የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ አርማ

ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከደረሰውና የሁለት ተማሪዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ግጭት በኋላ በአማራና በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ስጋት መኖሩን ያነጋገርናቸው ተማሪዎችና መምህራን ገልጸዋል።

ካለው ስጋትና ፍርሃት የተነሳም ትምህርት የተቋረጠባቸው ዩኒቨርስቲዎች መኖራቸውን፣ በዩኒቨርስቲዎቹ የመከላከያ ኃይል መግባቱንም ለማወቅ ችለናል።

ትናንት በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ መሞቱ የተሰማ ሲሆን፤ በሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም አለመረረጋጋት ነበር።

ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ጋር በተያያዘ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በአክሱም ዩኒቨርስቲ ግጭት የተጠረጠሩ ተያዙ

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ በስለት ተወግቶ የተገደለው ተማሪ ጥቃቱን ማን እንዳደረሰበት አለመታወቁን የሚናገሩት የዩኒቨርስቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ቡሊ ዮሐንስ (ዶ/ር) ከዚህ ጥቃት በፊትም ሆነ በኋላ በዩኒቨርስቲው ምንም ዓይነት ግጭት አለመከሰቱን አረጋግጠዋል።

ሰኞ ጠዋት በመደወላቡ ዩኒቨርስቲ ከአማራ ክልልና ከኦሮሚያ ክልል በሄዱ ተማሪዎች መካከል በተከሰተው ግጭት ዘጠኝ የሚሆኑ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አቡበከር ከድር (ዶ/ር ) ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በወለጋና በአምቦ ዩኒቨርስቲም ተማሪዎች ወደ ክፍል ገብተው ለመማር ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውንና በግቢዎቹ በጸጥታ አካላት ጥብቅ ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች አስረድተዋል።

ያነጋገርነው የወለጋ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ፤ እሁድ ዕለት የጸጥታ ኃይሎች በዩኒቨርስቲው 610 ሕንጻ ላይ ከገቡ በኋላ ተማሪዎች የመረበሽ ስሜት ውስጥ እንዳሉ ያስረዳል።

የዩኒቨርስቲው የጸጥታ አስከባሪ አካላትና የተማሪው ቁጥር በአቻነት እንደሚገኝ የሚናገረው ይህ ተማሪ፤ ብዙ ተማሪዎች በፍርሃት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ መሆኑን ተናግሯል።

የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስጋት ላይ ነን ይላሉ

በመቱ ዩኒቨርስቲ ብሔር ተኮር ውጥረት ነግሷል

በዩኒቨርስቲዎች የተከሰተውን ችግር ለማረጋጋት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት መግባቱን የየተቋማቱ ተማሪዎችና ኃላፊዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ተማሪዎቹ የጸጥታ ኃይሎች በግቢው ውስጥ ቢኖሩም እንኳ ካለባቸው ፍርሃት የተነሳ ሳይነጣጠሉ በጋራ በመሆን በማሳለፍ ላይ መሆናቸውን ገልጸው፤ የተወሰኑት ደግሞ በዩኒቨርስቲዎቹ አቅራቢያ ወደሚገኝ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ መጠለላቸውን ይናገራሉ።

በወለጋ ዩኒቨርስቲ የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ሌላ ተማሪ ሰሞኑን በወልዲያ ዩኒቨርስቲ በተፈጠረው ነገር ተማሪዎች እጅግ መቆጣታቸውን ገልጾ፤ ሰላማዊ ሠልፍ በማድረግ ድምጻቸውን እንዳያሰሙ ነቀምት ከተማ በሚገኘው ኮማንድ ፖስት ምክንያት አለመቻላቸውን ይናገራል።

ይሁን እንጂ ቁጣና ተቃውሟቸውን የረሃብ አድማ በማድረግ መግለፃቸውን ተናግሯል።

ይሁን እንጂ ቁጣና ተቃውሟቸውን የረሃብ አድማ በማድረግ መግለፃቸውን ተናግሯል።

app-facebookSab Boontuu Koo22 hours ago

Barattoonni Yuuniversiitii Finfinnee obbolaa keenya miidhamaa jiraniif haala kanaan nyaata lagannee gaddaaf mormii keenya ibsanneerra … Fitih le barattoota Oromoo

Image may contain: 9 people, people sitting
Image may contain: 9 people, people sitting
Image may contain: 9 people, people sitting
Image may contain: 3 people, people sitting and people eating
Image may contain: one or more people, crowd and indoor

+6

336301K

End of Facebook post by Sab

“ወንድሞቻችን እየሞቱ፣ ወንድሞቻችን እየተቸገሩ እኛ እንዴት ምግብ እንመገባለን ብለን [ሰኞ] ዕለት ምሳችን ባለመመገብ ሀዘናችንን ገልፀናል” በማለት ዩኒቨርስቲ ውስጥ በብሔር ምክንያት የተፈጠረ ችግር እንደሌለ ያስረዳል።

ቢቢሲ ያነጋገረው የወለጋ ዩኒቨርስቲ መምህር በበኩሉ፤ ተማሪዎች ላነሱት ቅሬታ ዩኒቨርስቲው የሰጠው መልስ እንደሌለ ገልጾ ትምህርት መቋረጡን አረጋግጧል።

“እኛ ለማስተማር ዝግጁ ነን። በየእለቱ ሥራችን ላይ ብንኖርም አንድ ተማሪ ተረጋግቶ መማር የሚችለው በሥነ ልቦና የተረጋጋ አካባቢና ሁኔታ ውስጥ ሲኖር ነው” ብሏል።

ወልዲያ ዩኒቨርስቲ

ሐሰን አሚን ሐሰን በወልዲያ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበረ ሲሆን ሕይወታቸውን ካጡት ሁለት ተማሪዎች አንዱ ነው። አባቱ አቶ አሚን ሐሰን ልጃቸው የተወለደው አባታቸው በሞተ በወሩ መሆኑን ያስታውሳሉ።

አባታቸውን ለማስታወስ በማለትም ለልጃቸው የአያቱን ስም አውጥተውለታል።

ልጃቸው የሞተ ማታ ደውለው እንዳወሩት የሚናገሩት አቶ አሚን፣ ከሐሰን ጋር የአባትና የልጅ ጨዋታ መጨዋወታቸውን በመናገር በእለቱ ስለተፈጠረው ነገር ምንም ነገር እንዳላወሩ ያስረዳሉ።

ስለልጃቸው ሲናገሩም “ጠባዩ ውሃ ነው” በማለት በጎረቤት፣ በወዳጅ ዘመድ በትምህርት ቤትም ሆነ በመስጂድ ምስጉን ልጅ እንደነበር ገልፀዋል።

አስተምሬ ወደ ዩኒቨርስቲ ስልከው ለመንግሥት ነው የሰጠሁት ያሉት አቶ አሚን “ልጆቻችንን ደብተርና ብዕር ገዝተን ልከን እንዴት ሕይወታቸውን አጥተው ይላኩልናል?” ሲሉ ለልጃቸው ሕይወት መጥፋት የፌደራል መንግሥቱን ተጠያቂ እንደሚያደርጉ ያስረዳሉ።

ስለ ስለልጃቸው አሟሟት የሰሙት አስክሬኑን ይዘውላቸው ከሄዱ ሰዎች መሆኑን ገልፀዋል።

ሰኞ ዕለት በወልዲያ ከተማ ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል በሄዱ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ድብደባና ግድያ በማውገዝ ሰልፍ የተደረገ መሆኑን ያነጋገርነው የዩኒቨርስቲው ተማሪ ገልጿል።

አሁንም ቢሆን በፌደራል የጸጥታ ኃይሎች ጥበቃ እንደሚንቀሳቀሱም ጨምሮ ተናግሯል።

“አሁንም ፈርተን አንድ ቦታ ላይ ተሰብስበን ነው ያለነው፤ እኛ ፍላጎታችን ወደ ቤተሰቦቻችን መመለስ ነው” የሚለው ይህ ተማሪ ዩኒቨርስቲው እንዲሄዱ እንዳልፈቀደላቸው ይናገራል።

“መንቀሳቀስ ፈርተናል፤ ራሳችን ወጥተን ለመሄድ ደግሞ [ጥቃት ይደርስብናል] ስንል ፈርተናል፤ መላው ጠፍቶን ተቀምጠናል” በማለት ያለባቸውን ስጋት ለቢቢሲ አስረድቷል።

ሰኞ ዕለት ተማሪዎችን የሚያወያዩ አካላት ለግቢው ጸጥታ እንደሚቆሙ ተናግረው ቢወጡም፤ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚደርስባቸው የሚናገረው ይህ ተማሪ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ እና የአማራ ልዩ ኃይል በብዛት እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ተናግሯል።

በተጨማሪም በወልዲያ ዩኒቨርስቲ የመማር ማስተማሩ ሂደት ሙሉ በሙሉ መቋረጡንና ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሄድ በጋራ እየጠየቁ መሆኑንም አስረድቷል።

በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀሰ ረብሻ የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ

“ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው”

በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተደጋጋሚ የሚነሳው ብሔርን መሰረት ያደረገ ግጭት ምን ያሳያል? ስንል ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ምሁሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና “የአገሪቱ ልሂቃን ወደ ቀኝና ወደ ግራ የወጠሩትን ፖለቲካ ወጣቱ በገባው መንገድ መልስ ለመስጠት ይሞክራል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተውናል።

አክለውም በአገሪቱ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ውጥረት ለእንደዚህ አይነት ግጭቶች መንስዔ መሆኑን ያስረዳሉ።

“በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ልሂቃን የሚያደርጉትን ነገር በግብታዊነት ከማድረግ ባሻገር በኃላፊነት፣ የሚያስከትለውን በማሰብ ስለማይሠሩ እንዲህ ዓይነት የፖለቲካ ውጥረት ሊፈጥ ችሏል” ሲሉም አስተያየታቸውን ያጠቃልላሉ