
የኦሮሞ ፖለቲከኞች ግባቸው ወሎን ሰሜን ኦሮሚያ ማድረግ፣ ሲዳማን ክልል በማድረግና ጌዲኦን አማራጭ በማሳጣት ወደ ኦሮሚያ ማጠቃለል፣ ደቡብ ክልልን በመበታተን በገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ማስገበር፣ አዲስ አበባን የኦሮሞ ማድረግ … ነው። ይሄ የኦዲፒም፣ የኦነግም፣ የጃዋር መሐመድም፣ የሌሎች ጥንፈኛ ኦሮሞውችም ህልም ነው።
በመሆኑም ለማ መገርሳናዐአብይ አሕመድ የግብ ልዩነት የላቸውም። ኦነግና ዐብይ አሕመድ፣ ጃዋርና ዐብይም እንዲሁ። የሚጋጩትም፣ የሚጣሉትም በታክቲክ ልዩነት ነው። እነ ዐብይ አሕመድ ኢትዮጵያዊንን በማታለልና ሥልት በመጠቀም የኦሮሞን የበላይነት ማንገስ ይፈልጋሉ። እነ ጃዋር መሐመድና ሌሎች ጥንፈኞ ኦሮሞዎች ደግሞ ዛሬውኑ በጉልበት የኦሮሞን የበላይነት ማምጣት ይሻሉ።
ልዩነታቸውም ይሄው ብቻ ነው።