December 5, 2019
Source: https://amharic.voanews.com/a/uganda-anti-corruption-march-12-5-2019/5194199.html
https://gdb.voanews.com/8358ba4e-f196-423d-8152-91aadf07e51a_cx0_cy8_cw0_w800_h450.jpg
ታህሳስ 05, 2019
- ቪኦኤ ዜና

የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ በትናንትናው ዕለት በመሩት ጸረ ሙስና ሰልፍ ላይ ሙሰኞች የህዝብን ሃብት የሚመጠምጡቱ ተውሳኮች ናቸው ሲሉ ተናገሩ። ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ነቃፊዎች ግን ፈጥነው ይሄ ለታይታ እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም ብለዋል፡፡
ዩጋንዳ በዓለም ላይ በከፋ ደረጃ በሙስኛ ከዘቀጡ ሃገሮች መካከል የምትጠራ ስትሆን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ጣታቸውን ይቀስራሉ፡፡
ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል በአምና ሪፖርቱ ዩጋንዳን ሙስና በከፋ ሁኔታ ከተንሰራፋባቸው የአፍሪካ ሃገሮች አንዱዋ አድርጎ አስቀምጧታል።
አክሺን ኤይድ የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅትም በአብዛኛው ተጠያቂው መንግሥታቸው ሆኖ ሳለ የእርሳቸው ጸረ ሙስና ሰልፍ መምራት የሚገርም ነው ብሎታል፡፡