የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲዎች ጋር ሲያካሂድ የነበረው ውይይት ተበተነ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በምርጫ ማስፈጸሚያ ሕጉ ዙሪያ ዛሬ ማካሄድ ጀምሮ የነበረው ውይይት ባለመግባባት ተቋርጧል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የሥነ ምግባር አዋጅ መጽደቁ ይታወሳል፡፡ የጸደቀው አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ ላይ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ለማድረግ በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ቢሰበሰቡም መስማማት ባለመቻላቸው ስብሰባው ተበትኗል፡፡
የጸደቀውን አዋጅ ብዙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ‹‹ያልተስማማንበት ሐሳቦች አሉበት›› በማለት ከፍተኛ ክርክር አንስተዋል፤ በሦስትና አራት ቀን ውስጥ ያላቸውን ጥያቄ ለምርጫ ቦርድ እንዲያቀርቡም ተጠይቀዋል፡፡
ቦርዱ በበኩሉ ‹‹ለጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት እየተደረገ በመሆኑ የደንብ ማስፈጻሚያው ላይ መወያዬት የግድ ነው›› ብሏል፡፡
የአዋጁ የደንብ ማስፈጸሚያ የፖለቲካ ፓርዎቹ የሚመሩበት በመሆምኑ የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር ፓርቲዎቹ በውይይት ችግሮችን ለመፍታት ከቦርዱ ጋር መወያዬት እንዳለባቸውም ቦርዱ አሳስቧል፡፡
ደንቡ የፓርቲዎችን ተንቀሳቅሶ የመሥራት ሁኔታ የሚያቻችና የምርጫ ሂደቱ የሚመራበት ስለሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምምነት ላይ እንዲደርሱም ተጠይቋል፡፡
Source : AMMA
►