November 11, 2019
የሲዳማ፣የትግሬ፣የኦሮሞ፣የአማራ፣እንዲሁም የሌሎች ብሔር የዘር ፖለቲካ አቀንቃኞች የእናንተ ትግል ሌሎች ብሔሮችን በመግፋት ፣የእናንተ ትግል ሌሎች ብሔሮችን፣በማፈናቀል ነፃ እወጣለሁ ብላቹ የምታስቡ ከሆነ መቼም ነፃ እንደማትወጡ አስረግጪ ልነግራቹ እወዳለሁ።
☞ እኛ ቤት ኦሮሞ ሚስት ናት ፣እኛ ቤት ኦሮሞ እናት ናት፣እህት ናት፣ልጅ ናት፣ሁሉ፣ነገር፣ናት፣ኦሮሞ እንኳን ለሰው ደጅ ላይ ላለው አውሬ እንኳን ወተት የሚያስቀምጥ ትሁትና ገር ነው።
ወይስ አሁን የማናውቀው ሌላ ኦሮሞን ሊያስተዋውቁን ነው የሚፈልጉት ከሚስቴ፣ከቤተሰቤ በላይ ምን አይነት ኦሮሞን ሊያስተዋውቁን እንደሚፈልጉ አይገባንም ሰለ ኦሮሞ ክፉ መስማት አልፈልግም።
☞ ሰለ አማራም ክፋት አትንገረኝ ድንቁርናዬን ጨለማዬን ገፎ እሱ በባዶ እግሩ እየሄደ ለኔ ጫማ ያደረገልኝ ነው ሰለሱ ክፉ መስማት አልፈልግም።
☞ሰለ ሲዳማም ክፉ መስማት አልፈልግም የቃልኪናን የበረከት ህዝብ ነው ክብሩን የሚያቅ በልኩ የሚገኝ ህዝብ ነው ሰለሱ መስማት አልፈልግም ሰለ ጨዋው የትግራይ ህዝብም ሆነ ሰለ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ህብረ ብሔራዊ ህዝቦች ክፋት መስማት አልፈልግም።
☞አንድ ጥያቄ ባለቤቴን ጠየኳት በትግሉ ጊዜ የገፋኝ በድሉ ጊዜ ያካፍለኛል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው።
በትግሉ ጊዜ የገፋኸውን ህዝብ፣አሁን እኔን ያላቀፈ ትግል አሁን እኔን የገፋ ትግል ፣አሁን እኔን ያኮሰሰ ትግል፣አሁን እኔን ያዋረደና አንገት ያስደፋ ትግል፣በድሉ ጊዜ ያኖረኛል እንጀራ ይሆነኛል፣ቤት ይሆነኛል ብዬ መቼም አላስብም።
☞ዘንድሮ የምትታገሉ ታጋዮች እንድታስቡ የምፈልገው ዛሬ የገፋቹት ህዝብ ዛሬ ያፈናቀላቹትን ህዝብ ነገ የጋራ መኖሪያ ቤት እንስራለህ ብላቹ እንደማትፎግሩት እርግጠኛ እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።
☞የዘር ክፋቱ በፀሎት ያለመቀየሩ ነው ስንዴ ዘርተህ ፀልየህ ፆም ፀሎት ይዘህ የዘራኸውን ስንዴ እንጂ በቆሎ አታጭድም ዘረኝነትም ልክ እንደዛ ነው።
☞አንዳድ ሰዎች ሰለ ኢትዮጵያ ያለን አመለካከት እንዲሻፈፍ ይፈልጋሉ።
☞ኢትዮጵያ ትቀጥላለች እንጂ እቺ አገር ጉደኛ ናት ይቺ አገር የአምላክ ካሴት ናት ሳትጨምር ሳትቀንስ ትቀዳለች።
☞ኢትዮጵያ እየተቸገረች ያለችው በጎረቤት እሳት ነው እያነደዱን ያሉት አምናለሁ ገሉ የተሰበረ ቀን እሳቱ እንደማይቀጥል አምናለሁ።
☞እኛ የኢትዮጵያ ወጣቶች ንቅናቄ በተፈጠረ ቁጥር ወየው እያልን ግራ የምናጋባ ወጣቶች አደለንም።ኢትዮጵያ አገሬ ላለፉት 50 አመታት ሰው እንዳላፈራች ያወኩት በአቋራጭና፣በልዋጭ፣በአማራጭ፣መንገስ የሚፈልጉ፣በነሱ ዘመን የተበሉትን ካርታ በኛ ዘመን አሲዘው፣ለማስመለስ የሚጫወቱ ቁማርተኞች ሳይ ነው።
☞በነሱ ዘመን የተበሉትን የፖለቲካ ካርታ ፣የስልጣን ካርታ፣ጃኬትና ጫማቸውን አሲዘው የሚጫወቱ ተስፋ የቆረጡ ናቸው።
☞ ዶክተር ተብለው የአለም አቀፍ ታሪክና እውቀትን ለኛ ያካፍሉናል ስንል ጭራሽ እንደ ዶሮ መንደር ለመንደር ሰፈር ውስጥ ገብተው እንደ ዶሮ አፈርና አቧራ የሚጭሩ ዶክተሮችን ሳይ እጅግ አፍራለሁ።
ኢትዮጵያ በልጆቹዋ ጥረት ታፍራና ተከብራ ትቀጥላለች።
(ብሔራዊ ቲያትር መድረክ ከተደረገ ላይ ካደረገው ካስተላለፈው ገንቢ መልዕክት የተወሰደ)
ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው ገፅ