December 21, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/185558

የሞጣ ሙስሊሞች ም/ቤት ቤተክርስቲያናትና መስጂዶች ላይ ጥቃት ከመድረሱ በፊት ለከተማው አስተዳደርና ጸጥታ መምሪያ በደብዳቤ አሳውቋል ተባለ !
የሞጣ ሙስሊሞች ግዴታቸውን ተወጥተዋል!
ከስር የሚገኘው ደብዳቤ የሞጣ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከአንድ ወር በፊት ለአማራ ክልል መንግስት የፃፈው ነው። እስልምና ምክር ቤቱ ከእሱ እውቅና ውጭ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የአካባቢውን ሙስሊሞች ለመከፋፈል ከዚህም ሲያልፍ የእምነት ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የሚሰባሰቡትም ማር ዘነብ ሆቴል መሆኑን ገልፆአል። እስልምና ምክር ቤቱ ከእውቅናው ውጭ የሆኑ አካላት ኮሚቴ መርጠው ከመስጊድ ውጭ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን፣ ልዩነት ቢኖር እንኳ መስጊዳቸው ውስጥ መነጋገር እየቻሉ ሌላ ቦታ የሚነጋገሩት ችግር ለመፍጠር ነው ሲል ጥቆማ ሰጥቶ ነበር። ጉዳዩ ወደ ሌላ ችግር ከመሄዱ በፊት የሚመለከተው አካል ክትትል ያድርግ ብለውም ነበር። የሞጣ ሙስሊሞች ግዴታቸውን ተወጥተዋል። ኃላፊነቱን ያልተወጣው የክልሉና የአካባቢው የመንግስት አካል ነው።
ሌላ አላማ ያላቸው አካላት ቤተ ክርስትያንም መስጊድም ቢቃጠል ጉዳያቸው አይደለም። ይህን የሚፈልጉት፣ ከአካባቢው እስልምና ጉዳዮች ውጭ ሌላ ኀይል ያሰማሩት እነ አህመዲን ጀበል ደግሞ ሰርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል። ከእነሱ አማራው ክርስትያን ለአማራው ሙስሊም ይቀርባል። ምክንያቱም የእነ አህመዲን ጀበል አለቃ የሆነው ጃዋር አማራ ሙስሊሞችን ከኦሮሚያ ሲያፈናቅል ምንም ብለው አያውቁም። ባለፈው ናዝሬት ላይ ቤተ ክርስትያን እንዳይቃጠል የጣረ ሙስሊም ሲገደል፣ መስጊድ ሲቃጠል ምንም አላሉም።
የሞጣ ሙስሊሞች ከወራት በፊት ግዴታቸውን ተወጥተዋል። አሁን ደግሞ ክርስትያኑ የወደሙትን በመስራትና ሰርጎ ገቦችን በማጋለጥ በማገዝ ግዴታውን መወጣት አለበት። እንዲህ ካልሆነ የሞጣ ሙስሊሞች ቀድመው እንዳሳወቁት ግጭት ለመፍጠር የመጡትን እኩዮች