የአዲስ አበባ ሕዝብ ሆይ! አንተ የህልውና ጉዳይ ሆኖብህ ጥሩ አልበላም፣ ጥሩ አልጠጣም!” ብለህ ጥሬ ቆርጥመህ፣ ጥሩ አልለብስም፣ ጥሩ አልጫማም፣ አላጌጥም ይቅርብኝ!” ብለህ ለዓመታት በቆጠብከው ገንዘብህ ከተገነቡ 20/80 የጋራ መኖርያ ቤቶች (ኮንደሚኒየሞች) ውስጥ 22,915 ቤቶችን ነገ በአዲስ አበባ ዳርቻ ለልማት በሚል ተነሥተዋል!” ለተባሉ አርሶ አደር አባወራዎችና 18 ዓመት ለሞላቸው ልጆቻቸው ለመስጠት ዝግጅቶች ተጠናቋል!!!

እጅግ በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ እነኝህ ተረካቢዎች ለሚሰጣቸው የጋራ መኖርያ ቤት ምንም ዓይነት ክፍያ የማይከፍሉ መሆናቸው ነው!!! ከፍተኛ ሕገወጥነትና ኢፍትሐዊነት የሰፈነበት ዝርፊያና ውንብድና ሊፈጸምብህ ነው ተነሥ!!!

እንደሚታወቀው ከዚህ ቀደም አርሶ አደር ለነበሩት ተነሺዎች ከቦታቸው በተነሡበት ወቅት እስከ 800 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ ካሳ ተሰጥቷቸዋል!!!

ይሄም ብቻ ሳይሆን ምትክ ቦታም ለአባወራ 500 ካሬ ሜትር ለልጆቻቸው ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 250 ካሬ ሜትር ተሰጥቷቸዋል!!!

ከእነዚህ ተነሽ አርሶ አደሮች ውስጥ አሁን ላይ በጥሩ ኑሮ ደረጃ ላይ ያሉት አሁንም ያለ ምንም ክፍያ የጋራ መኖርያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል!!!

ካሳውና ምትክ ቦታው ተሰጥቷቸው እያለ አሁን ላይ በጥሩ የኑሮ ደረጃ የሌሉትም ቢሆኑ በራሳቸው ችግር ላባከኑት ገንዘብና ለተጎዳው ኑሯቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕዳ ከፋይ የሚሆነው እኮ በምን ሒሳብ ነው???

አሠራሩ ዓይን ያወጣ ጠባብ ዘረኝነትና ተረኝነት የተጠናወተው ሕገወጥና ኢፍትሐዊ የአድልኦ አሠራር መሆኑን የሚያጋልጠው፦

* በተመሳሳይ ምክንያት ወይም ለልማት በሚል ከመሀል ከተማ ኑሯቸውን ከመሠረቱበት፣ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠሩ ሕይዎታቸውን ይገፉበት ከነበሩበት የሥራ ቦታቸውና የመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው የማትረባና ፍጹም ፍትሐዊነት የጎደለው ካሳ ተወርውሮላቸው ከከተማው ዳር ተጥለው ኑሯቸውን የመሠረቱበት ሥራቸው የተበላሸባቸውንና በዚህም ምክንያት ኑሯቸው የተመሰቃቀለባቸውን የአዲስ አበባ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች በዚህ የካሳ ማስተካከያ እርምጃ ያልተካተቱ መሆናቸው!!!

* አሁንም ከዚህ ቀደም ከመሀል አዲስ አበባ ለልማት ተብለው የተነሡ ነዋሪዎች ኮንደሚኒየም ሲሰጣቸው ክፍያ ተጠይቀው እየከፈሉ ያሉ መሆናቸው!!!

* በተመሳሳይ ጊዜ ካራ ቆሬ 73 አርሶ አደር ያልሆኑ አባወራዎች ሕገ ወጥ ናችሁ!” በሚል ያለ ምንም ካሳ ቤታቸው ፈርሶ እስካሁን ችግር ውስጥ ያሉትንና በተመሳሳይ እርምጃ ከሌሎች ስፍራዎችም ተነሥተው ችግር ላይ እንዲወድቁ የተደረጉ ዜጎችን አለማካተቱ ነው!!!

ወገን ሆይ! በዚህ የከተማው አሥተዳደር ሕገወጥና ኢፍትሐዊ ውሳኔ የብአዴን ሙሉ ድጋፍና ተባባሪነት እንዳለበት ልብ በሉ!!!

የአዲስ አበባ ሕዝብ ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይሄ ኢፍትሐዊ፣ ሕገወጥ፣ ውንብድና የተሞላ ዘረኝነትና ጠባብ የተረኝነት አድልዎአዊ አሠራር የሚያሳየው ጥሬ ሐቅ ቢኖር ልናየው የማንችለው ነገር ሆኖ ነው እንጅ አገዛዙ በዚህ ኢፍትሐዊና ሕገወጥ አስተሳሰቡና አሠራሩ የኢትዮጵያን ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ እየዘረፈና እያራቆተ ወገኔ ክልሌ!” የሚለውን እየጠቀመ ያለ መሆኑን ነው!!!

በመሆኑም በአገዛዙ ባዶ የመደለያ፣ የማታለያ፣ የማዘናጊያ ወሬዎች እየተደለልን፣ እየተታለልን፣ እየተዘናጋን ጊዜ መስጠታችንና ከልክ በላይ መታገሳችን የራሳችንንና የሀገራችንን ጥቅም፣ ህልውናና መብት በምናየው ደረጃ ከፍተኛ አደጋ ላይ እንዲወድቅ እንዳደረግነው እያየህ ነውና ነገሮች ሊቀለበሱ ከማይችሉበት ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት ፈጥነህ ተነሥ!!! ተነሥ!!! ተነሥ!!!

አሁንም ደግሜ ደጋግሜ እላለሁ ጊዜው ካለፈበትና እጅግ ከዘገየ የማይጠቅም ጸጸት ላይ ከመውደቃችን በፊት ተነሥ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው