November 7, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/167648

የሕግ የበላይነትን በማስከበር በኩል ኢትዮጵያ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የዓለም አቀፍ ጥናትን ጠቅሰው አንድ የሕግ ምሁር ተናገሩ፡፡
የሕግ የበላይነትን ማስከበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት በባሕር ዳር ተካሂዷል፡፡
(አብመድ) “የሕግ የበላይነትን ለማስጠበቅ ከእኛ ምን ይጠበቃል?” በሚል ርዕሰ በተካሄደው የምክክር መድረክ የሕግ
የበላይነት በአማራ ክልል ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በማንሳት ውይይት ተደርጓል፡፡ ቀጣይ መደረግ ስለሚገባቸው
ተግባራትም የመፍትሔ ሐሳቦች ተነስተዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህር አቶ ወርቁ ያዜ በአማራ ክልል እየተስተዋለ ያለውን የሕግ ጥሰት አስመልክቶ መነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል። በክልሉ የሕግ የበላይነት አለመከበር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንም አስታውቀዋል። በክልሉም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚስተዋለው የሕግ የበላይነት ጥሰት ከሀገሪቱ የማኅበራዊ፣ የኢኮሚ፣ የፖለቲካ እና የሕግ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡ የሕግ የበላይነት አከባበርን አስመልክቶ በተሠራ ዓለም አቀፍ ጥናት መሠረትም ኢትዮጵያ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ በጽሑፉ ተመላክቷል፡፡
በ2014 (እ.አ.አ) በተሠራ በዓለም አቀፍ ጥናት ከተካተቱት 99 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 88ኛ ደረጃ ላይ ነበረች፡፡ በ2017/18 (እ.አ.አ) በተደረገ ጥናት ደግሞ ከ113 ሀገራት መካከል 107ኛ ደረጃ ላይ እንደነበረች በጥናቱ ተመላክቷል፡፡ የሕግ የበላይነት ጥሰት ፈጣን መፍትሔ የማይሰጠው ከሆነ የጎላ ተጽዕኖ እንደሚያሳድርም ገልጸዋል፡፡ሕግን ማስከበር የሁሉም ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡ ሚዛናዊ እና ምክንያታዊ ትውልድ ለመፍጠር ወላጆች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ ብዙኃን መገናኛ እና የመንግሥት አካላት በታዳጊዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲስሩም አስገንዝበዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም የሕግ የበላይነት ጥሰት ከምንጊዜውም በላይ አስጊ ደረጃ ላይ