ወገን ሆይ! አዲስ አበባ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ የኦሮሚያ ክልል ወደሚሉት መጠቃለሏን ታውቃላቹህ ወይ???
ዐቢይ በቅርቡ አምቦ ከተመረጡ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ባደረገው ስብሰባ ላይ የኢሬቻን አዲስ አበባ መከበር በማሳያነት በመጥቀስ አዲስ አበባን በእጃቸው ማስገባታቸውን ተናግሮ እንደነበር ከተለያዩ ምንጮች ሲዘገብ ሰንብቶ ነበር፡፡ ይሄው እየሆነ ያለው ነገር ሁሉም ይሄንን የሚያረጋግጥ ሆኗል!!!
ወገን ሆይ አዲስ አበባ በለሆሳስ ስትጠለፍ ዝም ማለት ይኖርብናል ወይ??? ለመሆኑ አዲስ አበባ ኦሮሚያ ወደሚሉት ተጠቃለለች ማለት ምን ማለት እንደሆነ ይገባሃል ወይ??? የተለያዩ ሁነቶች ይሄንን እያሳዩ እንደሆነ በግልጽ መመልከት ይቻላል!!!
ለምሳሌ፦
1ኛ. ዛሬ ምሽት አቶ ንጉሡ ጥላሁን ነገ ስለሚደረገው የአቶ ዐቢይ አቀባበል ሥነሥርዓት በሰጠው መግለጫ “ሥነ ሥርዓቱን የጠ/ሚ ቢሮ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና ከአዲስ አበባ መሥተዳድር ጋር የሚያስፈጽሙት ይሆናል!” ብሏል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚፈጸም ሥነሥርዓት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሚሉትና የጸጥታ አካላቱ ምን አግብቷቸው እንደገና ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ የት ሔደው ነው እነሱ የሚያስፈጽሙት???
2ኛ. የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል አዘጋጅ ኦሮሚያ የሚባለው ክልል ነበር፡፡ አዘጋጁ ኦሮሚያ የሚሉት ክልል እንደመሆኑ መደረግ የነበረበት ናዝሬት ነበር፡፡ ኦሮሚያ የተባለው ክልል በምን ሥልጣኑ ነው የራሱ ባልሆነ ቦታ አዲስ አበባ ሊያዘጋጅ የቻለው???
3ኛ. በቀደምለት የኦሮሚያ ክልል የሚሉት ባለሥልጣናት እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ “የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ቢሮ ግንባታ!” ብለው የመሠረት ድንጋይ መጣላቸውን ኢቴቪ ዘግቦ አሳይቶናል፡፡ ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ??? ሌሎች ክልሎችስ ይሄንን ማድረግ ይችላሉ ወይ???
ወገን ሆይ! ዝም ብሎ መመልከቱ ችግርና ዕዳ ሲያመጣብህ፣ ወደባሰ ቀውስ ውስጥ ሲከትህ እንጅ መፍትሔ ሲያመጣልህ አላየህምና ሳይመሽብህ በጊዜ ቁጣህን አሰማና ከተማህን ከጅቦች እጅ አድን!!!
ብአዴን፣ አብን ምንንትስ የምትላቸው ሁሉ አንተን እያጃጃሉ የሚያስበሉ እንጅ ለመብትህና ለጥቅምህ የሚታገሉ አይደሉምና እነሱን አትጠብቅ አትመልከት!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው