November 23, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/173442

“46 ዩኒቨርሲቲዎች በመሰረትንበት ጊዜ ሐገሪቱ ውስጥ 46 ጥሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አልነበሩም” ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

የሸገር የአርብ ወሬ — ከፍ ያለ ሀሳብ የሚነሳበት፣ አለም አቀፍ የሆነ የአስተሳሰብ ስብዕና የሚገነባበት፣ ሚዛናዊ እይታ እንዲኖር የሚያቀነቅኑ፣ በደልና ጭቆና ይብቃ የሚል ሰው የሚፈራባቸው ተቋማት ናቸው ዩኒቨርስቲዎች፡፡

እነዚህን የላቁ ተቋማት ለመምራት ደግሞ በእውቀታቸው የተሻሉ፣ ከፊት ሆነው መምራት የሚችሉ ቀንዲል የሆነ አስተሳሰብ ባለቤት የሆኑ ሰዎች እንዲሆኑ ይመክራል፡፡

ለዚህ ደረጃ የሚበቁ ተማሪዎችም ከታች አልያም፣ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ሳሉ ደረጃውን የሚመጥን እውቀትና ስብዕና ላይ የደረሱ ናቸው ወይ? ብሎ መጠየቁ ተገቢ ነው የሚሉ ወገኖችም አሉ፡፡

Sheger FM 102.1 በዚህ ዙሪያ ከታዋቂው ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ጋር ቆይታ አድርጓል…