November 5, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/166821

የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓለም አደባባዮች የሃፍረት ሸማ እንዲላበስ ተደርጓል !-የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት
የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓለም አደባባዮች የሃፍረት ሸማ እንዲላበስ ተደርጓል ሲል የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት አስታወቀ።
ሕብረቱ “በማራቶን ደጋግመን ያሸነፍነውን ያህል፣ ሰሞኑን በጭካኔ ሬከርድ ሰብረናል!” በሚል ርዕስ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ ከ80 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ የቀጠፈውን ክስተት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

ሕብረቱ ለኢትዮ 360 በላከው መግለጫ እንዳለው ኢትዮጵያ ሃገራችን ፈታኝ ወቅት ላይ ትገኛለች።
ሕወሃትን ለማውረድ ብዙ መስዋእትነት የተከፈለበት ለውጥም በመቀልበስ ላይ መሆኑ ሃሜት ሳይሆን ሃቅ ነው ብሏል ሕብረቱ በመግለጫው።
ጁሃር መሃመድ ጥበቃዬ ሊነሳ ነው ድረሱልኝ ብሎ በደረቅ ለሊት ለተከታዮቹ ያደረገው ጥሪ ንፁህና ሰላማዊ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን እንደበግ በገጀራና በቆርቆሮ እንዲታረዱ፣ ቤንዚን ተርከፍክፎ እንዲቃጠሉ፤ በድንጋይ እንደእባብ ተቀጥቅጠው እንዲገደሉ ምክንያት ሆኗል ይላል።
የጀዋር መሐመድ ተከታዮች የገደሏቸው በአብዛኛው “ነፍጠኛ” ከሚሉት የአማራ ወገን ቢሆኑም ይላል መግለጫው ከጋሞ፣ ከጉራጌ እና ከዶርዜ ማህበረሰብ፣ እንዲሁም ሙስሊምም ክርስቲያንም ይገኙበታል ሲል ያስቀምጣል።–ቀሳውስት ታርደዋል፣ ቤተክርስቲያንና መስጊድ፣ የመኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ተቋማት መቃጠላቸውም እንዲሁ።
ሕብረቱ የተከሰተው ጭካኔ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሕዝብ ድንጋጤ ላይ ጥሎት ከርሟል ብሏል።
ትናንት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሰላም የኖቤል ሽልማት ማሸነፍ አገራችን በዓለም ጋዜጦች በአድናቆት ሲዘገብላት እኛ ኢትዮያውያኖች በያለንበት አንገታችንን ቀና አድርገን የነበርነውን ያህል ሰሞኑን በተከሰተው ጭካኔ ደግሞ አንገታችንን እንድንደፋ ተደርገናል ሲል ይናገራል።
ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብም በቀየው በተከሰተው ኢሰብአዊ ድርጊት ከሌላው ወገኑ ጋር እንደተሸማቀቀና በእጅጉ