December 25, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/188547

Image may contain: text


ምርጫ ቦርድ ብልጽግና ፓርቲ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጠው ወሰነ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፓርቲዎች ምዝገባ ጥያቄዎች ዙሪያ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ጥያቄ እና፣ የፓርቲ መለያ ሰንደቅ አላማ የማጸደቅ ጥያቄን ያቀረቡ ፓርቲዎችን ጉዳይ አይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚህም መሰረት
1.የኢህአዴግ አባል የነበሩ ሶስት ፓርቲዎች እና ሌሎች አምስት ፓርቲዎች በጋራ ራሳቸውን በማክሰም ብልጽግና ፓርቲን መመስረታቸውን በማሳወቅ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጣቸው ህዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም በጽሁፍ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረቡ ሲሆን ቦርዱም ጥያቄያቸውን በፓለቲካ ፓርቲዎችና ምርጫ አዋጅ 1162/2011 መሰረት መርምሮ ውሳኔውን ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ቦርዱ የእውቅና ጥያቄ ከቀረበለት በኋላ በተጨማሪ መሟላት ያለባቸውን ሰነዶች በታህሳስ 01 ቀን 2012 ዓ.ም በመጠየቅ በጥያቄውም መሰረት ታህሳስ 06 ቀን 2012 ዓ.ም የጥያቄዎቹ ምላሾችና ማብራሪያዎች ተሟልተው መቅረባቸውን በማረጋገጡ ብልጽግና ፓርቲን ለመመስረት
1. የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ( ኦዴፓ)፣
2.የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን)፣
3.የሃረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ)፣
4.አማራ ዴሞክራያዊ ፓርቲ ( አዴፓ) ፣
5. የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ)፣
6. የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ፣
7.የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ (ጋህአዴን)
8.የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ( ቤጉህዴፓ)
በተናጠል በጠቅላላ ጉባኤያቸው ውሳኔ መሰረት አድርገው ውህደቱን ለመቀላቀልና ፓርቲያቸውን ለማክሰም የወሰኑት ውሳኔዎች እንዲሁም ውህደቱን ለመመስረት ያደረጉትን ስምምነት በሙሉ ህጉን ተከትሎ የተፈጸመ በመሆኑ ቦርዱ ፓርቲዎቹ ተሰርዘው ብልጽግና ፓርቲ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጠው ወስኗል፡፡
በዚህም መሰረት ውህዱ ፓርቲ