በዚህች ሀገር ከ1966.. ጀምሮ በተለይም ከ1983.. ወዲህ የወንበዴ ቡድን አገዛዝ እንጅ መንግሥት ኖሮ አያውቅም!!!

በቀደም ዕለት ቤተክርስቲያን የደመራ በዓልን ስታከብር ከንዋዬ ቅድሳቷ አንዱ የሆነውን ያውም የመጀመሪያውን ንዋየ ቅዱሷን የቃልኪዳን ምልክቷን እንዳትይዝ ተደረገ፣ እየተነጠቀም ተወሰደ፣ ይሄንን የቃልኪዳኑን ምልክት የያዙ አገልጋዮችና ምእመናንም እንዲታሰሩ ተደረገ፡፡

ይሄው የቤተክርስቲያንን መብትና ጥቅም በዚህና ከዚህም በከፋ መልኩ እየገፈፈ፣ እየነጠቀ፣ እየጣሰ ያለው አገዛዝ በሌላ በኩል ደግሞ ከሰሞኑ እንቅስቃሴው እንደምትመለከቱት ይሄው የሚሠራውን የማያውቀውና ሥርዓት አልበኛው የወንበዴ አገዛዝ የገዛ ሕጉን ተላልፎ አያገባው ገብቶ ኢሬቻ የተባለን የባዕድ አምልኮ በዓል ለማክበር ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ሕገወጥ ትብብር በማድረግ ሽርጉድ እያለ ይገኛል!!!

ለዚህ የቃልቻ በዓሉ አከባበር ድምቀት በሚልም የዚሁ ባዕድ አምልኮ መለያ ምልክት ወይም አርማ የሆነውን ጥቁር ቀይ ነጭ ቀለም ያለውን ጨርቅ በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎች እየሰቀለ ይገኛል!!!

ለምሳሌም ዛሬ ፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት የቃልቻ ምልክት ወይም አርማ የሆነውን ይሄንን ጨርቅ ክርስቲያን በሆኑትና ይሄንን የቃልቻ ምልክት ይይዙት ወይም ይሰቀልባቸው ዘንድ ክርስቲያንነታቸው ፈጽሞ የማይፈቅድላቸውን የዐፄ ምኒልክን ሐውልት ይሄንን የቃልቻ ቀለማት የያዘ ጨርቅ ሰቅለውበታል፡፡

ዐፄ ምኒልክ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ እንደመሆናቸው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ይሄንን ዐፄ ምኒልክ በክርስቲያንነታቸው እንዳይይዙት እንዳይጠቀሙበት የሚከለከሉትን በዚህም ምክንያት የሚጠየፉትን ወይም የማይፈልጉትን የቃልቻ ወይም የባዕድ አምልኮ ጨርቅ ከሐውልቱ የማስነሣት ግዴታ አለባት!!!

ይሄ የአገዛዙ ተግባር ሌላ ምንም ሳይሆን በቀጥታ የሰብአዊ መብት ጥሰትና እምነትን በኃይል የመጫን ሕገወጥና አንባገነናዊ ጥቃት እንዲሁም ነውረኛ ትንኮሳ ነው!!! በመሆኑም ተግባሩ ዐፄ ምኒልክን አዋረድን፣ አረከስን፣ አቆሸሽን!” ተብሎ ታስቦ የተደረገ ሕገወጥና አንባገነናዊ እንዲሁም አጸያፊ ተግባር ነው!!!

ትናንትና በየክፍለ ከተማው የተደረጉ ስብሰባዎችን ከብዙኃን መገናኛዎች እንደተከታተላቹህት ኦነጋውያኑ የዐቢይ አሥተዳደር ወይም የወያኔ/ኢሕአዴግ አመራሮች ጭራሽ ከእነሱ ውጭ ያለውንና የዋቄፈታ ወይም የዋቄፈና ባዕድ አምልኮ ተከታይ ያልሆነው የአዲስ አበባ ሕዝብ ይሄንን ኢሬቻ የተባለውን የቃልቻ ወይም የባዕድ አምልኮ እምነት በዓል አከባበርን ከራሳቸው ከአጋንንት አምላኪዎቹ ጋር አብሮ እንዲያከብር አስገዳጅ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል!!!

ይህ የቃልቻ በዓል ግን እንኳን ከኦሮሞ ውጭ ያለውን ክርስቲያን ሕዝብ ይቅርና ክርስቲያን ኦሮሞዎችን እንኳ ፈጽሞ አይመለከትም!!! ይሄንን የባዕድ አምልኮ በየዓመቱ እየተገኘ አብሮ እያከበረና ከባዕድ አምልኮ ዋቄፈታ አምላኪዎቹ አንዱንም እንኳ አስተምሮ እንዲጠመቅና ይሄንን ባዕድ አምልኮ እንዲተው ያደረገው ሰው ሳይኖር ቃልቻ አምላኪዎችን አስተምሬ ለመመለስ ነው የተገኘሁት!” የሚል ሰው ቢኖር እራሱን እንጅ አምላክን ሊያታልል አለመቻሉን ጠንቅቆ ይወቅ፡፡ በአገዛዙም በኩል በሕዝብ ላይ ጫና በመፍጠር የዋቄፈታ የቃልቻ እምነት በዓል የሆነውን ኢሬቻን እንዲያከብር ማስገደድ እምነትን በኃይል የመጫን ሕገወጥና አንባገነናዊ ተግባር ነው!!! የማንም ይሁን የማን፣ በዋቄፈታም ይሁን በሌላ ባሕላዊ እምነት!” በማለት ስሙን አሳምራቹህ በምትጠሩት ባዕድ አምልኮ እግዚአብሔር አይመለክም!!! ይሰማል??? እደግመዋለሁ የማንም ይሁን የማን፣ በዋቄፈታም ይሁን በሌላ ባሕላዊ እምነት!” በማለት ስሙን አሳምራቹህ በምትጠሩት በማንኛውም ባዕድ አምልኮ እግዚአብሔር አይመለክም!!! ሕይዎትም፣ መንገድም፣ እውነትም፣ ሃይማኖትም አንድና አንድ ብቻ ነው!!! ኤር. 616, ማቴ. 713, ኤፌ. 45, ይሁ 13

እናንተ በሐይቅም ይሁን በዛፍ በፈለጋቹህት ማምለክ ትችላላቹ ለነፍሳቹህ ካላሰባቹህ መብታቹህ ነው፡፡ ይሄንን ከንቱ እምነታቹህን ግን በሌላው ላይ በኃይል መጫን አትችሉም!!! መብት የላቹህም!!!

የሰይጣንን ድፍረትና ጥበብ ተመልከቱ!!! የአገዛዙን ጡንቻ ተጠቅሞ ለእሱ ሊያሰግደን፣ እሱን ሊያስመልከንና ሊያረክሰን፣ እምነታችንን የሚጻረር ተግባር አስፈጽሞን ከአምላክ ጋር ሊያጣላን ጥበብ የታከለበት ጥረት እያደረገ ነው ያለው!!! ልብ ያለው ልብ ይበል! ጆሮ ያለው ይስማ!!!

እጅግ የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ በቀደም የደመራ ዕለት ቤተክርስቲያን በአደባባይ ንዋየ ቅዱሷ የሆነው ትእምርተ ኪዳኗ (የቃልኪዳን ምልክቷ) ከአገልጋዮችና ከምእመናን እጅ እየተነጠቀ እንደ ቆሻሻ የትም ሲጣል፣ በዋዜማውም የፌዴራል ፖሊስ በበዓሉ ላይ የቃልኪዳን ምልክቱን መያዝ የሚከለክል ሕገወጥ መግለጫ ሲያወጣ፣ ቤተክርስቲያን የአምልኮ ሥርዓቷን ያለ ማንም ጣልቃገብነት አስተምህሮዋ በሚያዛት መልኩ በነጻነት የመፈጸም የመከወን መብቷን ተነፍጋ እንዲህ ዓይነት የመብት ጥሰትና ጥቃት ሲፈጸምባት፣ ከዚህም ባለፈ በቃልኪዳን ምልክቷ ላይ የአገዛዙ መለያ የሆነው ባዕድ ምልክት ተለጥፎበት የዚህ ፀረ ቤተክርስቲያን አገዛዝ አገልጋዮች የሆኑ ሐሰተኛ ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪ ተብየዎች እንዲይዙት ተደርጎ በመንፈሳዊ በዓል ላይ ወይም በቤተክርስቲያኗ በዓል ላይ እንዲያዝ ሲደረግ ቤተክርስቲያኗን እመራለሁ!” የሚለው ሲኖዶስ ተብየው የምንደኛ ጳጳሳት ጥርቅም የቤተክርስቲያንን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ አንዳችም ያሰማው ተቃውሞና ቤተክርስቲያን ተደፍራለችና ይቅርታ ትጠየቅ፣ የእርምት እርምጃ ይወሰድ!” የሚል ጥያቄ አለማቅረቡና በዝምታ ማለፉ ነው!!!

ታዲያ በዚህ ሁኔታ ቤተክርስቲያን ወይም መንጋው ጠባቂ እረኛ አለው ትላላቹህ??? ይሄንን ማድረግ ያልቻለ ሲኖዶስ ተብየ ሌላ ምን ሊከውን፣ ቤተክርስቲያንንስ ከምንስ ሊያድን ይችላል???

እንዲያው ነገሩን አልኩ እንጅ ሲኖዶስ ተብየው እኮ ለ28 ዓመታት ሙሉ የቤተክርስቲያንን አከርካሪ ሰበርኩ!” ብሎ የሚፎክረውን ይሄንን ፀረ ቤተክርስቲያን አገዛዝ በትጋት ሲያገለግልና ቤተክርስቲያንን እጅና እግሯን ኮድኩዶ ይዞ ሲያስመታት፣ ሲያስቀጠቅጣት፣ ሲያሰይፋት፣ ሲያዘርፋት፣ ሲያሰብራት…. የኖረ የዚህ ፀረ ቤተክርስቲያን አገዛዝ አገልጋይ እኮነው!!! ታዲያ ከዚህ እግዚአብሔርን ሳይሆን አገዛዙን አምላኪና አገልጋይ ከሆነ የምንደኛ ጳጳሳት ጥርቅም ምን ይጠበቃል ታዲያ???

እጅግ ያሳዝናል!!! በደመራ በዓሉ ላይ እንዲያ አደረጉ ዛሬ ደግሞ እንደምታዩት የቃልቻ ጨርቃቸውን በክርስቲያኑ ንጉሥ ሐውልት ላይ ሰቅለዋል፡፡ ነገ ደግሞ አትጠራጠሩ ይሄንን የቃልቻ ጨርቃቸውን ቤተክርስቲያን ላይ እንሰቅላለን ይላሉ፡፡ ደግሞም ያደርጉታል! ማን ሊከላከል??? ሲኖዶስ ተብየው የምንደኛ ጳጳሳት ጥርቅም ነው ወይስ ይሄ ፈሪው ምእመን???

አንች ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ይሁንሽ ብቻ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው