ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

ሃይሌ አለማየሁ ማን ነው??

Image may contain: 1 person, smiling, beard

ሃይሌ አለማየሁ ከዚህ በፊት ታሪኩን ያስነበኳችሁ የ እስክንድር አለማየሁ ታላቅ ወንድም ነው። በአረመኔውና ፋሺስቱ ደርግ ሁለት ወንድሞቹን ያጣው ታናሽ ወንድማቸው መርድ አለማየሁ የጀግና ወንድሞቹን አጭር ታሪክ ከነፎቷቸው ለወጣቱ ትውልድ ለንባብ እንዲቀርብና ለታሪክ እንዲቀመጥ ፍቃደኛ ሆኖ ስለተባበረኝ ለሱና ለቤተሰቡ ከፍ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ። መፅናናትንም እመኛለሁ።

አብሮ አደጌና የ ሃይሌ አለማየሁ ታናሽ ወንድም መርድ አለማየሁ እንደተናገረው፤…

ሃይሌ አለማየሁ ከአባቱ አቶ አለማየሁ ገ/ ሚካኤልና ከእናቱ ከ ወ/ሮ የሻረግ ገሰሰ በ 1944 ዓ.ም በሐረር ከተማ ተወለደ። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርቱን በ ልዑል ራስ መኮንን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በሐረር መድሃኒ አለም ሁለተኛ ደርጃ ገብቶ ተከታትሏል።
ሃይሌ አለማየሁ የ ሁለተኛ ደርጃ ትምህርቱን ከ ሐረር መድሃኒ አለም በ 1964 ከጠናቀቀ በኋላ ከ እህቱ ጋር እየተቀመጠ በ 1967 ዓ.ም አዲስ አበባ የሚገኘው ዘ ኤኮል ሙኒሲፓሊቲ የ ቴክኒክ ት/ቤት ( The Ecole Municipality Technical college) ገብቶ ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል። ከዚያ በፊትም ለ ሶስት አመት ያህል በዚሁ ተቋም ውስጥ በስራ ተቀጥሮ ሲሰራ ቆይቷል።
አንደበተ ርቱእ፤ በጓደኞቹ በጣም ተወዳጅ የነበረው ሃይሌ ከልጅነቱ ጀምሮ በነበረው የሙዚቃ ፍቅርና ተሰጥኦ ሳክስፎንና ክላሪኔት (saxophone and clarinet ) የሙዚቃ መሳርያዎች ጠንቅቆ መጫወት እንድሚችል በተግባር ያረጋገጠ የዘመኑ ወጣት ነበር።
ሃይሌ አለማየሁ በኢሕአፓነት ተጠርጥሮና በ ደርግ ካድሬዎች ተይዞ በ 1970 ዓ.ም ለእስራት ተዳርጎ ለተወሰኑ ወራቶች አዲስ አበባ በሚገኘው ከፍተና 21 ተብሎ ይታወቅ በነበረው ቀበሌ ከቆየ በኋላ፤ አንድ ቀን ቤተሰቦች ሊጠይቁ ሲሄዱ እንደሌለ ተነግሯቸዋል። እስከዛረም ድረስ የት እንዳደረሱት አይታወቅም። ቤተሰቦቹም የወድ ልጃቸውን አስከሬን አግኝተው የመቅበር እድል እንኳን አላጋጠማቸውም። ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እመኛለሁ።
ሃይሌ አለማየሁ ላመነበት አላማ፤ ህዝባችን ከአንባገነኑና ፋሺስቱ ወታደራዊ ስርአት ተላቆ ህዝባዊ መንግስት እንዲቋቋም ብሎም ዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያ እንድትመሰረት የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ግዴታውን ተወጥቷል።

ክብር የህዝብን ጥያቄ አንግቦ ግንባሩን ለጥይት ለሰጠ ጀግና ትውልድ!!

ለህግ የበላይነት፤ ለሰላም ለዴሞክራሲና ለ እኩልነት..
ሁሉንም ያካተተ የሽግግር መንግስት!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!