October 13, 2019

ክቡር ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ “ለራሴ ደንነት ነው! በሚል በአይነቱም በይዘቱም ልዩ የሆነ የጥበቃ ኃይል አቋቋሙ፡፡ ስሙም የሪፑብሊካኑ ጋርድ ይባላል፡፡ ይህን ተከትሎ አንዱ የእንግሊዘኛ ሚዲያ እንዲህ ጽፎታል፡፡<<Dr. Abiy Ahmed created a “Republican Guard” to protect himself and his family.>> ብሎ ጽፏል፡፡

ይህ የሪፑቡሊካኑ ኃይል እንደ አብሪ ጥይት የሚፈጥን፣ እንደ ጅራታሙ ኮከብ የሚዘገዘግ ተወርዋሪ የጦር ኃይል ሲሆን፤ በከፍተኛ ወጪ አሰልጥነው በጥቅም ላይ ሲያውሉ አይ! ግድ የለም ይሁን ከእርሳቸው ህይወት የሚበልጥብን የለም ብለን በዝምታ አለፍን ፡፡

አሁን ደሞ የአዲስ አበባው አስተዳዳሪ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) ‘ተወርዋሪ ኃይል” ብለው ጀባ አሉን፡፡ ሁለቱም የሚሊተሪ አደረጃጀቶች መከላከያን ጨምሮ የትኛውንም የታጠቀ አካልን የመምታት አሊያም የመደምሰስ ጉልበት ያላቸው ይመስለኛል፡፡ እኛን (ሲቭሎችን) ካገኙንማ ሲኖቲራክ ያለፈበት ቲማቲም ያደርጉናል … lol፡፡

ጠቅላይ ሚ/ሩ ለራሱ ልዩ ጦር!
ከንቲባው ለራሱ ልዩ ተወርዋሪ ጦር!

ክልሎች ለራሳቸው ልዩ የጦር ኃይል!
የገንዘብ ያላቸው በተዘዋዋሪ የሚያዙት ጦር!

ምንድነው ይሄ ነገር? ራሳቸውን ከሕዝባቸው ሊጠብቁ ነው ወይስ? ሀገራቸውን ከወራሪ ኃይል ለመጠበቅ? ወይስ አጋዚ መልኩን ቀይሮ እየመጣብን ነው?

አዎን! ፈራሁ! አሁንስ ሰጋሁ!
ለማንኛውም የነገ ሰው ይበለን፡፡ ለአንዳንድ ጉዳዮች ነገን መጠበቅ ግድ ይለናል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ!