
ቻይና ትግራይና የፌዴራሉ ሕገ መንግስት ?
የቻይናው አምባሳደር ተጠርተው ማብራሪያ ሊጠየቁ ይገባል !
የኢፌዲሪ ሕገ–መንግሥት የፌድራል መንግሥትን ሥልጣንና ተግባር በወሰነበት አንቀጽ 51 (4) የውጭ ግንኙነትን ስትራቴጂና ፖሊሲ ማውጣትና ማስፈጸም የፌድራል መንግሥቱ ሥልጣን መሆኑን በግልጽ ይደነግጋል።
የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅናና ፈቃድ ውጪ ለፌዴራሉ መንግስት የውጪ ጉዳይና ኢንቨስትመት ቢሮ ሳታሳውቅ ባለስልጣናቷን ወደ ትግራይ ክልል ለመላክ አይሮፕላን ማሳፈሯ የሃገር ሉዓላዊነትን ከመድፈር ተለይቶ አይታይም።
የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርፖርት የመለሳቸው የቻይና ባለስልጣናት የመንግስትን አሰራር በመጣስ ወደ መቀሌ ሊያቀኑ የነበሩ መሆኑ በውስጥ ጉዳያችን ንትርክ ተከትሎ ያሳዩን ንቀት ነው።
ወደ ሆንግኮንግም ሆነ ታይዋን ለመሔድ የሚፈልጉ የሃገራት ባለስልጣናት የቻይናን ፈቃድ እንደሚጠይቁ ሁሉ ቻይናም ወደ ማንኛውም የኢትዮጵያ ክልሎች ለመሔድ የፌዴራሉን መንግስት ፈቃድ መጠየቅ ነበረባት፤ በባለስልጣናቱ ላይ የተወሰደው እርምጃ ተገቢ ቢሆንም አምባሳደሯ ግን ማብራሪያ ሊሰጡ ግድ ይላል።
ጉዳዩ እንዲህ ነው – 9 አባላት የያዘ ከአንዲት የቻይና ግዛት የተላከ ልኡክ ትላንት ማታ በ 1 ሰዓቱ የአየር በረራ ለስራ ጉዳይ ወደ መቐለ ለመብረር ፍተሻ ጨርሰው ለመብረር ሲዘጋጁ ድንገት ‘ከውጭ ጉዳይ ነው የታዘዝነው’ ባሉ የአየር መንገዱ ሰዎች ትእዛዝ መሰረት ቦሌ ኤርፖርት ላይ ወደ መቐለ እንዳይጓዙ መከልከላቸውና አ.አ እንዳደሩ ታውቋል።
በመሀከላቸው ከቻይና ኤምባሲ ዲፕሎማት ከልኡኩ ጋር ቢኖርም የጉዞአቸው ምክንያት ለማብራራት ቢሞክሩም ”እኛም ታዘን ነው የምናውቀው ነገር የለም” የሚል መልስ ተሰጥቶዋቸዋል። ኤምባሲው ትላንት አመሻሽ በስልክ ደውሎ ለውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ሀላፊዎች ቅሬታውን ገልጿል ተብሏል።
ቀደም ሲል የኤዥያ አምባሳደሮች በአንድ ላይ የትግራይ ክልል መንግስትንና የክልሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመጎብኘት በሄዱበት ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱኳን አያኖ ወደ ልኡካኑ ቡድን መሪ (ዲን) የሆኑት የባንግላዴሽ አምባሳደር የቪየና ኮንቬንሽን በመጣስ ስልክ በመደወል በአስቸኳይ ወደ አ.አ እንዲመለሱ ትእዛዝ መስጠታቸው አነጋጋሪ ሆኖ ነበር። #MinilikSalsawi