December 13, 2019

Source: https://amharaonline.org

የአዲስ አበባ ጉዳይ

የጠሚ አብይ አህመድ መንግስት ትሩፋቶች ለአዲስ አበባ።

1ኛ. አዲስ አበባ እራሷን በራሷ የምታስተዳድር የፌደራሉ ከተማ እንደሆነች ዶክተር አብይ “አይቀየርም” ያለው ሕገ መንግስት ይደነግጋል። ሆኖም ከተማችን ህገ መንግስቱ በሚለው መሰረት ራሷን በራሷ እያስተዳደረች አይደለም። በተወካዮች ምክር ቤትም ድምፅ ሳይኖራት ዶክተሩ በሚመራው #ኦዴፓ ሹመኞች እየተዳደረች ትገኛለች። ይህ በጠሚዶአ “ይከበር” የሚባለው ሕገ መንግስት አዲስ አበባ ላይ እንዳይሰራ ተደርጓል።

2ኛ. አዲስ አበባ #የሸዋ እንብርት ናት። በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ግማሽ ሚሊዬን ኦሮሞዎችን ከሱማሌ ክልል አምጥቶ አስፍሯል። ለአሁን በእቅድ የተያዘው 2 ሚሊዬን ኦሮሞዎችን ማስፈር ነው።

ለወደፊትም በስፋት ይቀጥላል። አላማው በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ያሉ ሌሎች ብሔሮችን #በመዋጥ/በማጥፋት ህብረ ብሄራዊ የሆነችውን ሸዋን በአጠቃላይ በኦሮሞ ቁጥጥር ስር ማድረግ ነው።

(የሸዋን ዲሞግራፊ መቀየር ያስፈለገው
2.1. በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚገኘው የኦሮሞ ቁጥር በጣም አናሳ ነው። ከ80% በላይ የሚኖረው ማህበረሰብ ኦሮሞ አይደለም። ሸዋ አዲስ አበባን ያቀፈ ስለሆነ ሙሉ በሙሉ ከሐረርጌና መሠል አካባቢዎች በመጡ ኦሮሞዎች ከተዋጠ በቀላሉ “የአዲስ አበባ ዙሪያ ነዋሪው ኦሮሞ ነው፣ አዲስ አበባ በኦሮሞ ስለተከበበች የኦሮሞ ይዞታ ከጥንትም ነበረች” የሚለውን #የፈጠራ ታሪክ ለማጠናከርና የሚያልሟትን አዲስ አበባን ፊንፊኔ የማድረግ ፕሮጀክትን ለማስቀጠል እንዲረዳ ነው።
2.2 ኦሮሞ ሸዋ ላይ በቁጥር ካነሰ ኦሮሚያ የተባለው የጨረቃ ክልል #ለሁለት ይከፈልብናል ብለው ስለሚፈሩ ነው። ኦሮሚያ ደግሞ ለሁለት ከተከፈለ ታላቁን የኦሮሚያ ኢምፓየር መመስረት አይቻልም። )

3ኛ. የአዲስ አበባ ነዋሪ ላልሆኑ ከ100 ሺህ በላይ ኦሮሞዎች በልዮ አሰራር የአዲስ አበባ መታወቂያ #አድሏል። አላማው አዲስ አበባን በኦሮሞ አጥለቅልቆ በማስዋጥ ወደፊት ምርጫዎች ሲካሔዱ የሌላው ድምፅ እንዳይሰማ ማፈን ነው።

4ኛ. በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ህገ ወጥ በሚል ታርጋ ሌሎች ብሔሮች በብዛት የሚኖሩባቸውን ሰፈሮች በማፍረስ #እያፈናቀለ ነው። አላማው አካባቢውን ከሌሎች ብሔሮች በማፅዳት ኦሮሞንና ኦሮምኛን ብቻ በቦታው በመተካት ማጠናከር ነው።

5ኛ. አዲስ አበባ ነዋሪ የራሱን ከንቲባ መርጦ እንዳያስቀምጥ መንገድ #ዘግቷል።

6ኛ. በባልደራስ ሲጀመር 10,000 ኢትዮጵያውያን የተገኙበትን ስብሰባና ቀጣይ ስብሰባዎችና መግለጫዎችን በፓሊስና በአደራጃቸው ቄሮዎች አደናቅፏል። ማናቸውም የመንግስት ሚዲያ ተቋማትም ዜናውን እንዳይዘግቡ አድርጓል። አባላቶቹንም ለእስር ዳርጓል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ድምፅ የመናቅና የማፈን አንዱ አዲስ አበባን የኦሮሞ ክልል አካል የማድረግ ስልት ነው።

7ኛ. የአዲስ አበባ ወጣቶችን ለማሸማቀቅ ለእስር ዳርጓል። የእስሩ አላማ ወጣቱ ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎችን ወደፊት እንዳያደርግ መቀጣጫ ኩርኩም መሆኑ ነው።

8ኛ. የኦሮሚያ ክልል ልዮ ሐይል አዲስ አበባ እንዲሰፍር ውሳኔ ተደርሷል። አላማው ከባልደራሱ ስብሰባ መልስ አዲስ አበቤ አቋሙን ስላሳወቀ የማይቀረውን የአዲስ አበቤን አመፅ #ማፈን ነው።

9ኛ. ያለአዲስ አበባ ነዋሪ ፈቃድ ኦሮምኛ ትምህርት በአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ #እንዲጫን አድርጓል።

10ኛ. የኦሮሞ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለመመስረት ለተቋቋመው ህገወጥ ኮሚቴ በተለያየ መልኩ ድጋፍ አድርጓል። ይህ ህገወጥ ኮሚቴ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ሲል መንግስት በፈቀደለት ተቋም በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።