
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፉት ሦስት ቀናት አዲሱን የብልጽግና ፓርቲ ለመመስረት የነበረውን ሂደት አስመልክተው መልዕክት አስተላለፉ።
የኢሕአዴግን ውሕደት በተመለከተ፣ አዲሱ ሕገ ደንብ እና ፕሮግራም ላይ መወያየታቸውና ውሳኔዎችን ማሳለፋቸውን ገልፀዋል።
• “ኢትዮጵያ የኢህአዴግ አባት እንጂ፤ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ አባት አይደለም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ መልዕክታቸው የአዲሱን ፓርቲ ስያሜ አስመልክተው “የብልጽግና ፓርቲ” መባሉን በመግለጽ፤”ብልጽግና በቁስ ብቻ ሳይሆን፣ በክብርም በነጻነትም ማረጋገጥ የሚችል ፓርቲ” ለመመስረት መወሰኑን ገልጸዋል።
የፌደራል ሥርዓቱ እስካሁን የነበረበትን ስህተቶች ለማረም በሚያስችል መልኩ የሚደራጅ እንዲሆን መስማማታቸውን በመግለጽም፤ ከአማርኛ በተጨማሪ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሶማልኛ እና አፋርኛ የፌደራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆን መወሰኑን ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት በዚህ መልዕክት ፓርቲያቸው የፌደራል መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጠንክሮ እንደሚሠራም ተናግረዋል።
Facebook post by Abiy Ahmed Ali
Posted by Abiy Ahmed Ali
79,828 Viewsapp-facebook
“ብልጽግና ለኢትዮጵያ በቁስ ብቻ ሳይሆን በክብርም፤ በነጻነትም፤ በሁሉም ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ የሚችል ፓርቲ እንዲሆን እና አሁን ባለችዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተበታተነ ጉልበት ሰብሰብ ብሎ በጋራ መቆምና መምራት እንድንችል መወሰናችን እጅግ በጣም ትልቅ ዉሳኔ ነበር።”
8.3K | 2.9K | 2.3K |
End of Facebook post by Abiy Ahmed Ali
ይህ ኢትዮጵያውያን አንዳቸው ከአንዳቸው ተምረው፣ በጋራ የጋራ አገራቸውን ለመገንባት ያላቸውን ፍላጎት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እርምጃው “እስካሁን ከነበረው በእጅጉ የላቀ እድገት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል” ብለዋል።
ከእዚህ ባሻገር እያንዳንዱ ሕዝብ በልኩ የሚሳተፍበትና ሌላውን የሚያከብርበት የዲሞክራሲ አውድ ለመፍጠር መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።
• “ኢትዮጵያ የኢህአዴግ አባት እንጂ፤ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ አባት አይደለም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ
ኢትዮጵያን በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ወደ ብልጽግና ለማሻገር የነበረውን ትልም ለማሳካት በእጅጉ የሚረዳን ነው በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ግንባሩን በማዋሃድ ወጥ ፓርቲ ለመመስረት በቀረበለት የውህደት ዝርዝር ጥናት ላይ ተወያይቶ በስድስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ከስምምነት ላይ መድረሱ እሁድ ዕለት መዘገባችን ይታወሳል።
በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት የግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል የቀረበውን ሃሳብ ተቃውመው ድምጽ የሰጡት የህወሓት አባላት ሲሆኑ ከቀድሞው የደህንነት ተቋም ኃላፊ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ በስተቀር የህወሓት አባላት መሳተፋቸውን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባል አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ በወቅቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል።