አቶ ዐቢይ አሕመድ ከታሰበው በግማሽ እንኳ ያልተጠናቀቀውን የቤተመንግሥት ፓርክን በማስመረቅ አሳቦ ግብዣ እያደረገ ያለው ይህችን ሀገር በማመሰቃቀልና አሁን ላለችበት ቀውስ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የምዕራቡ ዓለም ነገ ይፋ በሚደረገው የሰላም ኖቬል ሽልማት አቶ ዐቢይ አሕመድን አሸናፊ እንዳደረጉት ስለነገሩት ግብዣው ለዚህ ሽልማት የደስደሱን እንደሆነ ጠርጥሬያለሁ!!!

ምናልባት አንዳንዶቻቹህ ዐቢይ ምንም እንኳን አቶ ኢሳይያስ ሊገኝለት ባይችልም በዚህ ግብዣ ላይ የምሥራቅ አፍሪካ መሪዎች ተገኝተው ምስክርነት እንዲሰጡ ያደረገው የኖቬል ድርጅቱ አሸናፊ እንዲያደርገው የራሱን ቅስቀሳ እያደረገ ሊመስላቹህ ይችል ይሆናል፡፡

ይሁንና ግን ድርጅቱ ነገ በሰዓቱ ይፋ የሚያደርገውን ውጤት ማንም አያውቅም ማለት ይፋ እስከሚደረግበት ሰዓት ድረስ አሸናፊው አልተመረጠም ማለት ሳይሆን ምሥጢራዊ ነው ማለት ነው እንጅ የቦርዱ አባላት አሸናፊውን መርጠው የሚወስኑት አስቀድመው ነው!!! በመሆኑም ይህ የመሪዎቹ ምስክርነት የሚያመጣው ለውጥ የለም!!!

እውነት እንደጠረጠርኩት የኖቬል ሽልማት ድርጅት ይሄንን አድርጎት ከሆነ ይሄ ውሳኔው ድርጅቱ በታሪኩ ከሠራቸው ስሕተቶች እጅግ የከፋው ይሆናል!!!

በምንም መመዘኛ ቢታይ መጨረሻው ያልታወቀውና የስምምነት መቋጫ ያልተደረገለት፣ ከዚህም የተነሣ በማንኛውም ሰዓት ወደነበረበትና ከዚያም ወደከፋ ግጭት ሊመለስ የሚችለው የአገዛዙና የሸአቢያ ጊዜያዊ የሆነ ወቅታዊ የተረጋጋ ሁኔታ እና አገዛዙ በክረምቱ ወቅት ተከልኩት ያለው የውሸት አራት ቢሊዮን ችግኝ በርካታ ጥብቅና ጠንካራ መመዘኛና መስፈርት ባለው የኖቬል ሽልማት ድርጅት አሳማኝና ተቀባይነት ያለው ክንውን ሆኖ ተገኝቶ ፈጽሞ ለኖቬል ሽልማት እንደማያበቃው እርግጠኛ ሆኘ ልነግራቹህ እችላለሁ!!!

ይህ አገዛዙ በክረምቱ ተከልኩት የሚለው አራት ቢልዮን ችግኝ ሐሰት መሆኑን የምታረጋግጡበት አንድ ቀላል የማረጋገጫ ዘዴ ልንገራቹህ፡፡ አንዷን ችግኝ የሚያስፈልጋትን ሁሉ አድርጎ አፍልቶ ለመተከል ብቁ አድርጎ ለማቅረብ በትንሹ ዐሥር ብር ትጠይቃለች፡፡ አገዛዙ በክረምቱ ወቅት አራት ቢሊዮን ችግኝ እንደሚተክል ይፋ ያደረገው በክረምቱ መቃረቢያ ነው፡፡ ጥያቄው አገዛዙ ባለፈው በ2010.. ላይ ለ2011.. ክረምት ላይ ለሚተከል አራት ቢሊዮን የችግኝ ተከላ የዘመቻ ሥራ አርባ ቢሊዮን ብር ባጀት ይዞ ነበረ ወይ???” የሚለው ነው፡፡

መልሱ የባለፈውን ዓመት ማለትም 2010.. ባጀት መመልከትና ማረጋገጥ ትችላላቹህ እንኳን ይሄንን የሚያህል ግዙፍ ባጀት ይቅርና ይሄንን ያህል ተብሎ የተጠቀሰ አነስተኛ ባጀት እንኳ ለችግኝ ምርትና ተከላ ተብሎ የተያዘ ባጀት አልነበረም፡፡

የግብርና ወይም የደንና ዱር አራዊት ሚንስቴር ከሚመደብለት ባጀት በየዓመቱ ችግኝ በሚያመርትበት አነስተኛ ቁጥር ለሚያመርትበት የተለመደውን አነስተኛ ባጀት መድቦ ካልሆነ በስተቀር፡፡ በመሆኑም 2010.. ላይ አገዛዙ ከወጭዎቹ ሁሉ የሚበልጥ ትልቅ ወጪ የሆነ ይሄንን ያህል ግዙፍ ወጭ ለሚጠይቅ ለአራት ቢሊዮን ችግኝ ተከላ!” ብሎ የያዘው ባጀት ስላልነበረ አራት ቢሊየን ችግኝ የተባለው ወሬ ነጭ ውሸት ነው!!!

የኖቬል ሽልማት ድርጅት ከላይ የጠቀስኩላቹህን ዓይነት የማጣሪያ ስልት ተጠቅሞ የእራሱን ማጣራት ሳያደርግ እንደ እኛ የተነገረውን ዝም ብሎ አምኖ የሚቀበል ድርጅት ነው ብየ ስለማላምንና አሠራሩም ይሄንን የሚያሳይ ባለመሆኑ በዚህ የውሸት ችግኝ ተከላም ዐቢይን ተሸላሚ ያደርጋል የሚል እምነት የለኝም!!!

እውነታው ይሄ በሆነበት ሁኔታ የሽልማት ድርጅቱ አቶ ዐቢይን አሸናፊ ካደረገው ውሳኔው ፖለቲካዊ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ትችላላቹህ!!!

ይሄም ማለት ወያኔ/ኢሕአዴግ በራሳቸው በምዕራባውያኑ ተቀባይነት የሌለው የጠላትነት ምክንያት ለሥልጣን ላበቁት አሻንጉሊታቸው ሆኖ የታዘዘውን ሁሉ በመፈጸም በዚህች ታላቅ ሀገር እና በሕዝቧ ላይ ላደረሰው ወደር የለሽ ጭካኔ የተሞላ ሁለንተናዊ ጥፋትና ውድመት የተሰጠ ሽልማት ነው ማለት ነው!!!

ሁሉንም ነገ የምናውቀው ይሆናል!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው