
Reuters
የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሴኔት ፊት ቀርበው የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ በትናንትናው ዕለት ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።
ዶናልድ ትራምፕ በተወካዮች ምክር ቤት ሴኔቱ ፊት ቀርበው ክሳቸውን እንዲከላከሉ ሲደረግ በታሪክ ሶስተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ናቸው።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሴኔት ፊት ቀርበው ክሳቸውን ሲከላከሉ የሚሰጠው ውሳኔ በስልጣናቸው ላይ መቀጠል አለመቀጠላቸውን ለመወሰን ይረዳል።
• እሷ ማናት፡ ከሊስትሮነት እስከ ከተማ አውቶቡስ አሽከርካሪነት
በትናንትናው ዕለት ምክር ቤቱ በፕሬዝዳንቱ ላይ በቀረቡ ሁለት ክሶች ላይ ድምጽ ሰጥቷል።
አንደኛው ክስ ፕሬዝዳንቱ ስልጣናቸውን ያላአግባብ ተጠቅመዋል የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የምክር ቤቱን ስራ አደናቅፈዋል የሚል ነው።
ሁለቱንም ክሶች ዲሞክራቶች ሲደግፉት ሪፐብሊካን ግን ተቃውመውታል።
ድምጽ አሰጣጡ እየተካሄደ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሚችጋን የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ ሲሆን፣ ለተሰበሰበው ደጋፊያቸው” ስራ እየፈጠርንና ስለሚቺጋን እየተሟገትን ባለበት ሰዓት የምክር ቤቱ አክራሪ ኃይሎች በቅናት፣ በጥላቻና በቁጣ ተሞልተው ምን እያደረጉ እንደሆነ እያያችሁ ነው” ብለዋል።
ከምክር ቤቱ ውሳኔ በኋላ ዋይት ሐውስ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው፣ ፕሬዝዳንቱ በሴኔቱ ችሎት ” ነጻ እንደሚወጡ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ናቸው” ብሏል።
የፕሬዝዳንት ትራምፕ መከሰስ ጉዳይ በምክር ቤቱ ለ10 ሰዓታት ያህል አከራክሯል።
• የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በዋጋ የሚያንራቸው ምርቶች
በኋላም ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የዩክሬን አቻቸውን የምርጫ ተቀናቃኛቸውን፤ ጆ ባይደን፤ ላይ ምርመራ እንዲጀምሩ ጫና አድርገዋል በሚል፣ ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም በሚል የቀረበባቸውን ክስና ሁለተኛው ፕሬዝዳንቱ ለሚደረግባቸው ምርመራ መረጃዎችን ለመስጠት ተባባሪ ባለመሆናቸው የምክር ቤቱን ስራ በማደናቀፍ በሚለው ክስ ላይ ድምጽ ሰጥተዋል።
በሁለቱም ክሶች ዲሞክራቶች አብላጫውን የድጋፍ ድምጽ በመስጠት አሳልፎታል።
ከዚህ በፊት በአሜሪካ ታሪክ ሴነት ፊት ቀርበው ክሳቸውን የተከላከሉ ፕሬዝዳንቶች አንድሪው ጆንሰንና ቢል ክሊንተን ሲሆኑ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሶስተኛው ይሆናሉ።