December 7, 2019
Source: https://www.zehabesha.com
የአብይ ለጋዜጠኞች ጥያቄ እምቢ ማለት
፡ሰሞኑን እንደ ዋና የመነገጃ አጀንዳ ሆኖ የተገኘው የአብይ የኖቤል ሽልማትን በተያያዘ ለጋዜጠኞች ነጻ ጥያቄ እምቢ ማለት ነው፡፡ አብይ ከምንሰጠው ምክነያት የተለየ የራሱ የሆነ ምክነያት ሊኖረው ይችላል፡፡ እንደኔ ምክለታ ግን ለአገርና ሕዝብ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘሁት እንኳን እምቢ አለ ብያለሁ፡፡ የአገርና ሕዝብ ጉዳይ ምናቸውም ያልሆኑ ለትችት ተመችቷቸዋል፡፡ እኔ አብይን በብዙ ነገር ከአዘንኩበት ሰው ነው፡፡ አሁንም እንደዛው ነው፡፡ እንደሌሎች አብይ ቅን ነው የሚለውን ቀረርቶ ለእኔ በተግባር ከአደረጋቸው ሴራዊ ድርጊቶቹ በይፋ የማያቸው ስለሆኑ ደጋፊው ሆኜ አደለም፡፡ ይሁንና በራሱም ምክነያት ይሁን እንደተባለውም ለአገር አስቦ ከዚህ መድረክ ራሱን ማግለሉ እንመለካም ውሳኔ ነው የማየው፡፡ ስለምጠላው መተቸት ስለምወደው ማድነቅ አደለም የእኔ እይታ፡፡ ከአገርና ሕዝብ ጋር የሚቃረን ከሆነ ማውገዝ የሚስማማ ከሆነ ማገዝ እንጂ፡፡
ሌላው የኖቤሉን ሽልማት አጠያያቂ ሊያደርጉ የሚሞክሩ አሉ፡፡ አብይ እንደ ግለሰብ የኖቤል ተሸላሚ መሆን ይገባዋል አይገባውም ሌላ ጥያቄ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ሂደትና አፈጻጸም በምድራችን ትልቁ የዓመቱ የሰላም ስኬት እንደነበር አንዳች ጥርጥር የለኝም፡፡ ከዚህ ስኬት በላይ በምድር ላይ ቀድሞ በኖቤል የተሸለመ ሂደት ካልሆነ አንዳች አለ የምትሉ ከአላችሁ ብንሰማው ጥሩ ነው፡፡ እንግዲህ ጥያቄው ይሄ ሽልማት ለአብይ ለብቻው ሳይሆን የብዙ ሌሎች ሰዎችና ይበልጠውንም የኤርትራና ኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በእርስ ለመገናኘት በናፍቆት ያደረገው ጥረት ውጤት ነው ከተባለ በጣም ከሚስማሙትና የሽልማቱም ገጽታ ይሄን ያላበሰ ቢሆን ጥሩ እንደነበር አምናለሁ፡፡ አብይ በአጋጣሚ በነበረበት ስልጣንና ቦታ ጉዳዩን ያስተናገደበት ሁኔታ ከዚህ ሂደት ከላይ ከጠቀስኩት ከሁለቱ ሕዝቦች አስተዋጾ በመቀጠል ከዋነኞቹ አንዱ ተሳታፊ መሆኑንም አያጠያይቅም፡፡ በዚህ ሂደት የኤርትራውም መሪ ኢሳያስ ትልቅ ድርሻ እንደንዳላቸው አይካድም፡፡ ጉዳዩ የዚህ የሰላም ሂደት ብቻ ከተመለከትን፡፡ በፊት የነበረውንና ሌሎች ቦታ የሚያደርጉትን ጥፋት ሳናይ ማለቴ ነው፡፡ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴውም ይሄንኑ ስላለ፡፡ በመሆኑም የኤርትራውም ኢሳያስ የኖቤሉ ተካፋይ ቢሆኑ እንደ ስህተት አላየውም፡፡ ሆኖም ይሄ ኖቤል ሽልማት ከማንም በጸዳ ለሁለቱ አገር ሕዝቦች በልዩ ሁኔታ የተበረከተ ቢሆን ምሳሌነቱም የውሳኔውንም ምሉዕነት የስልማቱንም ውበት በጨመረው፡፡ ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ አሸላለም ኖሮ ላያውቅ ይችላል ሆኖም ይሄ ቢደረግ ለዓልም አዲስ የሠላም ሂደት ምሳሌ ሆኖ ብዙ ሕዝቦች በሠላም ሂደት እንዲሳተፉ አስተማሪ በመሆን መሠረት ይጥላል፡፡ አሸላለሙም የሁለቱ አገራት መሪዎች በተገኙበት በሐይማኖትና አገር ሽማግሌዎች እጅ ቢበረከት መልካም በሆነ፡፡ ያም ሆኖ የሽልማት ኮሚቴው አብይን መምረጡ እንደስህተት አላየውም፡፡ አስተያየት ቢሆን የበለጠ መሆን የሚችለውን እንጂ፡፡ በአጠቃላይ ይህ የሠላም ሂደት መሸለም ነበረበት በኮሚቴው ውሳኔ መሠረት የዚህ ሂደት ተሳተፊ ለነበረው ለአብይ ተሰጠ፡፡ መልም! ለአገር ገጽታም ትልቅ ነው፡፡ ከኢትዮጵያም አልፎ በአፍሪካ ደረጃ ጥሩ እድል ነው! መመቀኛኘት ካልሆነ! ከዚህ በፊት ቴደሮስ አድሀኖም ለአለም የጤና ድርጅት ሲወዳደሩ የቱንም ያህል የወያኔን ጉዳይ አምርሬ ከሚጠሉት ብሆንም ቴድሮስ በኢትዮጵያዊነት በእንዲህ ያለ ኃላፊነት ለመቀመጥ ሲወዳደሩ ከሚደግፏቸው ነበርኩ፡፡ እንዲህ ያሉትን ጉዳዮች ከግለሰቦቹ በላይ አገርንና ሕዝብን ከወከለው ኃላፊነታቸው ጋር አያይዝን ማሰብ ካልቻልን አዝናለሁ፡፡ ቁልፍ ጉዳዩ እዚህ ጋር ነው፡፡ አገርና ሕዝብን ሳይሆን ግለሰቦችን በማመለክ የተበላሸ በባርነት የወደቀ አስተሳሰብ ነው ዛሬ እንዲህ አገርንና ሕዝብን እየጣለ ያለው፡፡ አዝናለሁ! በመሆኑም አብይ የተሸለመው ሽልማት ያላንዳች ጥርጥር ለሂደቱ የሚገባ ነው! ለጋዜጠኞች ጥያቄ መልስ አልሰጥም ማለቱም አሁን ወሮበሎች ወደሚፈልጉት ነገሮችን ለመጠምዘዝ አሰፍስፈው በአሉበት ወቅት ትክክል ነው! አእምሯችን በትክክል የሚያስብ ይሄን እንደግፋለን!
የመቀሌው ስብሰባና የኦብነግ መልስ፡- ሌላው ሰሞኑን ትልቅ ጉዳይ ሆኖ የሰነበተው የመቀሌው በወያኔ ሰብሳቢነት የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ጠላቶች የተሰበሰቡበት መድረክ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወያኔ ጋብዛቸው የነበሩና ግብዣዋን የተቀበሉትና እምቢ ያሉትም የተለዩበት ሁኔታ ሌላው አስገራሚ ነገር ነበር፡፡ በተለይ የኦብነግ ለወያኔ ሰጠው የተባለው ደብዳቤ እጅግ የሚደነቅና የሕዝብና መከራና ግፍ የሚያመው ቡድን መመለስ የሚገባውም ልዩ መሳሌያው መልስ እንደነበር ከኦብነግ ተመልክተናል፡፡ አሁን አሁን እንደምንገነዘበው በዙማሌ ክልል ያሉ ምሁራንና ፖለቲከኞች ከምርም የሕዝባቸው ነገር የሚሰማቸውና ከምንም በላይ ሠላምን ለማምጣት ቆርጠው መነሳታቸውን እያየን ነው፡፡ ከክልሉም አልፈው በአገሪቱ ደረጃ ትልልቅ ምሳሌያዊ የሚሆኑ ተግባሮችንና አስተሳሰቦቹን እያመጡ ነው፡፡ ይገርማል! ለብዙዎቻችን የማናውቀውን የሴማሌን ሕዝብ ፍልስፍናና አስተሳሰብ እያስተማሩን ነው፡፡ ይሄን እውነት የምናየው ከሁሉም ከሰማናቸው ኦብነግን ጨምሮ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችም ነው፡፡ ይሄ የሚያስደስት እውነት ሆኖ በርቱ እንላቸዋለን፡፡ ለብዙዎች የሙስጠፌ ብቻ አስተሳሰብ ለሚመስላቸውም በአጠቃላይ የሱማሌ ምሁራንና ፖለቲከኞች እንዲሁም እነሲህ የወጡበት ማህበረሰብ አስተሳሰብ ጭምር እንደሆነ ስናሰብ እንበረታታለን፡፡
የመቀሌ ስብሰባና የኦሮሞ “ምሁራን” ፖለቲካ፡ በሌላ በኩል ለ27 ዓመት በያኔ ሲገደልና አለ የተባለ መከራ ሲደርስበት የነበረው የኦሮሞ ሕዝብን ወክለንዋል የሚሉ ፖለቲከኞችና ምሁራን ነን የሚሉ እጅግ ሕዝብን አዋራጅ በሆነ የአስተሳሰብ አረንቋ ለራሳቸው መግባታቸው ሳያንስ ሕዝብን የዚሁ አስተሳሰብ ባሪያ አድርገው እየነገዱበት እንዳለ ስናይ እግግ እናዝናለን፡፡ በሰሞኑ በወያኔ ስብሰባ ከተሳተፉት የኦሮሞ ምሁር ነኝ በሚል የኦሮሞን ወጣት በጥላቻና ዘረኝነት ባርነት የሚጥል አስተሳሰብን የሚነዛው አንዱ ሕዝቅኤል ገቢሳ የተባለው እንደሆነ ታዝበናል፡፡ ለነገሩ ወያኔ አስራ መከራ ስታሳየው ሕዝብ ሁሉ ሲጨነቅለት የነበረውም በቀለም ዛሬ ከወያኔ ጋር ወግኖ ስናይ እርግማን ነው እንጂ ምን ይሉታል ብለን ትተንዋል፡፡ የሚያሳዝነው ብዙ ኦሮሞ በእነዚህ ነውረኞች የአስተሳሰብ ባርነት ውስጥ ወድቆ ለገዳዮቹ እያገለገለ አብሮት ሲሞትና ሲሰቃይ የነበረውና በኋላም ከጎኑ የቆመለትን የአማራን ሕዝብ ወያኔ በፈጠረችለት ታሪክ እንደጠላት መቁጠሩ ነው፡፡ አማራን ብቻም ሳይሆን ሌሎችንም ከኦሮሞ ውጪ የሆኑትን እንደሱ መከራን የተቀበሉትን ሕዝብ መጥላት ብቻም በአሳቃቂ ሁኔታ በእነዚህ ሁሉ ግፍ መፈጸምን አምኖ የመቀበሉና የአስተሳሰብ ባርነት ውስጥ መውደቁ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ሁሉም ከእነዚህ ግፎች ራሱን ለመከላከል የሚዘጋጅ መሆኑ ባይቀርም በዚህ አስተሳሰብ ግን እስከመቼ እንደሚቀጥል ሳሰብ አዝናለሁ! ዛሬ ለኦሮሞ የሚስማማው ከሌሎች ጋር የመኖር አብሮነት ሳይሆን ነፍጠኛን እናጠፋለን የሚል አጀንዳን የመነዛለት መርዘኛን ነው፡፡ ከሊቅ እሰከደቂቅ በዋነኞቹ እየተመራ ሕልምና ምኞቱ ይሄ ሆኖ በባርነት ይኖራል፡፡ አዝናለሁ!
ለማና የመረጠው መንገድ፡ ሰሞኑ ለማ የዚሁ አስተሳሰብ አባል እንደሆነ ስለተገለጸ ብዙዎች የተለመደ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የውስጥ አስተሳሰብ እንደሆነ ስለተረዱት ብዙም አልደነቃቸውም፡፡ ለማ በለውጡ ትልቅ ቦታ የነበረውና በሕዝብም ዘንድ ትልቅ ከበሬታ ያገኘ ሰው እንደነበር ራሱም የሚረዳውም ቢሆን ግን ደብቆት የቆየው ይሁን ወይም በሆነ ጊዜ አስቦት ያገረሸበት ማንነት እንደሆነ ባናውቅም አሁን የመረጠውን ምርጫ ምን ያህል ለኦሮሞ የዘረኛና ጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች እንዳስፈነደቃቸው ታዝበናል፡፡ አጋጣሚው ግን ለኢትዮጵያውያን ጥሩ መሆኑን እያየን ነው፡፡ ከኦሮሞ ፖለቲከኛ ከዚህ ያለፈ ማንነት ማግኘት አለመቻሉ ግን እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ አብይ ከዚህ የተለየ ነው የሚል ከአለ ሌላ ስህተት ነው፡፡ አብይ ከኢትዮጵያውያን ድጋፍና ክብር ይልቅ የወሮበላ የኦሮሞ ፖለቲከኞችንና ምሁር ነን የሚሉ አክቲቪስቶችን ለማስደሰት የራሱን ብዙ ከሄደ በኋላ ዛሬ በራሱ ላይ እንደመጣ እያየው ነው፡፡ በኢትዮጵያዊነት መለኪያ ሳይሆን በኦሮሞነት ብዙ ቦታዎችንም በኦሮሞ አሲይዞ ያሳደገችውን የወያኔን ስልት ሞክሯል፡፡ እንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ያየንው ጉድ የሚገርም ነው! የሚያሳዝን ነው! ለማ ሕዝቤን አማክሬ ከአባ ገዳ ጋር ተማክሬ ይለናል፡፡ ለመሆኑ አንድ ፖለቲከኛ የቃደውን ለሕዝብ ያቀርባል እንጂ በየትኛው መስፈርትና ስልት ሕዝብ በሚለው እየተመራ ሕዝብን መሪ እንደሚሆን እንግዲህ የተገለፀለት ልዩ ጥበብ ከአለ አናውቅም፡፡ የሚሊየን ሕዝብ ሐሳብን ሳይሆን ገዥ ሀሳብን ለሕዝብ ማቅረብ ነው የአንድ መሪ ዋና ተግባሩም፡፡ አባ ገዳን የኦሮሞ ሽማግሌውች ማህበር (ስለ አባ ገዳ ጠንቅቄ አውቃለሁ ጠፍቶኝ አደለም) እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ማህበር ኦሮሞን በመወክል አንደሽማግሌ ከሌሎች ሕዝብ ጋር ወዳጅነትና ሠላምን ከመስበክ ይልቅ ዋናኛ የጥላቻና ዘረኝነት አራማጅ እንደሆነ እየተረዳን መጥተናል፡፡ በትላቻና ዘረኝነት የተበከለውን ትውልድ በመገሰፅና በመምከር ወደ መልካም አስተሳሰብ ከማምጣት ይልቅ በጥላቻና ዘረኝነት ትልልቅ ሚና ከአላቸው ጋር በመተባበር ይበልጥ ትውልድን በመርዘኛ የአስተሳሰብ ባርነት እየከተተ ያለ እንደሆነም እያየን ነው፡፡ ሽምግልና ምን ያህል ጉልበት እንዳለው እሳት ሆኖ የወጣውን የአርባምንጭን ወጣት የጋሞ ሽማግሌዎች በብጣሽ ሳር እንዴት እንዳቆሙት ታዝበናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከሽማግሌዎቹ እኩል የሽማግሌዎቹን ቃል ያከበረውን በንዴት እሳት የነበረውን የጋሞ ወጣትም ታላቅነት ያየንበት ነበር፡፡ ይሄ ዛሬ የኦሮሞ ሽማግሌ ለራሳቸው ከጥላቻ ነጸተው ቢሞክሩት እንኳን የሚቀበላቸው ወጣት ለመኖሩ አጠያያቂ ነው፡፡ ለዛም ይመስላል ሽማግሌዎቹ በሽምግልና የተሰጣቸውን ጸጋ ክደው ወጣቱ ያስደስተዋል የሚሉት የጥላቻና ዘረኝነት ተግባሩን የሚደግፉለትና የሚያበረታቱት፡፡
ኢሬቻና መዘዙ፡ ከዚሁ ከኦሮሞ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ኢሬቻና መዘዙ በሚል ፓስተር ቶሎሳ ለሕዝብ ያቀረቡት ትምህርት ሌላው መነጋገሪያ ነበር፡፡ የፓስተሩን ንግግር ለአብዛኛው በኦሮሞነት እምነቱን ለካደ ከጠላት ሴራ ይቆጥረዋል፡፡ እውነቱ ግን እግዚአብሐየርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው እንደተባለው ነው፡፡ ኢሬቻ መሠረቱ ምንም ምን ምን ዛሬ የሚከበርበት ሥርዓት በእስልምናውም በክርስትናውም የባዕድ አምልኮ ለመሆኑ አንዳች ጥርጥር የለም፡፡ ኦሮሞን ለማስደሰት በሚል ብዙ ሌሎች ሕዝቦችም በዚሁ የአምልኮ ሥርዓት ተሳታፊ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ብዙ ኦሮሞ በክርስትናውም በእስልምናውም ለዘመናት ትቶት ከነበረ ከዚህ አምልኮ ተቀላቅሏል፡፡ ይሄ ሁሉ የሆነው ግን በጥላቻና ዘረኝነት ለተበላሸ አስተሳሰብ ባርነት ስለወደቀ ጠላቴ ብሎ እያሰበ ያለውን በተለይም የነፍጠኛውን (አማራን) ሕዝብ የተበቀለ እየመሰለው ነው፡፡ ይሄን ነበር የኦሮሞው መሪም በኢረቻ የአምልኮት ስርዓት ላይ በይፋ እየደነፋ ሲናገር የነበረው፡፡ በጣም አሳዛኝ ነው! እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደድከው መጠን እንድህ ትሆናለህ! በጥላቻ እብድ ትሆናለህ! ዛሬ የምስጋና ቀን በሚል ግልጽ የሆነውን የባዕድ አምልኮ ለመደለል ብዙ ተኬዷል፡፡ የኋላ እውነታውን ግን ከማንም በላይ በዚህ አምልኮ የኖሩ ኦሮሞ የሆኑ ራሳቸው አሳምረው ያውቁታል፡፡ ይሄን ነበር ፓስተሩ የተናገሩት! ዛሬ እየሆነ ያለው ከዚሁ የባዕድ አምልኮ መንፈስ ጋር ነው ሲሉም ለብዙዎች መቀለጃ ሆነዋል፡፡ እውነቱ የኖህ ዘምን አይነት ነው! የጥፋት ውሃ አንገታቸው ደርሶ እያጠፋቸውም ከሀጥያታቸው መመለስን እንዳያስቡ አእምሮአቸው ተጋርዷልና፡፡ እንዲህ በግልጽ ዛሬ አይኑ እያየ የሚገድለውንና ብዙ ግፍ ለሚያደርስበት እየሰገደ አብሮት ግፍ የተቀበለውን ሌላውን ወንድሙን ለመጥላት ያስቻለው ለዘመናት በሐሰት የተነገረውን እያመና አይኑ የሚያየውን አውነት እንዲክድ ያደረገው ምን እንደሆነ ማሰብ ሲገባን እንዴት ክፉ መንፈስ እንደሚሰራ እንረዳለን፡፡ አዝናለሁ!
ዘሐበሻና የኦብነግ መሪ ንግግር፡ ሰሞኑ ሌላው በኬንያ የኦብነግ መሪ የብልጽግናን ፓርቲ እቃወማለሁ የሚል አንድምታ ያለውን አርዕስት የያዘ የኦበነጉን መሪ ንግግር በዘሐበሻ ፌስቡክ ገጽ ላይ አይተናል፡፡ ገበያ ለማግኘት እንዲህ ያለ አስነዋሪ ድርጊት የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ የኦብነጉን መሪ ንግግር ዝርዝር ግን ስናነብ አንዳችም ከተሰጠው ርዕስ ጋር አለመገኛኘቱ ብቻም ሳይሆን ይበልጡንም በመልካም እይታ የተመላ እንደሆነ ታዝበናል፡፡ የኦብነጉ መሪ ሲጀምር ስለ ብልጽግና ፓርቲ ለማውራት ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ ምክነያቱም አያገባቸውምና ነው፡፡ ሊያወሩ የሞከሩት ስለራሳቸው ፓርቲ ነው፡፡ ያም ሆኖ የብልጽግ ፓርቲ ዋና የሆነውን አብይን ግን ደጋግመው እያወደሱ ሲናገሩ ነው የተነበበው፡፡ በአጠቃላይ የኦብነጉ መሪ እንደራሳቸው ፓርቲ ማውራት ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ ሠላም ለማምጣት ያላቸውን ተስፋና በዛም በሠላማዊ መልክ ተፎካካሪ ሆነው ለመቅረብ እንዳቀዱ ከመናግር ያለፈ አንዳች ስለ ብልጽግናም ሆነ ሌላ ፓርቲ ያወሩት መጥፎ ነገር የለም፡፡ እንግዲህ የሰዎችን አእምሮ የሚያስደስተው የመጥፎ ዜና ነው በሚል እምነት እየተዘፈቀ ያለው ንግድን ታሳቢ በማድረግ የሕዝብና አገርን ጉዳይ ለራስ ጥቀም ማትረፊያ ለመጠቀም የተለመደ እየሆነው በመጣው ስልት አንዳች የተቃውሞ ሀሳብ የሌለው የኦብነጉ መሪ ንግግር በአየንው መልክ በአስገራሚ የተቃውሞ ርዕስ ተጋብዘናል፡፡ ዘሐበሻ ርዕሱን ያገኘሁት ከኬንያው ዘጋቢ ነው ሲል ስህተቱን ለለማመን እኛን ሊያሳምን ሞክሯል፡፡ አሳፋሪው ነገር ግን ከታች የሚነበበውን እውነት ሳይሆን ከላይ ገበያ ለማግኘት እየተጠቀመበት ካልሆን መረጃውን ከሚነበበው እውነት ጋር የሚያዛምድ ርዕስ በሰጠው ነበር፡፡ እግረ መንገዱንም ኃላፊነትን መወጣት በሆነለት፡፡ ይህ አልሆነም! አዝናለሁ!
በአጠቃላይ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የምመክረው ነገሮች በማስተዋል ይሁን፡፡ ማንንም በመጥላትና በማምለክ በሚመስል ደጋፊነት አይሁን! እውነትን እንፈልግ! ለሕሊና ክብር ነውና! እኔ የኢትዮጵያን ትውልድ ወደ በጎ አስተሳሰብ ሊወስድ የሚችልን ልዩ አጀንዳ በሰፊው ለማሰራጨት የሚያስችል ሥራን ለመሥራት የሚችሉ ምሁራንና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች በአንድ ላይ ሆነው የራሳቸው የእውነትና ለትውልድ መዳን በጎ አስተዋጾ የሚያበረክት የመረጃ ማሰራጫ ቢኖራቸው እላለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ለመተባበር የሚፈልግ ከአለ አሁን ትልቅ መሠረት ለመጣል የተጀመረ ሐሳብ በአንዳንዶች እየተሰራጨ ስለሆነ የዚህ ሀሳብ ምሰሶ የሆኑ ጉዳዮችን ለማካፈል ፍቀደኛ ነኝ፡፡ በዚህ ሂደት ለመሳተፍና የበለጠ ሀሳቡን በማጎልበት በቶሎ ለሕዝብ በሚደርስበት የራሱ በጎ አስተዋጾ ለማበርከት የሚፈልግ ከአለ ይሄን ጽሁፍ በሚያስተናግደው ሚዲያ በኩል ሐሳቡን ለማካፈል ፍቃደኛ ነኝ፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር በጎ ማሰብን ይስጠን! አገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቅ! አሜን!