2019-10-02

ጥቅምት 2 መስቀል አደባባይ እንገናኝ፤ ስለ አፓርታይዳዊው አገዛዝም ድምጻችንን እናሰማ!!!ባልደራሱየአዲስ አበባ ህዝብ ጥቅምት 2 ቀን ጧት 3ሰዓት ላይ መስቀል አደባባይ በመገኘት አዲስ አበባን ወደ ኦሮሚያ ለመጠቅለል በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እየተተገበረ ያለውን ህገወጥ ስራ ተቃውሞ ድምጹን እንዲያሰማ ተጠርቷል።  * በአዲስ አበባ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን እና አረንጓዴ ስፍራዎችን ለቄሮዎች ህገ ወጥ ካርታ በማደል ማከፋፈል እንዲቆም፣ * ህዝብ ለዓመታት ገንዘብ የቆጠበባቸውን የጋራ መኖሪያዎች በልዩ ጥቅም ስም ለአንድ ጎሳ ያለእጣ ጠቅልሎ መስጠትን ለማስቆም፣ * በህገ ወጥ መንገድ ከባለቤቶቹ እውቅና ውጭ የቤተሰብ ፎርም ላይ ሰዎችን እየሞሉ መታወቂያ ማደል እንዲቆም ፣ * በየ መንግስታዊ ተቋማቱ እየተተገበረ ያለውን የዘር መድሎ የሚታይበትን አሰራር ለማጋለጥ፣ * በይፋ ከዜግነት መስመር ተገፍቶ አፓርታይዳዊ መስመር ውስጥ እንዲገባ በተፈረደበት የአዲስ አበባ ህዝብ እና ስለአዲስ አበባ እጣ-ፈንታ ድምጻችንን እናሰማ። Filed in:Amharic