10 ዲሴምበር 2019

በኖርዌይ የሚገኙ ኤርትራውያን

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን የሰላም የኖቤል ሽልማት በመቃመወም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ሰልፈኞች በኖርዌይ መዲና ኦስሎ መፈክራቸውን አንግበው ወጥተዋል።

በትናንትናው ዕለት በኖርዌይ የሚኖሩ ኤርትራውያን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሽልማት ለሰጠው የኖቤል ኮሚቴ “የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰላም በሚገባ አልተረጋገጠም፤ የኖቤል ሽልማት ሊሰጣቸው አይገባም” በሚልም ተቃውሟቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት

ከተለያዩ የኖርዌይና የስዊድን ከተሞች የመጡ 250 የሚጠጉ ኤርትራውያን “በሰላም ስም ሳይታሰብበት ሽልማት ሊሰጥ አይገባም፤ በተግባር እንጂ የወሬ ሰላም አንቀበልም” የሚሉ የታቃውሞ ድምፆችን በማሰማት ወደ መንግሥታዊ ተቋማትም አምርተዋል።

የኤርትራ መንግሥትን በተመለከተ የተለያዩ ስር ነቀል ለውጦች ሊመጡ ይገባል በሚል የሚንቀሳቀሰው በኖርዌይና አካባቢው የሚገኝ የ ‘ይበቃል’ (ይአክል) ኮሚቴ ለሦስት የመንግሥት ተቋማት ደብዳቤ እንደፃፈ የኮሚቴው ሊቀ መንበር ቲቲ ኃይለ ለቢቢሲ ገልፃለች።

ቲቲ እንደምትለው፤ ለኖርዌይ መንግሥት በአካል፣ ለኖቤል ኮሚቴ በአድራሻቸው እንዲሁም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ደግሞ በኢሜይል ያላቸውን ተቃውሞ አድርሰዋል።

የይበቃል ኮሚቴ ፀሐፊ ይብራህ ዘውደ፤ ምንም እንኳ ኤርትራና ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ቢፈራረሙም “መሬት ላይ ያለውን እውነታ ስናይ ወደ ተግባር የተሸጋገረ ነገር እንደሌለ” ይናገራል።

የኤርትራ ሕዝብ የጠበቀውና የተመኘው ለውጥ እንዳልመጣ በመግለፅ፤ በሁለቱም አገራት የሰላም ስምምነት አማካኝነት የተሰጠው የኖቤል ሽልማት ፍትሃዊ እንዳልሆነም አክሎ ገልጿል።

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ክፍፍልና ጠብ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ለሁለት አስርት አመታት ተቋርጦ የነበረው የስልክ፣ የበረራ መስመሮች ተጀምረዋል። ለአጭር ጊዜ ቢሆንም የተዘጉ ድንበሮች ተከፍተው የተለያዩና የተነፋፈቁ ሕዝቦች መገናኘታቸውን ብዙዎች በበጎነት የሚያዩት ተግባር ነው።

በኖርዌይ የሚገኙ ኤርትራውያን

ይሁን እንጂ እነዚህ መልካም ጅምሮች እንዳሉ ሆነው፤ በሁለቱ አገራት መካከል በተጨባጭ የመጣ ሰላም አለመኖሩን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊገነዘብ እንደሚገባው ተቃዋሚዎቹ ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንም እንኳን ጅምሮቻቸው መበረታት ቢገባቸውም፤ ሽልማቱ የሁለቱን አገራት መሬት ላይ ያለ እውነታ የሚያንፀባርቅ እንዳልሆነ ከተቃዋሚዎቹ መካከል ለይላ ካሊድ ታስረዳለች።

ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . .

ፊንላንድ በዓለም በእድሜ ትንሿን ጠቅላይ ሚኒስትር መረጠች

“በሌላ በኩል የኤርትራ ሁኔታ እየባሰ እንጂ እየተሻሻለ የመጣ ነገር የለም፤ የተከፈቱ ድንበሮች ተዘግተዋል፤ ሕገ መንግሥቱ አሁንም ቢሆን ሥራ ላይ አልዋለም፤ ለተወሰነ ጊዜ መሆን የነበረበት ብሔራዊ አገልግሎት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ለማስገንዘብ ጭምር” የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ትናገራለች።

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ኖርዌይን ጨምሮ የተለያዩ የአውሮፓ አገራት ለኤርትራ እያደረጉት ካለው ድጋፍ ባሻገር በአገሪቷ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በደል እንዲወገድ ከሕዝቡ ጎን ሊቆሙ እንደሚገባ ለይላ አበክራ ትናገራለች።

“የኤርትራ ሕዝብ ሰላምና ፍቅርን ይፈልጋል ይሁን እንጂ የናፈቀውንና ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለበትን ሰላም ሊያገኝ አልቻለም” ያለው ይብራህ፤ “በተግባር የሚጨበጥ ሰላም እንጂ የወሬ ሰላም አንቀበልም” በማለት መረር ባለ ቃል መልእክቱን አስተላልፏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከጋዜጠኞች ጋር ሊያደርጉት የነበረው ቃለ መጠይቅ አልሳተፍም ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኖ ሰንብቷል።