
ዛሬ ከሰዐት በኃላ ከአ.አ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ ካምፓስ በየመግለጫዉ የማይጠፋ ኦብሳ የተባለ ነውጠኛ የጃዋር ቄሮ በግቢው ውስጥ ነውጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀስ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ከግቢዉ አንጠልጥለዉ ወስደዉታል፡፡ 27 ሰዎች ታስረዋል።
የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት/ባልደራስ በተደጋጋሚ ጊዜ የጠራቸውን ጋዜጣዊ መግለጫ እና ስብሰባዎችን ሲረብሽ የነበረው ወጣት ኦብሳ በዛሬው ዕለት መታሰሩ ተገልጿል።
ኦብሳ የተባለው ይህ ወጣት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ግቢ ተማሪ ሲሆን በዛሬው ዕለት የታሰረው አመንቴ ከሚባለው ጓደኛው ጋር አብሮ በመሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ረብሻ ለማስነሳት ሲሞክር መሆኑን የመረጃ ምንጮች አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ ግቢ ከጠዋት ጀምሮ የፀጥታ ችግር መኖሩ ተማሪዎችም ስጋት ላይ በመሆን ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ሆነው መዋላቸውና በኃላም እንደተረጋጋ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ መዋሉ ይታወሳል።
