November 3, 2019

Source: https://mereja.com/tv/watch.php?vid=ac1d0fb02

Special Wektawi Gudayoch edition with journalist and human rights advocate Eskinder Nega   — Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL Get the latest news and information about #Ethiopia and Ethiopians from #Mereja For …

https://youtu.be/Fi1QvLTdAb8

«በርካታ የግድያ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርሰኛል፤ ጥበቃይከብደኛል፤ ኅሊናዬም አይፈቅደውም» እስክንድር ነጋ

November 3, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/166341

ጋዜጠኛ እና የአዲስ አበባ ባለደራ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆነው እስክንድር ነጋ ትላንት በበርካታ ወጣቶች ተከቦ እንደነበር ለቢቢሲ አረጋግጧል።
BBC Amharic : “ትናንት ቅዳሜ ምሽት 1፡00 አካባቢ፤ ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ከሚገኘው ቢሯችን ስብሰባ ጨርሰን ስንወጣ ነው የተወሰኑ ወጣቶች ናቸው የከበቡን” ይላል እስክንድር።
እስክንድር ቁጥራቸው ከ10 በላይ ይሆናል ያላቸው ሰብሰብ ያሉ ወጣቶች ከቢሮው ውጪ ደጃፍ ላይ ጠብቀው እርሱንና አራት የባልደራስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን እንደከበቧቸው ያስረዳል።
«አልፈናቸው ስንሄድ በከበባ መልክ ተከትለውናል። እንቅስቃሴያቸው አስጊ ስለነበር ወደ ኋላ ተመልሰን ፖሊስ ይዞ እንዲጠይቅልን ሙከራ አድርገናል። ቢሆንም አንዱ ብቻ ነው በፖሊስ ቁጥጥር ሥራ መዋል የቻለው።»
ወጣቶቹ ተቃውሞም ሆነ ጥያቄ አቅርበው ነበር ወይ? ሲጠጓችሁ ዓላማቸው ምንድን ነበር? ተብሎ የተጠየቀው እስክንድር ምንም ያሉን ነገር የለም፤ ነገር ግን በከበባው ውስጥ አስገብተው ተከትለውናል ይላል።
«እኛ ላይ ከሚደርስብን የግድያ ዛቻ አንፃር አስጊ ነበር። እንደዚህ ዓይነት ነገር ተፈጥሮ አያውቅም። ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ብዛት ነበራቸው እና አደጋ ለማድረስ በጣም ቀላል ነበር።»
ወጣቶቹ ጥቃት ሊያደርሱብን ይችሉ ነበር የቦታ መረጣ ጉዳይ እንጂ ብሏል እስክንድር ጨምሮ።
«በእኛ ድምዳሜ ለከበቡን ሰዎች ቦታው አመቺ አልነበረም፤ እኛም ተመለስን። ፊት ለፊታችን ጨለማ ነበር። ከጨለማው ወደኋላ ተመልሰን። እንደ አጋጣሚ አንዲት ፖሊስ ስትመጣ አገኘን። አጠራጣሪ ሁኔታ ስላለ ሰዎቹን እንዲያዙልን እንደምንፈልግ አመለክትን። ተጨማሪ ኃይል ፈልጋ ነበር። በዚያ መሃል ነው እንግዲህ ልጆቹ ተሰባስበው ከአከባቢው የሄዱት።»
ከአንድ ወጣት በቀር የተቀሩት በሚኒባስ እንዳመለጡ የሚናገረው

https://youtu.be/Fi1QvLTdAb8