November 11, 2019
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ በዚህ ሳምንት ለንባብ በምትቀርበው ዘመን መጽሔት ላይ ስላላፈውና ስለአሁኑ የአገሪቷ ፖለቲካ ጉዳይ ሃሳባቸውን ዘርዝረው አካፍለዋል፤
(ኢ.ፕ.ድ)
• በትክክል ኢህአዴግ ውስጥ የተበላሹ፣የሚያሳዝኑ ብዙ ነገሮች ተሰርተዋል፡፡ እኔም ያለጥፋቴ አስር ዓመቴን አጥቻለሁ፡፡ ይሄ ሆኖ አልፏል፡፡ በዚህ ቁስልና ስሜት መንጠልጠል ለኢትዮጵያ አይጠቅምም፤
• በጥላቻ ላይ፣ በትናንት ታሪክ ላይ ተቸንክረን እሱን እየመነዘርን፤ አንዱ ወደ አንድ አቅጣጫ ሲጎትት ሌላው ወደ ሌላ አቅጣጫ እየጎተተ እሱን ብቻ እያኘክን መኖር አለብን የሚል ስሜት የለኝም፤
• ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት ከነበረው ሁኔታ አንጻር በተለየ ሁኔታ ቢገፋና ለውጥ ባይመጣ ኖሮ ኢትዮጵያ ምን ልትሆን እንደነበረ ሰው አይገነዘብም፡፡ የኢትዮጵያ ውድቀት እነየመን ከወደቁበት በታች ነው የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም የተወሳሰበና የተጠላለፈ በርካታ ችግሮች አሉባት፡፡
• በቡድንም ግጭቶችን ስፖንሰር የሚያደርጉ የጥላቻ ሰባኪ ሚዲያዎችን የከፈቱ አካላት አሉ፡፡
• ሁሉንም የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች በዚህ ደረጃ መፈረጅ ባይቻልም በእያንዳንዱ ድርጅት ውስጥ አንዳንድ ጽንፈኞች አሉ፡፡ ሲናገሩ ግራ ቀኙን ሳይመለከቱ ለግጭት ለጥርጣሬ መነሻ የሚሆኑ ነገሮችን የሚያነሡ አሉ፡፡
•በሕገ መንግሥቱ እጅግ ወሳኝ ሰብአዊ መብቶች ተቀምጠውበታል ነገር ግን ሰዎች ሲኮላሹ ነበር፤ሰው ያለጥፋቱ በሐሳቡ ምክንያት ብቻ ይታሰር ነበር፡፡ እኔ ለዚያ ምስክር ነኝ፡፡
• በእውነት ለመናገር የኦሮሞ ህዝብ ባለፉት ስርዓቶች ተገፍቷል፡፡ የተገፋው ኦሮሞ ብቻ ነው ብለን አናምንም፡፡ ኦሮሞ ከሚገባው በላይ ተገፍቷል፡፡ ይሄ መስተካከል እንዳለበት እናምናለን፡፡ ይሄንን ስናስተካክል ግን ሌላ ቁስል እየፈጠርን ኦሮሞ ከወንድሞቹ ጋር ያልተገባ ግጭትና መፈራራት ውስጥ እንዲገባ ማድረግ አንፈልግም፡፡
• አምቦ የፖለቲካ ስዕሉ ትልቅ ስለሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ኦዴፓም ኪሳራ እንዲደርስባቸው ተብለው የተሰሩ ስራዎች አሉ፡፡ ይህ ተጣርቷል፤ ህብረተሰቡም አውቋል፡፡
• ኤልቲቪ ላይ በነበረኝ ቆይታ ያነሳኋቸው ነገሮች ነበሩ ተቆራርጠዋል፡፡ ያደረግነው የሁለት ሰዓት ውይይት ነው ፡፡ በእኔ ግምገማ የቀረቡት የመጨረሻ መጥፎ መልሶች የተባሉት ብቻ ናቸው፡፡ በተለይ ካነሳኋቸው ሁለት ዋና ዋና ጠቃሚ ጉዳዮች ሆን ተብሎ እንዳይተላለፉ ተደርጓል፡፡ አንደኛ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ አልተመለሰም፣እንዴትስ ይመለሳል በሚል ጉዳይ ላይ ያነሳኋቸው ሀሳቦች ተቆርጠዋል፡፡
ሙሉ መረጃውን በዚህ ሳምንት ለንባብ በምትቀርበው ዘመን መጽሄት ላይ ይጠብቁን
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት