November 11, 2019

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሚቀጥለው ረቡዕ ተሰብስቦ ውህደቱን ያጸድቃል፤ ከዚያ ቀጥሎ ባሉት ቀናት ደግሞ የኢህአዴግ ምክር ቤት የሥራ አሰፈጻሚውን ውሳኔ ተቀብሎ በማጽደቅ አዲሱ የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይገመታል። በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የትህነግ ጃዋር ኦነግ ሸኔ እና በአማራ፣ በደቡብ፣ በአጠቃላይ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ቅጠረኛ አክራሪ ቡድኖች ሂደቱን ለመረበሽ በከፍተኛ ደረጃ ግጭትና ረብሻ ሊፈጥሩ ይችላሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰው ሕይወትና ነፍስ ላይ በመረማመድ ከየትኛውም ጊዜ በተለየ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኃይሎችን በንቃት በመከታተል፣ የድርጊታቸው ተባባሪ ባለመሆን፣ የሽብርና ትርምስ ምልክቶችንና እንቅስቃሴወችን በማጨናገፍ፣ ያልተረጋገጡ መረጃወችን ባለማሰራጨትና ባለማራገብ እኩይ ዓላማቸውን ማክሸፍ ይገባዋል።

ብሩክ አበጋዝ