በአንድ አመት የአቢይ መንግስት እድሜ የሚከተሉት ግፎች እና በደሎች ተከናዉነዋል::

1-ሶስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ተፈናቅሎ
2-45 ቤተክርስቲያናት ተቃጥለዉ
3-በብዙ አስር ሽህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በጅማ: አርሲ: ሀረር: አጣዬ: ከሚሴ : በቡራዩ በገጀራ አንገታቸዉን እንደ ሳር ተጨፍጭፈዉ
4-ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ እንዲሁም በኦሮሚያ ከተሞች ኢትዮጵያዉያን ቤት አልባ እንዲሆኑ ተደርጎ እና በሜዳ ላይ ወጥቶ ተጥሎ
5- የአማራ ሰዉ ፖለቲከኛዉ: ጋዜጠኛዉ: ሰብአዊ መብት ትሟጋቹ እና የጦር መሪዉ እየተመረጠ በጅምላ ሲጨፈጨፍ እና ሲታረድ እዬታዬ
6-የአብን እና የባልደራስ መሪዎች እና አመራሮች እንዲሁም የአስራት ጋዜጠኞች በጅምላ ታስረዉ እየተሰቃዩ
7- መንገዶች በደብረብርሃን እና በፍቼ አቅጣጫ ተዘግተዉ ኢትዮጵያዉያንን እየተጉላሉ እና በሀገራቸዉ የመቀሳቀስ መብታቸዉ ተገፎ

8-ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ኦሮሚያ በሚባል ወያኔ ሰራሽ ክልል ላይ እንዳይንቀሳቀሱ ታግተዉ

9-የተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ልታደርግ ያሰበችዉ ሰላማዊ ሰልፍ ተከልክሎ:

10-የባልደራስ ሰልፍ በተደጋጋሚ ታፍኖ

11- እዉነተኛ ዲሞክራሲ የተናገሩ ሶስት ሽህ የአዲስ አበባ ወጣቶች
አላግባብ ታስረዉ እና ተጉላልተዉ አንዳንዶቹም እስካሁን ሳይፈቱ

12- ኦዴፓዉያን/ኦነጋዉያን ከአስር በላይ ባንክ ዘርፈዉ ከሚሊዮን በላይ ሰራዊት እንዲያሰለጥኑ ሁኔታዎችን ያመቻቸዉ የአቢይ መንግስት ነዉ::ሆኖም አሳምነዉ አምስት ሽህ ሚሊሻ አሰለጠነ ብሎ በመፈንቅለ መንግስት በማሳበብ በአደባባይ አሳምነዉን እና ዶ/ር አምባቸዉን የገደላቸዉ የአቢይ መንግስት መሆኑ እየታወቀ

13. የአማራን ህዝብ በአባቶቹ ጥንታዊ ምድር ኢትዮጵያ ላይ እንደ መጤ ህዝብ ለመሳደብ አፋቸዉን ሲከፍቱበት ብቻ ሳይሆን ለዘር ፍጅት ሁኔታዎችን ሲያመቻቹ

14. የኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን/የጀዋራዉያን ሰራዊት አሁንም በብዙ አካባቢዎች /በአጣዬ; ሰሜን ሸዋ: ወሎ: እንዲሁም ኦሮሚያ: ሶማሌ: ቤኒሻንጉል/ ግልጽ ወረራ በማድረግ ህዝብን እያተራመሰ እና የሌሎችን ኢትዮጵያዊ ነገዶችን እያፈናቀለ እየገደለ

15- የኢትዮጵያ ህዝብ ዘሩ እየተመረጠ በኑሮ ዉድነት እንዲጠበስ እየተደረገ ባለበት ሁኔታ: ብስራ አጥነት እንዲቆራመት እየሆነበት ባለበት ሁኔታ:: በረሃብ አለንጋ እየተጠበሰ ባሌት ሁኔታ

16- ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያዉያን በአባቶቻቸዉ ሀገር ላይ እኒሸማቀቁ ሀገር እንደሌላቸዉ ዜጋ እንዲሆኑ እየተደረገ ባለበት ሁኔታ

ይሄን ሁሉ ግፍ ባላየሁም የሚያልፉ ብዙ እሥስቶች ዞረዉ ደግሞ ስለ ዲሞክራሲ እና ፍይህ ሲሰብኩ ያስገርማሉ::

ይሄ ሁሉ ግፍ ግን ዋና ዋናዉ እንጅ ሁሉም አይደለም::በየቢሮዉ የሚከናወነዉን የዘረኝነት ምደባ: ሰዎች ማባረር እና ማፈናቀል አልተካተተም::በብሄራቸዉ የተነሳ በርካታ ቢዝነሶች ተዘግተዋል:: በርካታ ንጹሃን ሰዎች የደረሱበት አይታወቅም::የዚህ ሁሉ የግፍ አለቃ ደግሞ አቢይ እራሱ ነዉ::አለ አቢይ እዉቅና አንዳች መንገድ ላይ አንዲት ድንጋይ አትደረደርም::አንድ ሰራተኛ እንኳን አይባረርም::

ይሄ ሁሉ እየተከናወነ እስኪ እስካሁን ስንት እሥስት ፖለቲከኞች:ታዋቂ ሰዎች ምሁራን እና ተራ ሰዎች አስተዋላችሁ ?የአገም ጠቀም ፍትህ ናፍቆት: የሰላም ሰባኪ በመሆን: የዲሞክራሲ አቀንቃኝ በመሆን የእስሥትነት ስራቸዉን የሚያከናዉኑ ስንት ሰዎችን ታዘባችሁ? ባንድ እጃቸዉ ለአቢይ ያጨበጭባሉ: በሌላ እጃቸዉ እኩልነት ዲሞክራሲ እያሉ ያጨበጭባሉ::ይሄ ታላቅ እሥስትነት ነዉ::

ከታዋቂ እስከ ተራ ዜጎች ብዙ አይነት የእሥስት ባህሪ የሚከዉኑ ሰዎች በዬቀኑ እያስተዋልን ነዉ::አንዳንዱም የሀይማኖት መምህር ነኝ : ዳቆን ነኝ እያለ በሁለት ወጭት የሚበላ: ሌላዉም ፓስተር ነኝ እያለ በሁለት ማንኪያ የሚጎርስ: አንዳንዱም ተቃዋሚ ፓርቲ ነኝ እያለ በሁለት ማማ ላይ ለመዉጣት የሚወናከር ብዙ ነዉ::

በአንድ እጃቸዉ ወንጀልን እና ወንጀለኛን እየደገፉ በሌላ እጃቸዉ ደግሞ ተቃዋሚ እና የፍትህ ሀይል ለመምሰል ተቃዉሞ መሰል ነገር የሚያሰሙም እሥስቶችም ሞልተዋል::

ወንጀለኛ ፓርቲዎችን: ወንጀል እና ግፍን የሚደግፉ ብዙዎች አንድም በጥቅም አንድም በጎሳ ሀረግ በመሳሳብ አንድም በሀይማኖት ቀጭን ክር በመተሳሰር መሆኑ ነዉ::

መጽፋ ግን የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሄርን ለእግዚአብሄር ስጥ ነዉ ያለዉ::ፍትህ እና እዉነት የእግዚአብሄር ገንዘቡ ናቸዉ::ወንጀል: ወገንተኝነት እና ጭፍን የወንጀለኞች ተባባሪ መሆን ደግሞ የቄሳር ዋጋ ናቸዉ::እናተ የእስስት ባህሪያትን እየተወናችሁ ያላችሁ ሆይ ህዝብ የማያስተዉል እየመሰላችሁ በአንድ እጃችሁ ለወንጀለኛ ታጨበጭባላችሁ::

ዞር ብላችሁ ደግሞ የዲሞክራሲ እና የእኩልነት ጠበቃ ለመሆን የማስመሰያ ቃል አደባባይ ላይ ትናገራላችሁ::ይሄን የምታደርጉትም ህዝቡን ለማደንዘዝ የተሰጣችሁን ተልዕኮ ለመወጣት ነዉ:: ችግሩ ግን ይሄ ስራችሁ ሀገርንም እናንተ እራሳችሁንም መራራ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ ነዉ::

የእሥስት ፖለቲካ ሀገር ያፈርሳል እንጅ ዲሞክራሲም አይገነባ ሀገርም አያንጽ::