተገኝተው ከማስታወቂያ ሚኒስትሩ፣ የማነ ገብረመስቀል፣ ጋር ኬክ የቆረሱ ስደተኛ ኤርትራውያን ላይ የኖርዌይ መንግሥት የጥገኝነት ጥያቄያቸውን አንደገና እየተመለከተው እንደሆነ ተነግሮ ነበር።
የኖርዌይ መንግሥት ከሀገሬ ይውጡልኝ ብሎ ካሰናበታቸው የተለያዩ ሀገራት ዜጎች መካከል 23 ታዳጊዎች ይገኙበታል ተብሏል።
ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉ እና ወደ ሶስተኛ ሀገር የተሸጋገሩ ዜጎች ጥገኝነት ጠይቀው የነበሩ፣ ወደ ኖርዌይ እንዳይገቡ የታገዱ እንዲሁም እንዲወጡ የተደረጉ ናቸው ሲል ቢሮው አስታውቋል።
BBC Amharic