October 24, 2019

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/97762

– እስካሁን ሊገባኝ ያልቻለው ለምን በለሊት ጥበቃ ማንሳት እንደተፈለገ ነው። ከፌደራል ፖሊስም ሆነ ከደህንነት ተቋማት ጋር የነበረኝ ግንኙነት ጥሩ የሚባል ነበር።

– የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ትናንት “ጥበቃዎቹ እንዲነሱ የተፈለገው የፀጥታ ችግር ስለሌለ ነው” ብሎ ነበር። እውነታው ግን ከሁለት ሳምንት በፊት እንቅስቃሴያችንን እንድንቀንስ እና በርካታ ህዝብ ከሚሰበሰብበት ቦታ ከመሄድ እንድንታቀብ ተነግሮን ነበር። እንደውም ተጨማሪ ሀይል ለመጨመር ሀሳብ እንዳላቸው ነግረውን ነበር። ስለዚህ ይህ እየተባለ የፀጥታ አካላቱን ለማንሳት መፈለጋቸው ግር የሚል ነበር።

– ለምን ይህ እንደተከሰተ ሊናገር የሚፈልግ የለም። ጣት መጠቋቆም ብቻ ነው ያለው፣ ይህም የሰው ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል።

– ከጠ/ሚሩ ጋርም ሆነ ከሌሎች አመራሮች ጋር ቁጭ ብለን ማውራት እንችላለን። እኔ ለዛ ዝግጁ ነኝ።

– ጠ/ሚሩ በፓርላማ ያረጉት ንግግር ግርታን ፈጥሮብኛል። ልዩነት ቢኖረንም ጥሩ ግንኝነት ነው ያለን። ከሀገር ከወጡ በሁዋላ በስልክ አላወራንም። ሲመለሱ ግን በሆኑት ጉዳዮች ላይ ብናወራ ፍላጎቴ ነው።

– ሚኔሶታ ስንገናኝ የመንግስት ጥበቃ እንዲኖረኝ የነገሩኝ ጠ/ሚሩ ናቸው። እንደውም መንግስት እንዲህ አይነት ጥበቃ ከመንግስት አካላት ውጭ ላሉ ሰዎች እንደሚሰጥ አላውቅም ነበር። አሁን ላይ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም።

– “መደመር” መፅሀፍን አንብቤዋለሁ። ሀሳቡ ጥሩ ነው፣ ሊሻሻልም ይችላል። ግን እንደ እኛ ላለ ሀገር ፖሊሲ ሲነደፍ ሁሉም ሊመክርበት ይገባል። አሁን እየተሄደበት ያለው መንገድ ግን ግለኝነት ያለበት ይመስላል። መለስ የሰራው አይነት ስህተት ማለት ነው። አብዮታዊ ዴሞክራሲ መጥፎ ሀሳብ አልነበረም፣ ግን ተቃዋሚዎችን ያማከለ አልነበረም ስለዚህ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አጣ። አሁንም ያ ሁኔታ እንዳይከሰት እሰጋለሁ።

– የመሪው ፓርቲ አንድ መሆን ጉዳይ ግን የተቻኮለ ይመስለኛል። አሁን ላይ አስፈላጊም አይመስለኝም። እንዲሁም (ጠ/ሚሩ) የፖለቲካ ስርአቱን አሀዳዊ ለማድረግ ያላቸው ዝንባሌ ላይ ሊያስቡበት ይገባል።

– ውጪ እያለሁ የሆነ ግዜ ፖለቲካውን ትቼ፣ የፌስቡክ አካውንቴን ዘግቼ ወደ ትምህርት እንደማደላ አስብ ነበር። ያ ግን እስካሁን አልሆነም። ዋናው ነገር ግን እኔ እዚህ የመጣሁት ላግዛቸው ነበር፣ ሳግዛቸውም ነበር።

– አሁን ግን ዳር ላይ ሆኜ መቀጠል እንደሌለብኝ እየተሰማኝ ነው። ፖለቲካው ላይ እንድሳተፍ የህዝብ ፍላጎትም አለ። ይህ ተቃዋሚዎችን መርዳት ይሁን፣ ተቃዋሚዎችን እና ገዢው ፓርቲን ማቀራረብ ይሁን እስካሁን አልወሰንኩም። ይህ በቅርብ የመጣ ሀሳብ ነው፣ በተለይ ባለፉት 24 ሰአታት። ከተቃዋሚዎችም፣ ከዢው ፓርቲ ሰዎችም እንዲሁም ከሌሎች ጋር አወራበታለሁ። ዋናው ግን ለሀገር የሚጠቅም ነገር መስራት እፈልጋለሁ።

– አሁን ላይ ሀገሪቱ ባለችበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ እጅግ አደገኛ ነው ብዬ አስባለሁ። ጠ/ሚሩ እንዲሁም አንዳንድ ምርጫውን እናሸንፋለን ብለው የሚያስቡ ፓርቲዎች ምርጫው እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ አውቃለሁ። ምርጫውን ማሸነፍ ይቻላል፣ ሀገር ግን ይጎዳል።

– ዛሬ ከተለያዩ የፖለቲካ አመራሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር አብረን በመሆን መረጋጋት እንዲኖር በአንድ ላይ መግለጫ ሰጥተናል።

በሌላ ዜና!

በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ሰልፉ እና ግጭቱ ዛሬም እንደቀጠለ ሲሆን በአንዳንድ ስፍራዎች ማንነትን መሰረት ያረገ ጥቃቶች እንደተሰነዘሩ መረጃዎች ደርሰውኛል።

እንደ ሻሸመኔ ያሉ ከተሞች እየተረጋጉ ቢሆንም በምስራቅ ሀረርጌ አካባቢ፣ ሮቤ፣ ጎባ፣ አምቦ፣ ድሬዳዋ እንዲሁም ሱሉልታ እና ቢሾፍቱ ግርግሮች እና ጥቃቶች እንደነበሩ ታውቋል። ሌሎች ያልጠቀስኳቸው ከተሞችም እንዲሁ።

በዚህ ሁሉ መሀል በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎችም በአንዳንድ ስፍራዎች ተወስነው እና ሙውጫ አጥተው እንዳሉ ታውቋል። ትናንት የውጭ ሀገር ዜጎችን ለማንሳት ዝዋይ ሄዶ የነበረ ሄሊኮፕተር እንዳረፈ በጥርጣሬ በወጣቶች ተይዞ እንደነበር እና ሁዋላ ላይ እንደተለቀቀ ታውቋል።