November 1, 2019
የሀይሌ ገ/ስላሴ ክስ እና የፌስቡክ መልስ! ( ኤልያስ መሰረት )

አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ ትናንት ፌስቡክን ሊከስ እንደሆነ አሳውቆኝ ነበር። እንደ ሀይሌ አገላለፅ “ይህ ሁሉ ትርምስ በፌስቡክ አማካኝነት ሲፈጠር እና ሲራገብ ድርጅቱ ምንም አላረገም።
ሌላ ሀገር ቢሆን ተጠያቂ ስለሚሆን እነዚህን አስደንጋጭ እና ሌሎችን ለጥቃት ለማነሳሳት እየዋሉ ያሉ ምስሎችን እና ቪድዮዎችን ያስወግድ ነበር።
ይህንን አላረገም። መንግስት ድርጅቱ ላይ እርምጃ የማይወስድ ከሆነ እኔ ራሴ ክሱን እመሰርታለሁ። ሀገር በፌስቡክ ሲታመስ ዝም ብዬ አላይም” ብሏል።
በጉዳዩ ላይ ፌስቡኮችን እናግሬ ነበር። የሰጡኝ መልስ ይህን ይላል: “በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት እየሆነ ያለው ነገር ያሳዝናል፣ ጉዳዩም ውስብስብ እንደሆነ እንረዳለን።
የጥላቻ ንግግሮች እና የሀሰት መረጃዎች በድርጅታችን ውስጥ ቦታ እንደሌላቸው አስምረን ልንናገር እንወዳለን። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ሰራተኞቻችን እንዲሁም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አማካኝነት ተገቢ ያልሆኑ ፖስቶችን ማስወገድ እንቀጥላለን።”