ባለፈው የአሸባሪው ጃዋር አሸባሪ ጭፍሮች ምዕራብ አሩሲ ዶዶላ የአሸባሪ ጥቃት የፈጸሙባቸውና ከጥቃቱ ተርፈው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተጠግተው የነበሩ ወገኖቻችን፦
* አገዛዙ ወደየቤታቸው እንዲመለሱ ስላልፈለገና እንደወጡ እንዲቀሩ ስለፈለገ እስከዛሬም ድረስ በቤተክርስቲያኑ እንደተጠጉ እንዳሉና በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን፣
* ከፊሎቻቸውም ተስፋ በመቁረጥ እግራቸው ወዳመራቸው ወደሌላ ሀገር እየተሰደዱ መሆናቸውን፣
* የሚሰደዱበት ቦታ የሌላቸው ወገኖች ደግሞ እዚያው ለረሀብና ለበሽታ ተዳርገው በአፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን፣
* ለአንድ አፍታ ከተጠጉበት ቤተክርስቲያን ወጥተው ጥቂት ፍራንክ ከኪሳቸው ያላቸው በፍራንካቸው፣ የሌላቸው ደግሞ በእጃቸው ያለውን ሰዓትም ሞባይልም ምኑንም ሸጠው አንዳንድ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለመግዛት ሲሞክሩ የአገዛዙ አካላት ኅብረተሰቡን “ምንም ነገር ቢሆን ለእነሱ አትሽጡ፣ ከእነሱ አትግዙ!” በማለትና ኅብረተሰቡን በአማርኛ ለሚናገር ሰው መልስ እንዳይሰጥ በማድረግ አድማ እንዲመታባቸው በማድረጉ መገበያየት እንዳይችሉ በመደረጋቸው እጅግ ችግር ላይ መውደቃቸውን፣
* ከተለያየ አካባቢ የተላከላቸው እርዳታም ዶዶላ ከገባ በኋላ ለእነሱ ሳይሰጣቸው ተመልሶ ወደሌላ ቦታ የሚወሰድ መሆኑን ወዘተረፈ. ከብዙኃን መገናኛዎች ሰማን!!!
ወገን ሆይ! ለመሆኑ እስከዛሬም ድረስ ከተለያየ አካባቢ በተለያየ ጊዜ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ አማሮች እንደተፈናቀሉ ይቀራሉ እንጅ ወደየቤታቸውና ወደየቦታቸው እንዲመለሱ እንዳልተደረገና እንደማይደረግ ታውቃለህ ወይ??? መዚህ እያሰለሱ በሚፈጽሙት የማፈናቀል መንገድስ አማራን ከብዙ ስፍራዎች እንዳጸዱትና ማፈናቀሉን አገዛዙ ሆን ብሎ አማራን ለማጽዳት አቅዶ የሚያደርገው መሆኑን ታውቃለህ ወይ??? በዚህ የአገዛዙ እርምጃስ ብአዴን ዋነኛ ተባባሪ መሆኑንስ ታውቃለህ ወይ???
ይሄ ሁሉ ግፍ የተፈጸመው ደጋፊ፣ ተቆርቋሪ፣ አቋጣሪ፣ አሳቢ፣ የኔባይ አካል በሌለውና ለራሱም በማያውቀው፣ ለራሱ በማይቆመው በአማራ ላይ ሆነና በሀገሪቱ በ21ኛው መቶ ክ/ዘ ፈጽሞ የማይጠበቅ ይሄ ሁሉ አረመኔያዊ ግፍ እየተፈጸመ ምንም እንዳልተፈጠረና ሀገር ሰላም እንደሆነ ሁሉ ነገሮች እንደወትሮው ሁሉ ባሉበት ቀጥለዋል!!!
ይሄንጊዜ ይሄ ሁሉ ግፍ አይደለም የዚህ ሁሉ ግፍ ኢምንቷ እንኳ በኦሮሞ ወይም በትግሬ ላይ ተፈጽሞ ቢሆን ምን ይፈጠር እንደነበር እያንዳንድሽ አሳምረሽ ታውቂያታለሽ!!! ባለሥልጣኖቻቸው በቁጣ ወጥተው መግለጫ ይሰጣሉ፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶቻቸውም በተመሳሳይ ግስላ ሆነው መግለጫ ይሰጣሉ፣ አክቲቪስቶቻቸው ዘራፍ ይላሉ፣ ሕዝባቸውም “ተፈጸመብን!” ከሚሉት ስንት ጊዜ እጥፍ የሚሆን የአጸፋ ጥቃት ፈጽመው ሲበቃቸው ያቆማሉ!!! ኧረ እንዲያው ነገሩን አልኩ እንጅ እነሱንማ ማን ነክቷቸው???
እጅግ በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ ይሄ ሁሉ ግፍ በየዕለቱ በአማራ ላይ እየተፈጸመ እየታየ ብአዴንንና አብንን እየጠቀሰ አማራ የሚታገልለት ድርጅት ያለው የሚያስመስሉ ዘገምተኞች መኖራቸው ነው!!!
ብአዴንና አብን ለአማራ ሕዝብ የቆሙ ድርጅቶች የቆሙና የሚታገሉ ከሆኑ ለእነዚህ ዶዶላ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖቻችን ብቻ ሳይሆን በየስፍራው ከተማሪ እስከ ገበሬ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖቻችን የታል የደረሱት??? ምን ሲያደርጉስ ታዩ??? እንደሌሎቹ በቁጣ ወጥተው “ሁኔታው በአስቸኳይ ወደነበረበት ካልተመለሰ….!” በማለት መግለጫ በመስጠት የአማራን መብትና ጥቅም አስጠበቁ??? እንዲያው ለአንድ ቀን እንኳ ይሄንን ሲያደርጉ ታይተው ያውቃሉ??? ለመሆኑ አማራ የማይገደልበት የትኛው የሀገሪቱ ክፍል ነው??? በዚህች ሀገር አማራ ሳይገደልና ሳይፈናቀል ሰላም ውሎ ሰላም አድሮ የሚያውቅበት ቀን ኖሮ ያውቃል እንዴ??? ብአዴንና አብን ከምን ታደጉህ??? የታለ ችግርህ እንዲፈታ ያደረጉት??? ትዝም ብለሀቸው አታውቅ!!! ለዚያም ነው ለችግርህ ፈጥነው የሚይደርሱትና ፈጣን ምላሽ የማይሰጡት!!! የተመሠረቱትም ጠላቶችህን ለማገልገል እንጅ አንተን ለማገልገል አይደለም!!!
ከዚህ ያላዳኑት ከምን ሊያድኑት ነው “ድርጅቴ!” እያልክ የምታላዝንላቸው እነ ምድረ ዘገምተኞ??? ዛሬ ያልደረሱ መቸ ሊደርሱ ነው እነሱን ተስፋ የምታደርገው ምድረ ዘገምተኛ??? ብአዴን የዚህ ፀረ አማራ ጥቃት ተባባሪ ስለሆነና የአማራን ጉዳይ ጉያየ ስለማይለው እንጅ ጠንካራ አቋም ይዞ “እኅት ድርጅቴ!” የሚለውን ኦሕዴድን ይሄንን እንዲያስተካክል ማድረግ አቅቶት ይመስልሃል??? የብአዴን የበኩር ልጅ አብንም እንደዚያው!!!
የአፍሪካ ኅብረት ሳይቀር አገዛዙ ለእነኝህ ተፈናቃዮች አስፈላጊውን ሰብአዊ እርዳታ እንዲያቀርብ፣ ለወደመባቸው ንብረት አስፈላጊው ካሳ እንዲከፈላቸው፣ መጠለያዎቻቸውን በአስቸኳይ አዘጋጅቶ ወደየቤታቸው እንዲመለሱ እንዲያደርግ፣ ጥቃት የፈጸሙ አካላትን በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ እነኝህን እርምጃዎች ለመከወን የአቅም ውስንነት ካለበትም ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪ እንዲያቀርብ በመግለጫው አሳስቦ ነበር!!!
ነገር ግን “ባለቤቱ ያናቀውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም!” ሆነና ነገሩ እራሱ የጥቃቱ ሰለባ የአማራ ሕዝብ ጉዳየ ብሎ ስላልያዝነውና ስላልጮህንበት አገዛዙ ይሄው በዚህ መልኩ እንኳንና ምላሽ ሊሰጥ በግፍ ላይ ግፍ እየጨመረ በወገኖቻችን ላይ በነፍስ በሥጋቸው እየተጫወተ ይገኛል!!!
በተፈናቀሉበት ሰሞን ዶዶላ ድረስ ሔደው የጎበኟቸው ጳጳሳትስ ምን መፍትሔ አመጡ??? እንዲያው ዝምብሎ ለማተሽተሽና ለታይታ ኖሯል እንዴ እዚያ ድረስ የሔዱት??? ቤተክርስቲያኗ እራሷስ ምን ፈየደችላቸው??? ጳጳሳቱ ወይም ቤተክርስቲያን እንዴት “እነዚያ ተፈናቃይ ምእመናን እንዴት ሆኑ? ምን መፍትሔ ተሰጣቸው?” ብለው መለስ ብለው አይጠይቋቸውም??? እንዴት አይከተሉም??? ቤተክርስቲያኗን አሥተዳድራለሁ የሚለው አካል አገዛዙ ለዚህ ችግር መፍትሔ አልሰጥ ካለ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪ በማቅረብ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እርዳታና ትብብር እንዲያገኙ ማድረግ እየቻለ ይሄንን ማድረግ ያልፈለገውና ወገኖቻችንን ስቃይ ላይ የተዋቸው ለምን ይመስላቹሃል???
ለሕዝብ መብትና ጥቅም ቆመናል የሚሉት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና የፖለቲካ ድርጅቶች ለዚህ ችግር ድምፃቸውን ጮክ ብለው ያላሰሙ ለምን ሊያሰሙ ነው??? እንዴትና ለምን ጭጭ ይላሉ???
እኔ ግን እላለሁ ወገኔ አማራ ሆይ! ወያኔ/ኢሕአዴግ በሥልጣን ላይ እስካለ ጊዜ ድረስ ላንተ የሚሆን የምትጠብቀውና ተስፋ የምታደርገው የሚመጣልህ መልካም ቀን ፈጽሞ የለምና ቀስ በቀስ በተለያየ ጥቃት አመናምኖ ሳይጨርስህ በፊት የሚያዋጣህ ግልብጥ ብለህ ወጥተህ በማመፅ ከጠላትህ ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናነቅና የፈጀኸውን ፈጅተህ የተረፈው ወገንህ ተርፎ ቀን ይውጣለት!!! ሌላ ምንም አማራጭ የለህም!!! ፈጽሞ ተስፋ የማይጣልባቸውን ፀረ አማራ ጠላቶችህን ብአዴንንና አብንን ተስፋ አድረገህ መቀመጥህና ጊዜ መስጠትህ ለጠላቶችህ እንጅ ለአንተ አልጠቀመምና ፈጽሞም አይጠቅምምና ተነሥ!!!
ድል ለአማራ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com