2019-10-21

በአፍና እና በአፈ-ሙዝ መካከል የሚዋልለው የኦሮሞ ፖለቲካ !!!ሙሉአለም ገብረመድህን

– የኦሮሞን ፖለቲካ በየሳምንቱ ‘ላይድን የተረገመ ነው’ ማለት አይጠበቅብንም!  በአጭሩ በከፍተኛ ህመም ላይ ይገኛል:: ለወጣቶቹ የሥራ ዕድል መፍጠር ያልቻለው አመራር ቅራኔን እያደሰ : ጥላቻን እየጋተ ወጣቱን ዛሬም ወደ ቤቱ እንዳይገባ ጎዳናው ላይ ቆሞ ምኒልክ የሚባል አንድ ሺህ ቶን የሚመዝን ታሪካዊ “ጠላት” ሲፈልግ ይውላል::

– ሐረር- ቆቦ መስመርም ሆነ ኮዬ ፈጨ ላይ ዛሬ ያየነው ይሄንን ነው ። ጣሊያን ራሱ  በዘመኑ ያን የኩራት ምንጭ የሆነን ሰንደቅ ዓላማ  በቄሮ ልክ የሚጠላው አይመስለኝም ። – የኦዴፓ አመራር ኦሮሞ በትግሉ ‘አሰርት’ የሚያደርገውን ነገር ለይቶ ከማቅረብ ÷ በሰጥቶ መቀበል መርሆ ለመደራደር ከመሻት  ይልቅ ጠቅላይነት መገለጫቸው ሆኗል! እናም የኦሮሞ ጥያቄ ‘የእኔ የራሴ ነው የአንተን ግን እንደራደርበት’  የሚል ነው! –  “ኮዬ ፈጨ አትምጣ አዲስ አበባን አምጣ“ – ብላችሁ ልትተረጉሙት ትችላላችሁ ። በሌላ ገፅ [ እንደሚገባኝ] የኦሮሞ ፖለቲካ በአፍ እና በአፈሙዝ መካከል እየዋለለ ይገኛል ። የውስጥ ቅራኔቸው እየተንተከተከ ነው ። ጃዋር የሽብር መተማመኛ ዜግነቱን  ጥሎ ‘ኦፌኮን ይቀላቀላል’ የሚል ጥርጣሬ አይሏል ። ‘ቅራኔ ውስጥ ያሉትን ለማ መገርሳን ቢያስኮበልላቸውስ’ የሚለው ስጋትም ሌላኛው ነው ። ቄሮን በየራሱ የፖለቲካ ፍላጎት ለመቀራመት መተጋገሉ ቀጥሏል ።  ይህች የአደባባይ መሸላለም ቅጥፈት ብየዋለሁ ። ማስመሰልም ሆነ ቅጥፈት ለፖለቲካቸን ባይተዋር አይደሉም ። ቅራኔው አለ! – ምናልባት የሰኔ 15ቱን episode  2 ፍላሚንጎ አልያም መሿለኪያ ወይንም ደግሞ ኢሊሊ ሆቴል ግድም እናየው ይሆናል ። ያኔ የኦሮሞ ፖለቲካ ተጠቃሎ ወደ አፈሙዝ ዞረ እንላለን ። ለጊዜው በአፍና በአፈሙዝ መካከል እየዋለለ ይገኛል!  [ወለጋ በኦሮሚያም ሆነ በፌዴሬሽኑ አባል ስር ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም] Filed in:Amharic