2019-10-01

ኢሬቻ በዶ/አብይና በአቶ ለማ አንደበት!ዮሀንስ መኮንን*
Irreechi kenya irree keenyaa (ኢሬቻችን ክንዳችን ነው)
ኦቦ ለማ መገርሳ እና ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኢሬቻ በዓል አከባበርን አስመልክቶ በ OBN ላይ በአፋን ኦሮሞ የተናገሩትን ነገርና ያሳዩትን ወገንተኝነት ለማየት በአንጻሩም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባከበረችው የመስቀል በአል አከባበር ላይ ከታየው የፖሊስ “ሕግ አስከባሪነት” ለሁሉም እኩል መሥራቱን ማነጻጸሪያም ይሆነናል:: ወዲህም ከመንግሥት ግልጽ አቋም ተቃርነው ከመሥመር የወጣ ወገንተኝነት ለሚያሳዩ ባለስልጣናት መሞገቻ ሠነድም ነው::አቶ ለማ መገርሳ – ኢሬቻን የምናከብረው ስለተገደድን ሳይሆን ስለምንዋብበት ነው::– ሌሎችም እንዲወዱልን እንዲያደንቁልን ነው ይምንፈልገው::– ከዚህ ቀደም ኢሬቻ ላይ ሁላችንም ያፈርንበት እና ያዘንንበት ነገር ተከስቶ ነበር:: ያንን ችግር አንረሳውም::– ይሁን እንጂ ከችግራችን የምንማር እንጂ ከችግራችን ጋር አብረን የምንኖር መሆን የለብንም:: ከችግሩ ጋር ሲያለቅስ የሚኖር ችግረኛ ነው::– ከዚህ ቀደም ኢሬቻ ላይ ይገጥመን የነበረው ችግር ሊቀር ይገባዋል:: ይቅር::– ኢሬቻ ላይ በገጠመን ችግር እኛ ነን የተጎዳነው:: የሚሳቅበት እና የሚታፈርበት ባህል ሆኖ በሌሎች እንዲታይ ነው ያደረገን::– ኢሬቻ የመንግሥት በዓል አይደለም:: የዚህ ህዝብ በዓል ነው:: …መንግሥት ማገዝ ያለበትን ከመርዳት ያለፈ በዓሉ ላይ ድርሻ ወስዶ ወይንም ባለቤት ሆኖ ማጋፈር የለበትም::– መንግሥት የበዓሉ ባለቤት ከሆነ ባህሉን ማበላሸት ነው:: …ባህል ከምንም ጋር መቀላቀል የለበትም::– ታዲያ ኢሬቻን እንዴት አድርገን ነው የምናከብረው? ልክ ክስቲያኖች ጥምቀትን እንደሚያከብሩት, ልክ ሙስሊሞች ኢዳቸውን መስጊድ እና ስታዲየም ሄደው እንደሚያከብሩት ነው ህዝቡ በባለቤትነት ማክበር ያለበት::– የጥምቀት በዓሉ ባለቤት ቀሳውስቱ፣ የኢዱም ሺኪው ወይንም ኢማሙ ነው:: እንደዚሁ ሁሉ የኢሬቻ ባለቤትም መንግሥት ሳይሆን የመልካው ባለቤቶች ነው::– አባ ገዳ ስለሆነ የመንግሥት ባለስልጣን ስለሆነ ማንም ይህንን (የተለየ ነገር) ሊያደርግ አይችልም::– ቢሾፍቱ ላይም (ሆራ አርሰዴ) ሆነ በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚከናወነውን የኢሬቻ አከባበር ማከናወን ያለባቸው የቦታው ባለቤቶች ናቸው:: (መንግሥት አይደለም)– ይህ በዓል ባህል የሚንጸባረቅበት እንጂ ከዚያ ውጪ ምንም ዓይነት ነገር መታየት የለበትም::– በዓሉ ቢያምር እኔ ነኝ የማምርበት:: እያንዳንዳችን ነን የምንዋብበት:: ቢበላሽስ? እኔ ነኝ የምጠቁረው:: እያንዳንዳችን ነን የምንጠቁረው::– እውነት ተነጋግረን የምንደማመጥ: ቃል ተገባብተን የምንተጋገዝ ከሆነ ዘንድሮ “ኢሬቻችን ወኔያችን ነው” ኢሬቻችን ምልክታችን ነው:: ብለን አንድነታችንን እና ውበታችንን በሚያሳይ መልኩ ልናከብር ይገባናል::ዶ/ር ዐብይ አህመድ– በባህል እና በታሪክ መድረክ ባህልና ታሪክን ማሳየት ልማት ቦታ ልማትን ማሳየት የሃሳብ ክርክር በሚደረግበት ቦታ ደግሞ በሃሳብ መሙዋገት (ይገባል)– የኢሬቻ ምንጭ ሠላም ነው:: አንድነት ነው:: ፈጣሪን ማመስገን ነው::– የበዓሉ በሠላም መጠናቀቅ ሌሎች ከዚህ ባህል ለመማር ለመካፈል እንዲመጡ ያደርጋቸዋል::– ከሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከሀገር ውጪ ያሉ ሰዎችም በርካቶች በአንድ ጊዜ ተሰብስበው የማያከብሩትን ይህን መሰል በዓል ማየት ይፈልጋሉ::– ባህላችንን ታሪካችንን ማንነታችንን ኦሮሞነታችንን ለዓለም እንድናሳይ በሠላም ጀምረን በሠላም እንዲፈጸም መደማመጥ አለብን::– ወጣትነት ማወክ (መረበሽ) ብቻ ሳይሆን ልማትም ጭምር ስለሆነ በዘዴ እና በጥንቃቄ ልንጠቀምበት ይገባል::https://www.youtube.com/watch?v=zXu1tbFMiDY&feature=shareFiled in:Amharic