ግልጽ አፓርታይድ:-  ለኦሮሞ ተወላጆች ብቻ የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያና የስራ እድል  ተመቻችቷል!! 

ስዩም ተሾመ

ብሔርተኛ ሲባል “ራስ_ወዳድ ጥቅመኛ ነው” የምላችሁ ለዚህ እኮ ነው። በአርከበ_ዕቁባይ ዘመን የትግሬ ብሔርተኛ ከትግራይ ትምህርት ቢሮ ነቅሎ መጥቶ አዲስ አበባ መስተዳድር ውስጥ ከተሰገሰገ በኋላ የከተማውን ነዋሪ ግጦት ሄደ።በታከለ_ኡማ ዘመን ደግሞ የኦሮሞ_ብሔርተኛ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች መልሶ ለመጋጥ እንዲህ አሰፍስፏል። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ባወጣው ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ላይ “የታደሰ የአ/አ መታወቂያ መያዝ” እንደ መስፈርት ተቀምጧል።ከታች በምስሉ ላይ ያለው በኦሮምኛ የተፃፈ መልዕክት በተጠቀሰው ክፍት የሥራ ቦታ ለሚያመለክቱ የኦሮሞ ተወላጆች የአዲስ አበባ #ነዋሪነት_መታወቂያ ለማደል በስልክ ቁጥር 0921879712 ላይ እንዲደውሉ ጥቆማ ይሰጣል። የዚህን ስልክ ባለቤት ጨምሮ በዚህ ህገወጥ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ተጠያቂ ካልሆኑ ከከንቲባ ፅ/ቤት እስከ ቀበሌ ድረስ እየተሰራ ያለው #ወያኔን ለመተካት መሆኑን በተጨባጭ ያረጋግጣል።ለኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ በሚስጥር ሲተላለፍ የነበረው መልዕክት የአማርኛ ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል። የአ/አ (የፊንፊኔ ) ከተማ አስተዳደር በሁሉም የትምህርት መስክ አምስት ሺህ ሰዎችን አወዳድሮ ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የሥራ ማስታወቂያ በማውጣት ገልጿል፣የምዝገባ ቀን 2/3/2012መመዝገቢያ ቦታ አዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮአስፈላጊ መመዘኛዎች— በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ— በ2010 እና 2011የተመረቃችሁ ብቻ— የሥራ ልምድ 0 ዓሠትአንድ ተወዳዳሪ ይዞ መገኘት ያለበትየ10ኛና 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትየ8: 10 12ኛ ክፍሎች ካርድ ኦርጅናልና ኮፒየተመረቁበት ወረቀት ዋናውንና ኮፒውንየታደሰ የአ/አ መታወቂያ መያዝይህን መሥፈርት አሟልታችሁ የአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ የሌላችሁ የኛ ልጆች 0921879712 ላይ ደውሉ -በውስጥ መስመር ብቻ ሼር ተደራረጉ።Filed in:Amharic