November 25, 2019

Source: https://ethiothinkthank.com

የህወሓት ደጋፊ የሆኑ ልሂቃን ነገረ ስራ በጣም ይገርመኛል። በእርግጥ የፖለቲካ ልሂቃን በመንግስት ሥራና አሰራር፣ በማህብረሰቡ ኑሮና አኗኗር ረገድ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመጠቆም፣ እንዲሁም ግፊትና ጫና በማድረግ ለውጥና መሻሻል እንዲመጣ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋፅዖ አላቸው። እንደ ዘፅዓት አናኒያ (በፌስቡክ ስሙ) ያሉ ፅንፈኛ የትግራይ ብሔርተኞች በጭፍን ጥላቻ ታውረው በራሳቸው ህዝብ ላይ ዕልቂትና ጥላቻ ሲደግሱ ይውላሉ።

በእርግጥ ለትግራይ ህዝብ ዋንኛ ጠላቶች የህወሓት አመራሮች እና እንደ ዳንኤል ብርሃኔ፣ ዳዊት ከበደ፣ ፍፁም ብርሃኔ እና ዘፀዓት አናኒያን የመሳሰሉ የትግራይ ልሂቃን ናቸው። ለረጅም ግዜ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች በትግራይ ተወላጆች ጥቃት ደረሰ በተባለ ቁጥር እዬዬ የሚሉት እነሱ ናቸው። እንደ አንድ ብሔር ተወላጅ በደልና ጥቃቱ ጎልቶ ቢሰማቸው አይገርምም። ነገር ግን ውሎ አድሮ በትግራይ ተወላጆች ላይ ደረሰ የተባለው ጥቃት ውሸት ሆኖ ሲገኝ በጉዳዩ ላይ ምንም አይሉም። ይባስ ብሎ ለምሳሌ በጎንደርና ቆቦ በትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ያደረሰው ራሱ ህወሓት እንደሆነ ሲታወቅ አንዲት ቃል ትንፍሽ አይሉም።

አንድ የሌላ ብሔር ተወላጅ ስለ ህወሓትና ትግራይ የሆነ ነገር በተናገር አሊያም በፃፈ ቁጥር ስድብና ዛቻ ለማውረድ፣ የዘረኝነት ሙሾ እያወረዱ ለማልቀስ የሚቀድማቸው የለም። እነዚህ ልሂቃን ራሱ ህወሓት በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚፈፅመው ግፍ ለአንድ ቀን እንኳን ታይቷቸው የማያውቁ ሰዎች፣ ወልዶ ካሳደጋቸው ህዝብ ይልቅ ለህወሓት የጥላቻ ፖለቲካ ተገዢ የሆኑበት መሰረታዊ ምክንያት ከህወሓት አመራሮች ባልተናነሰ አሊያም በላቀ መልኩ በዚህ ተግባር ተሳታፊ ስለሆኑ ነው። ለዚህ ደግሞ ዘፀዓት አናኒያ የተባለው የህወሓት አፈቀላጤ ትላንት ያወጣውን ፅሁፍ እንደ ማሳያ መጥቀስ ይቻላል።

ዘፀዓት ትላንት በፌስቡክ ገፁ ባወጣው ፅሁፍ “መጨውን ግዜ የተሻለ ለማድረግ በትግራይ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ጭቆና ተባብሶ መቀጠል ይኖርበታል” ይላል። የፅሁፉ የአማርኛ ትርጉም ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።

ትንሽ ጭካኒ ወይንም ክፉ ምኞት ሊመስል ይችላል፤ ሆኖም ግን ትግራዋይ አሁን ተብትቦ ከያዘው ህሊናዊ ባርነት እና የመወሰን ችግር ወጥቶ መጪው የትግራይ ሁነታ የተሻለ ለማድረግ፤ ትግራዋይም ሙሉ ፖለቲካዊ ንቃት እንዲይዝና እንደህዝብ ቀጣይ መንገዳችን ማደላደል ከፈለግን ይህ አሁን በሀገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ይሁን በዚህ አገር በትግራዋይ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆናና ግፍ ተባብሶ መቀጠል ይኖርበታል፡፡

ይህ ሲባል እዛም እዚህም ብዙ ወንድሞችና እህቶች በየቦታወ ተበትነው እንዳሉና በነሱ ላይ ምን ሊደርስ እንደሚችል አልጠፋኝም፡፡ ሆኖም ግን የትግራይ እጣ ፋንታ በትግራይ እና ትግራይ ባለው ትግራዋይ ነው መወሰን ያለበት፡፡ በመሀል አገር ያለው የትግራዋይ ሂወትና ንብረት እጃችንና እግራችን እጅ ተወርች ሊያስረን አይገባም፡፡ አለመረጋጋቱና ጥቃቱ መቀጠል ያለበት ምክንያት

  1. ትግራዋይ በተገቢው መንገድ ከእንቅለፉ ስላልባነነ፤ ትግራይ ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ መሀይምነት ሰፊ ስለሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ ትግራዋይ በጎንደር እየታረድ በ”ጎንደር ጎንደር፡ የጀግኖች ሀገር” በሚል ዘፈን የሚጨፍር ትግራዋይ ብዙ ነው፤ አሁንም “ብሂር ብሂረሰቦችና፤የኢትዮጵያ ህዝቦች ተመሳሳይ ህልም አለን፤በአንድነትና በፈቃደኝነት ትባብረን ጠንካራ አገር እንፈጥራለን” ብሎ የሚያምን ብዙ ትግራዋይ (ሙሁሩን ጨምሮ) አለ፡

ዘፅዓት ከላይ የተጠቀሰውን ፅሁፍ አስመልክቶ እነ አምዶም ሰፊ ትችትና ነቀፌታ ሰንዝረውበታlል። እሱም ፅሁፉን ያወጣው ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት በመጠጥ ኃይል ተገፋፍቶ እንደሆነ በመግለፅ ነገሩን ለማድበስበስ ሞክሯል። እውነታው ግን ፅሁፉ የዘፀዓትን ትክክለኛ አቋምና አመለካካት የሚያንፀባርቅ ነው። ይህን ፅሁፍ ያወጣበት ምክንያት ደግሞ ህወሓት እሁድ ዕለት በመቀሌ ከተማ የጠራው ሰልፍ በመሰረዙ ምክንያት በብስጭት የፃፈው ነው።

ህወሓት ውህደቱን ጥሎ በመውጣቱ ምክንያት ብቻውን ተነጥሎ በመቅረቱ እየደረሰበት ያለውን ጫና እና ግፊት ለመቅረፍ ታስቦ ነበር። ሆኖም ግን ህወሓት ገና እንቅስቃሴውን እንደጀመረ ህወሓት “የለቅሶ ሰልፍ ጠራ” እያልን በመጋለጡ፣ የትግራይ ህዝብ ደግሞ በአሁን ወቅት ለህወሓት የድጋፍ ሰልፍ የመውጣት ፍላጎት እንደሌለው በማሳየቱ ፕሮግራሙ ተሰረዘ። በህዝቡ ዘንድ ያለውን የተቀዛቀዘ ድጋፍ በመመልከት ቁጭትና ብስጭት ውስጥ ያስገባው ዘፅዓት “በሀገሪቱ ያለው አለመረጋጋት መቀጠል አለበት፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው ጭቆና እና ግፍ ተበብሶ ሊቀጥል ይገባል” በማለት ፅፏል። ይህ ሃሳብ የፃፈው በስሜት ሳይሆን በተጨባጭ ያለው ነባራዊ ሁኔታ አይቶና አገነዝቦ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።

ከዚህ ፅሁፍ የምንረዳው ሁለት ነገር ነው። የመጀመሪያ የህወሓት አመራሮችና ልሂቃን በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ከሚነሱ ግጭቶች በስተጀርባ እጃቸው እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ሁለተኛ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃትና መፈናቀል የሚያደርሱት ራሳቸው ህወሓቶች ናቸው። በድርጊቱ ላይ ቀጥተኛ ቁጥጥር ወይም ተሳትፎ የሌለው ሰው በሀገሪቱ የሚታየው ግጭትና አለመረጋጋት እንዲቀጥል፣ የብሔር ጥቃቱም እንዲባባስ የውሳኔ ሃሳብ አያቀርብም።

የህወሓት አባላትና ደጋፊ ልሂቃን በትግራይ ህዝብ ላይ የሽብር/ብሔር ጥቃት እንዲፈፀም ጥሪ እያቀረቡ እንደሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ በግልፅ ሊነገረው ይገባል። በተመሳሳይ በየትኛውም የኢትዮጵያ አከባቢ ከሚነሳ ግጭትና አለመረጋጋት በስተጀርባ የህወሓቶች እጅ እንዳለበት ለትግራይ ህዝብ በግልፅ ሊነገው ይገባል። እነዚህ ሰዎች ወልዶና ባሳደጋቸው፣ ራሱን ገብሮ ለስልጣን ባበቃቸው የትግራይ ህዝብ ላይ ጥቃትና ዕልቂት እየደገሱለት እንደሆነ ዓለም ሊያውቀው ይገባል። እንዲህ ያለ አሸባሪ ቡድን የመንግስት ስልጣን ይዞ እንዳለ ዓለም አውቆ በሽብርተኝነት ሊፈረጁ ይገባል።

ይህን የዕልቂት ጥሪ ያቀረበው ዘፀዓት የአዕምሮ መቃወስ የገጠመው ሰው ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። ከዚያ ይልቅ ዘፀዓት (በትክክለኛ ስሙ ዶ/ር ጎይቶም) በመቀሌ አይደር ሆስፒታል የህክምና ዶክተር እንደሆነ ስታውቁ ራሳችሁ የአዕምሮ መቃወስ ይደርስባችኋል። ነፍሰ-ስጋው በጥላቻና ዘረኝነት በሽታ የተበከለ ግለሰብ ህሙማንን እንዴት እንደሚያክም ማሰብ በራሱ ያስጨንቃል።

ዘፀዓት በፅሁፉ ያንፀባረቀው ትክክለኛ አቋምና አመለካከቱን ስለመሆኑ ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም። ከቀናት በፊት ዶ/ር አብይን ከጀርመኑ የናዚ መሪ አዶልፍ ሂትለር ጋር አነፃፅሮ ሲፅፍ አልገረመኝም። በዚህ ፅሁፍ ላይ በትግራይ ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለማስወገድ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና የኤርትራው ፕረዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ መገደል አለባቸው ብሎ ሃሳቡን በይፋ ገልጿል።

የትላንቱ ሆነ ከዚያ በፊት ያወጣው ፅሁፍ የዘፀዓት ትክክለኛ አቋም ስለመሆኑ የሚጠራጠር ካለ ህወሓቶችን ጠንቅቆ አያውቃቸውም ማለት ነው። እንዲህ ያሉ በጥላቻና ዘረኝነት የታጨቁ ፅሁፎች የሚያወጡት በስሜታዊነት ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። ዘፀዓት ከአመስት አመት በፊት የትግራይ ክልል ከአማራ የሚቃጣበትን ጥቃት ለመከላከል አገው እና ቅማንት ላይ የመጠባበቂያ ዞን (Buffer Zone) ማቋቋም እንደሚገባ ፅፎ ስመለከት የአዕምሮውን ጤንነት ተጠራጥሬ ነበር።

አሁን ላይ የአገው ዴሞክራሲያዊ ሸንጎ እና የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የሚባሉ ተላላኪ ቡድኖች መቋቋማቸው ሳይያንስ ከህወሓት ጋር ግንባር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ስለመለከት የታወሰኝ ነገር ቢኖር ከዘፀዓት እብደት ይልቅ የእኔ አላዋቂነት ነው። ይህን እየተናገርኩ የእነ ዘፀዓት ፅሁፍ እንደ ተራ ስህተት የሚያይ ሰው ካለ ነገ ላይ በእውን ሆኖ ሲያየው ቂልነቱን ይረዳል። እነዚህ ሰዎች የለየላቸው አሸሪዎች ናቸው፤ በሆኑት ልክ መጠራትና መዳኘት አለባቸው። በተለይ ይሄ ዘፀዓት የሚባል ግለሰብ በሽብር ወንጀል ሊከሰስ ይገባል።