November 23, 2019
Posted by: ዘ-ሐበሻ
ሲዳማ 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል
የሲዳማ ዞን ቀጣይ ዕጣ ፈንታን ለመወሰን ረቡዕ ዕለት በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ዞኑ የአገሪቱ 10ኛው ክልል የመሆን ድምጽ ማግኘቱን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ::
በዚህም መሰረት በሕዝበ ውሳኔው በመሳተፍ ድምጽ ከሰጠው ህዝብ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት: ማለትም 98.51 በመቶው ዞኑ ክልል እንዲሆን የሚያስችለውን ድምጽ ሰጥተዋል::
በሕዝበ ውሳኔው ውጤት መሰረትም እስካሁን ድረስ ዞኑን በስሩ አድርጎ ሲያስተዳድረው የቆየው የደቡብ ክልል ኃላፊነቱን አዲስ ለሚመሰረተው የሲዳማ ክልል ያስተላልፋል::
ዋና መቀመጫውን በሲዳማ ዞን ውስጥ በምትገኘው በሐዋሳ ከተማ ያደረገው የደቡብ ክልል ለሁለት የምርጫ ዘመን ያህል መቀመጫውን ከአዲሱ የሲዳማ ክልል ጋር ተጋርቶ እንደሚቆይ ቀደም ሲል ተገልጿል::
በሕዝበ ውሳኔው መሰረት አዲስ የሚመሰረተው የሲዳማ ክልል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አንድ አባል ይሆናል::
#etv የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ ውጤት
Posted by Ethiopian Broadcasting Corporation on Saturday, November 23, 2019