2019-12-21
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በወቅታዊ ሁኔታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መግለጫ
. በመላው ዓለም የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን በደረሰው ወቅታዊ እና ያልታሰበ ጉዳት በሐዘን ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና ምዕመናት: የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት እና የመጅሊስ አባላት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ወገኖቻችን፦ • በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ወረዳ በቤተ እምነቶች ላይ የቃጠሎ ጉዳት መድረሱን ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ሰምተናል። በጉዳቱም የተሰማንን ልባዊ ሐዘን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እንገልጻለን። • የተፈጸመው ድርጊት የሀገራችን ሰላም እና እድገት የማይጠቅም ለዘመናት የቆየ አብሮነት የመኖር ዕሴቶቻችን የሚንድ መሆኑን መላው ሕዝባችን ተረድቶ በተረጋጋ እና በሰከነ መንፈስ ጉዳዩ እስከሚጣራ በትእግስት እንድትጠባበቁ እናሳስባለን። • ከዚሁም ጋር የሚመለከታችሁ የመንግሥት አካላት ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊው ክትትል እንድታደርጉ እናሳስባለን። • ይኽንኑ ድርጊት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሚመለከተው የመንግሥት የአስተዳደር :የሕግ እና የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን አጣርተን ይፋ የምናደርግ መሆኑን በአጽንዖት እንገልጻለን። • እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!! መ/ር ኃይሉ በላይ EOTC TV Filed in:Amharic