December 16, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/181644
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/26588938_2_dwdownload.mp3

DW : ኢትዮጵያዉያዉን ከሰላም ኖቤል ሽልማቱ ድግስ፣ ግብዣ፣ ከደስታ፣ ፌስታ አቀባበሉ ቱማታ በኋላ ያዉ «ሥራ-አለ እንደገና» ከሚሉበት ደርሰዋል። የዘንድሮዉ የሠላም ኖቤል አሸናፊ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ሽልማቱን ሲቀበሉ እንዳሉት «ሠላም እንደ አትክልት እፅዋት፣ ሰብል ሁሉ የማያቋርጥ እንክብካቤ ትፈልጋለች።
ጠቅላይ ሚንስትሩ የሠላም ኖቤል ከተሸለሙ ካለፈዉ ጥቅምት፣ ሽልማቱን እስከተቀበሉበት እስካለፈዉ ሳምንት ድረስ ብቻ ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ በሐገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ የጎሳና የፖለቲካ ግጭት በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል፣ በሺሕ የሚቆጠሩ ቆስለዋል፣ በብዙ መቶ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር የደሐ ሐብት ንብረታቸዉ ወድሟል፣የኃይማኖት ተቋማት ጋይተዋልም።
የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በተለይ የገዢዉ ፓርቲ መሪዎች ግን ግጭት ግድያዉን ለማስቆም ከሚያደርጉት ጥረት ይልቅ ጎራ ለይተዉ አዲስ አበባ እና መቀሌ ላይ የብልፅግና ፓርቲ እና የፌደራሊስት መድረክ ያሏቸዉን የፖለቲካ ስብሰቦች መመስረታቸዉን እየነገሩን ነዉ።
ስለብልፅግና ፓርቲ መመሥረት ከዚሕ ቀደም ከአንዴ በላይ ባለሙያዎች በማወያየታችን ዛሬ በቀጥታ አንደግመዉም ይሁንና ብልፅግና ፓርቲን እየጠቀስን ከብልፅግና ፓርቲ መመሥረት ጥቂት ዘግይት ብሎ መቀሌ ላይ የተመሰረተዉን «የፌደራሊስት ኃይላት መድረክ» ወይም ፎረምን አመሠራረት፣ ዓላማና የገጠመዉን ተቃዉሞ አንስተን  እንወያየለን። Audio Player00:0000:00Use Up/Down Arrow keys to increase or decrease volume.Filed in:Amharic