October 15, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/157254

ኤልያስ መሰረት እንደዘገበው
የአ/አ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከቦታቸው ሊነሱ እንደሆነ በአንዳንድ ሰዎች ዛሬ ሲገለፅ ነበር። ይህ መረጃ ትክክል እንደሆነ እና ም/ከንቲባው ከሳምንት በላይ ስልጣናቸው ላይ እንደማይቆዩ ታማኝ ምንጮች ማምሻውን አሳውቀውኛል።
ምንጭ 1: “ም/ከንቲባው ስራቸውን ለመቀጠል ፍላጎት ነበራቸው። ነገር ግን ስራቸው ላይ እንደማይቆዩ ላረጋግጥልህ እችላለሁ፣ ምናልባት ከዚህ በሁዋላ አንድ ሳምንት ቢቆዩ ነው። ለምን ሊነሱ እንደተፈለገ ግን ግልፅ አይደለም፣ ምናልባት የፓርቲያቸው ውሳኔ ሊሆን ይችላል።”
ምንጭ 2: “መረጃው ትክክል ነው። አሁን ባለው ጭምጭምታ የገቢዎች ሚኒስትር ሀላፊዋ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ኢ/ር ታከለን ይተካሉ ተብሎ ተገምቷል።”
በዚህ ላይ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰኝ አቀርባለሁ!
ኤልያብ ጌታቸው እንደዘገበው
መደበኛ ባልሆነ መንገድ እየተገለጸ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ እያገለገሉ ያሉት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሃላፊነት የመነሳት ዜና የተለያየ ስሜት ፈጥሮ እያነጋገረ ይገኛል።
ኢንጂነሩ ለምን ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱ በግልጽ የተነገረ ነገር ባይኖርም ሁኔታውን ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተጠርቶ ከነበረው የባልደራሱ የተቃውሞ ሰልፍ እና ሰልፉን ለማቀብ ከተደረገው እንቅስቃሴ ጋር በማዛመድ የጠ/ሚ/ር ዓብይ አሕመድ ካቢኔ እርምጃ አድርገው የሚወስዱት ወገኖች ብዙ ናቸው።
ውሳኔው እውን የሚሆን ከሆነም ከንቲባውን ከሚደግፉትና ከሚቃወሙት ወገኖች የተለያዩ ስሜቶች ሊንጸባረቁ እንደሚችሉ በጉዳዩ ዙርያ ያነጋገርናቸው አካላት የተጠቃለለ ሃሳብ ያመለክታል።
በተቃዋሚዎቻቸው በኩል ምክትል ከንቲባው ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ ሕጋዊ አይደሉም በሚል ሲቃወሟቸው የቆዩ በመሆኑ ዜናውን በመልካም ጎኑ የወሰዱት ሲሆን የትኩረታቸው አቅጣጫ በቀጣዩ ከንቲባ ማንነት ላይ ያተኮረ ሆኗል።
ከንቲባውን የሚደግፉት ወገኖች በበኩላቸው ጉዳዩን በጥርጣሬ እየተመለከቱት ሲሆን ኢንጂነሩ ባለፉት ወራት ሲያከናውኗቸው የቆዩትን ለከተማዋ እድገት የሚጠቅሙ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ማሕበራዊ መግባባት እንዲፈጠር የተጓዙባቸውን ቀና ጎዳናዎችና
የከተማዋ ነዋሪዎች በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች እንዲደገፉ ያደረጓቸውን በርካታ ጥረቶች በማውሳት መረጃው እውነት ከሆነ ከፍተኛ ቅሬታ ሊፈጥር የሚችል እንደሆነ ይገልጻሉ።
በጉዳዩ ዙርያ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን አስተያየት የጠየቅን ቢሆንም ጉዳዩ በይፋ ሳይነገር በፊት ሃሳባቸውን ለመግለጽ እንደሚቸገሩ ገልጸውልናል።
በተባለው ጉዳይ ዙርያ ለመረጃው ቅርበት ያላቸውን ሃላፊዎች ጠይቀን በቀጥታ ምላሽ ባይሰጡበትም ለማስተባበል እንዳልፈለጉ ለመግለጽ እንወዳለን።
የዮናታን ተስፋየ አስተያየት
ሀገሪቷ ገና ብዙ አድካሚ የሴራ መጓተት ይጠብቃታል። በመሃል ቅን ሀገር ወዳድ ታታሪ መሪዎች የሴራው ሰለባ ይሆናሉ። በታከለ መነሳት ስንት ደባ ሲሰሩ ከነበሩት አዴፓዎች በላይ ከጀርባ ሲወጉ እና ሲያስወጉት የነበሩ ኦዴፓዎች ጮቤ ይረግጣሉ። ከጨለምተኛ ተቃዋሚዎቹ በላይ የራሴ የሚላቸው የፓርቲው ሰዎች በደስታ የዘላሉ።
ክፋቱ ገና አንዳቸው በአንዳቸው ላይ መነሳታቸው አይቀርም። የኔ ፀሎት ፈጣሪ አብይን ከነዚህ ደናቁርት የውር ድንብር ክፉ አካሄድ እንዲጠብቀው ነው – ምኞቴ ሳይቀድሙት እንዲቀድማቸው ነው! በሴራ የተጨማለቀ ፖለቲካ ውስጥ ሳይጨማለቁ መንፃት ሳይቆሽሹ መታጠብ የሚቻል አይመስለኝም!
የኢያስፔድ ተስፋየ አስተያየት
እንግዲህ በእንቅስቃሴው ከሚነኩ ቦታዎች አንዱ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር መሆኑን ሰምታችኋል። ከዚህ እንቅስቃሴ ጀርባ ያሉ ሰዎች በሁለት መንገድ ለማትረፍ አስልተዋል። የመጀመሪያው ታከለን ማስነሳት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ታከለ ‘ሰቦና’ ያለው ሰው ስለሆነ አብይ እሱን አውቆ አስነሳው የሚል ዘመቻ በመክፈት አብይንም መምታት ነው። ነገርን ግን ከታከለ መነሳት ጀርባ ያለው አብይ ሳይሆን ራሳቸው ናቸው። በቀጣይ ቀናት ሌሎችም ሪሸፍል የሚደረጉ ቦታዎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በነገራችን ላይ የከተማው መስተዳድር እውቅና ያልነፈገው ሰላማዊ ሰልፍ ለምን ተከለከለ? ማንስ አስከለከለው? የአማራ-ኦሮሞ መንገድ ማን ዘጋው? በእነማን ውሳኔ ተዘጋ? ክስተቱን አጀንዳ ከተወረወረለት ይልቅ አጀንዳ ወርዋሪው ቡድን ብዙ አትርፎበታል።
የስዩም ተሾመ አስተያየት