October 13, 2019

ከአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት ዛሬ የወጣው መግለጫ::
ፖሊስ የጥቅምት ሁለቱን ሰልፍ ስለመከልከሉ …….
የአዲስ አበባ ምክር ቤት ጥቅምት 2 2012 ዓ.ም የጠራውን ሰልፍ የአዲስ አበባ መስተዳድር በህጉ መሠረት በዝምታ ፍቃድ ከሰጠ ቦኃላ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥቅምት 1 2012 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ክልከላ አድርጎበታል።
ይህን አስመልክቶ ምክር ቤቱ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፣ ምክር ቤቱ ቀደም ብሎ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፣ለሀገሪቱ ሰላምና ለህዝቧ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሰልፉን ሰርዟል።
የመንግስት ህገ ወጥ ክልከላ የዴሞክራሲ እና ፍትህ ቅልበሳውን አረጋግጧል። ስለዚህም፣ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደገለፀው፣ ሰላማዊ ትግሉን በሂደት ወደ ቀጣይ ምእራፍ ለማሸጋገር እንደሚገደድ በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል።
የአዲስ አበባ ባላደራ ምክርቤት የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማሳካት ሲንቀሳቀሱ የታሰሩ በርካታ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።
በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ፣ እንዲሁም፣ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ቀን ከሌሊት ያደረጋችሁት ልፋት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ መምጣት የምትከፍሉት ዋጋ ቢሆንም፣ ባለ አደራ ምክር ቤቱ የላቀ ምስጋናውን እና አክብሮቱን ይገልፃል።
ፈጣሪ ህዝቧንና ኢትዮጵያን ይባርክ
የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት
አዲስ አበባ