በደኖ፣ አርባ ጉጉ በእጥፍ ተደገመ
==================
ይህ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተካሄደ ያለው ሀላፊነት በጎደለው የገዥ ክፍል መሆኑ ደግሞ ርዋንዳን እንድናስታውስ አደረገ፡፡ የርዋንዳ የዘር ፍጅት በ100 ቀናት ውስጥ 800 ሽህ ቱትሲወች ታርደዋል፡፡ ይህ የሆነው በስልጣን ላይ ያለው የሁቱወች መንግስት ይሁንታ ነው፡፡ ከሁለት ቀን በፊት የጀመረው የሀገራችን የዘር ፍጅት እስከ አሁን ከሩቅ በሰማነው ያውም ሪፖርት በሖነው 67 ንፁሀንን ህይወት ቀስፏል። የዘር ዘመቻው አሁንም አልተገታም ይህ እየሆነ ያለው የኦሮሞ ድርጅት የገዥው ክፍል ስልጣን ተረከብሁ ካለው የትግራይ ጠባብ ቡድን ጋር በተለያየ መልክ ትብብር በማድረግ ከ ሜይ 15/2019 ጀምሮ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ የማሳደድ፣ የማሰር እና ግድያ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል። ይህ ወንድም ወንድሙን የሚያርድበት ተውኔት በታሪካችን አይተን የማናውቀውን እንድናይ አደረጉን፡፡ በታሪክም የሚያልፍ ጠባሳ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሰላም እና ፍቅር ባሉት እሬቻ ላይ የጀመረው ዘር ተኮር ዛቻ እና ፉከራ ለዛሬው ወንጀል ቤንዚን እንደሆነ ሊመዘገብ ይገባዋል። በፖለቲካ ታሪኩ አማራን በሜንጫ ማረድ በማለት በቪዲዮ የተቀረጸ መረጃ ያለውን ዘረኛ ግለሰብ ክብር እና ዝና ሰጥቶ የጥላቻ ማስተላለፊያ የሆነውን የቴሌቪዥን ጣቢያ ፈቃድ ለግሶ ባሻው ጥላቻውን እንዲያቀረሽ መደረጉም በስልጣን ላይ ያለው የዘር መንግስት ሀላፊነት ነው።የታላቁን የእኦሮሞ Hዝብ ክብር በእጅጉ የቀነሰ (የሚያሳንስት) ትንሽ ተግባር በወገኖቻችን ላይ ተፈጸመ። ትልቋ ቤተክርስቲያን በርካሽ ዘር ያሰከራቸው ወንጀለኞች ተደፈረች። አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ።፡አድባራትን የሚያገለግሉ አባቶች እና መነኩሳት በስለት ታረዱ። ይህ የሆነው በሀገራችን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስልጣን ላይ እያለ እና ለኦሮሞ መንግስት በሽመልስ አብዲሳ ይሁንታ በመሆኑ እጅግ ሀገራችንን እና ሕዝቧን አንገት ያስደፋ መራር ታሪክ ነው።

በድንጋይ ተወግረው በስለት ታርደው ህይወታቸው ያለፉ ወገኖቻችንን ነስፍ ይማር
ለርዋንዳ ፍጅት ታላቅ አስተዋጸኦ
የ ራዲዮ Radio Télévision Libre des Mille Collines (RTLM) ነበር። በሀገራችን OMN ተመሳሳይ ሚና ወስዷል፡፡ ከታሪክ ያልተማረ ክፉ ታሪክን በዚህ መልኩ ይደግማል

Rwanda

Image may contain: 1 person, beard
Image may contain: one or more people, people standing, people walking, outdoor and nature