October 26, 2019

ኢትዮጵያ ለገጠማት የተሳሳተ ፌዴራላዊ ስርዓት ትግበራ ተጠያቂው የኢህአዴግ የአመለካከት እና የአሠራር ችግር እንደሆነ ተመላከተ።

AMMA : የፌዴራላዊ ስርዓት ጥቅሞች እና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ስርዓት አተገባበር ላይ ያተኮረ ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

የፌዴራል ስርዓት አተገባበር በኢትዮጵያ ሲዳሰስ በርካታ ችግሮች የተስተዋሉበት እንደነበር በውይይት ተገልጧል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም ልዩ ድጋፍ ዳይሬክተር ጀኔራል ረዳት ፕሮፌሰር ደገፋ ቶሎሳ ይህ የመንግስት የአስተዳድር ስርዓት ብሄር ብሄረሰቦች እራሳቸውን በማስተዳደር ማንነታቸውን እንዲያጎሉ እድል የፈጠረ አካሄድ ቢሆንም ያልተገባ ፉክክር በክልሎች መካከል እንዲፈጠር ምክንያት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የፌዴራሊዝም ሙከራ የክልሎች እና ፌዴራል መንግስት ግንኙነትን ያልወሰነ በመሆኑ ታክስን ጨምሮ ችግሮች ተስተውለውበታል ያሉት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ፕላን እና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶከተር ተሾመ አዱኛ ናቸው።

በአንድ ሀገር የማይኖሩ እስኪመስሉ እየታዬ ያለው አለመስማማትም የፌዴራሊዝሙ የአተገባበር ስህተት ማሳያ ሆኖ ቀርቧል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን ደግሞ ኢህአዴግ የጠቅላይነት አስተሳሰብ እና አመለካከት ይዞ በመቆየቱ ለፌዴራል ስርአቱ እንቅፋት ሆኗል ነው ያሉት፡፡

በመፍትሄነት የተቀመጡ ሀሳቦችም አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን በፌዴሬሽን ምክር ቤት ማሳተፍ፣ የኢህአዴግን ውህደት ማጠናከር፣ የሕዝቦችን ተሳታፊነት ማሳደግ እና ችግር ሲፈጥሩ የቆዩ የክልል መንግስታትን ተጠያቂነት ማረጋገጥ የሚሉት ናቸው።

Image may contain: 3 people, people sitting