22 ዲሴምበር 2019

የቦርድ ሰብሳቢ መልአከ ሠላም ኤፍሬም ሙሉዓለም

ከትናት በስቲያ በአማራ ክልል፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ የሚገኘው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ ጀሚዑል ኸይራት ታላቁ መስጊድ እና አየር ማረፊያ መስጊድ ላይ ቃጠሎ መድረሱ አሳዛኝ መሆኑን የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታውቋል።

ጉባኤው በድርጊቱ ማዘኑን አስታውቆ ለወደፊትም እንዲህ አይነት ድርጊት እንዳይፈጸም ጥሪውን አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ሐይማኖት ጉባኤ አባላትና የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት ወደ ሞጣ በማቅናት ከነዋሪዎች ጋር እንደሚወያዩና የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

በሞጣ የተፈጠረው ምንድን ነው?

ይህ የተገለጸው የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሞጣ ከተማ በሐይማኖት ተቋማት ላይ በደረሰው ጉዳት ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

“የሠው ልጅ ሊደረግበት የማይገባውን ነገር ሌሎች ላይ ማድረጉ ተገቢ አይደለም” ያሉት የጉባኤው የቦርድ ሰብሳቢ መልአከ ሠላም ኤፍሬም ሙሉዓለም ናቸው።

የትግራይና የፌደራል መንግሥቱ ግንኙነት በጣም አሳሳቢ ነው- ዶ/ር አብረሃም ተከስተ

ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ

“ሰው የሚያደርሰው ይህን መሰሉ ጥፋት በሰማይም በምድርም የሚያስጠይቀው ነው” ያሉት ሰብሳቢው የሐይማኖት ተቋማት እንክብካቤ ሊደረግላቸው ሲገባ መቃጠላቸው ግራ የሚያጋባ ነው ብለዋል ።

“የአካባቢው ህብረተሰብ አብሮ የሚበላ እና የሚጠጣ እንጂ ለዘረፋ እና ለእሳት የሚዳረግ አይደለም፤ ክቡር የሆነውን ቤተ ዕምነት ማቃጠልም ተገቢ አይደለም” ብለዋል

መንግሥትም ቢሆን በየጊዜው በተለይ በአማራ ክልል የሚፈጠሩ ችግሮችን ቀድሞ ፈጥኖ የመከላከል ሥራ መሥራት እንዳለበት አስታውሰው እንዲህ አይነት ጥፋት ከተፈጸመ በኋላ ሰዎችን ለህግ አቅርቦ ፍጻሜ ላይ ማድረስ እንደሚገባ አስምረዋል።

ነገር ግን ህግ የጣሱ እርምት ማግኘት ሲገባቸው የተቀጡ ሰዎች ባለመኖራቸው ችግሩ እንደተስፋፋ ገልፀዋል።

“እንዲህ ከሆነ ነው ሰው ነፍሱንም እጁንም የሚሰበሰብው” ብለዋል።

ሁሉም ማህበረስብ ያገባኛል ብሎ መሥራት ያለበትን መሥራት እና ኃላፊነቱን መወጣት አለበትም ሲሉ ተናግረዋል።

“ሁሉም የነበረውን አብሮነት እና መቻቻል ማጠናከር፤ የተሳተፉትንም ለህግ እንዲቀርቡ በመተባበር እና የተዘረፈውንም ሃብትም መተካት አለብን” ብለዋል የቦርዱ ሰብሳቢ መልአከ ሠላም ኤፍሬም ሙሉዓለም።

በሞጣ ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ 15 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ ተስፋዬን ጠቅሶ የአማራ መገናኛ ብዙን ዘግቧ