
ታህሳስ 14 ቀን 2012 ዓ.ም የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ከቦርዱ ውስጥ በወጡ ከፍተኛ የቦርዱ አባላት እና የግንቦት ሰባት የፓርቲ አባላት ትብብር የፓርቲያችንን ህልውና ለማጥፋት ዘመቻ እየተደረገብን ነው በሚል ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር እንዲሁም በቀጥታ ከኢዜማ ጋር የገባበት ሰጣ ገባ በመፍታት ከምርጫ ቦርድ በግፍ የተማነውን ፍትህ በእልህ አስጨራሽ ትግላችን መልሰን አግኝነተናል በሚል እና በቀጣይ የያዛቸውን አቋሞች አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫውን ሰጥቷል።
በመግጫውም በርካታ ፖለቲካዊ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን ፓርቲ ኢዴፓ አሁን ላይ እንደ ሐገር የተጋረጡብን ችግሮች በርካታ መሆናቸውን አምኖ በዋነት ግን እንደ ሐገር የሚያስቀጥለንን ህልውና ላይ ያለምንም እረፍት ልንሰራ ይገባል ሲል የዚህም ጅማሮ ደግሞ ላለፉ 18 ወራት አሻግራችኋለው ብሎ አሁንም ሐገሪቷን እያስተዳደረ የሚገኘው ኢህአዴግ ያለፈው ስህተት ላይ እየሰመጠ በመምጣቱ ምክኒያት ቀጣዩን ምርጫ ነቻ እና ፍትሃዊ እንደማይሆን ኢዴፓ አረግጫለው ብሏል።
ታዲያ ይህን ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ሲሰራ ዳር ይዞ እንደማያይ እና ለዚህም ባለው አቅም ሁሉ ምርጫው የሚራዘምበትን ምክኒያት በግልጽ በማሳየት በንግግር መፍታት ያ ካልሆነ ደግሞ በምርጫው ላይ አቅም ያለው ፓርቲን ይዞ እንደሚቀርብ ገልጸው ለዛም በቅርቡ ከሰባት ካለነሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ጥምረትን እንደሚፈጥር የኢዴፓ የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው ገልጸዋል።
ከጋዜጠኞች ከተነሱት ጥያቄዎች ውስጥ አሁን ላይ በስልጣን ላይ ያለው የለውጥ መንግስት የውጭ ግንኙነቱን በተመለከተ ፓሪው ያለው ምልከታን ያቀረቡት አቶ ልደቱ አያሌው እንዳሉት ከሆነ የተሰጠውን ዕድል አልተጠቀመበትም የሚሉት የለውጡ መንግስት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ላይ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የሚጎርፉት የስጦታ እና የብድር ድጋፎች ያለምንም ቅድመ ስምምነት ሊደረጉ ስለማይችሉ በግልጽ መታወቅ ያለባቸውን ስምምነቶች ህዝቡ ማወቅ አለበት ነጻ ምሳ ብሎ ነገር በውጭ ግንኙነት ላይ የለም ሲሉ እየተሄደ ያለበትን መንገድ ላይ ያላቸውን ስጋት አንስተዋል።