በእውነት ነው የምላቹህ እንደ ብርሃኑ አድማሴ ያለ በእግዚአብሔር ስም የሚነግድ ኤቲይስት ወይም ኢአማኒ ዓይቸ አላውቅም፡፡ ከዳንኤል ክብረትምይብስብኛል!!!

ትናንትና ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የዝግጅቱ ምን እንደሆነ አላወኩም በማኅበረ ቅዱሳንን ቴሌቪዥን ይሄው ጉደኛ ካድሬ ብርሃኑ አድማሴና መምህር ግርማ ከታዳሚው ጥያቄ ቀርቦላቸው መሰለኝ ለተጠየቁት ጥያቄ መልስ ሲሰጡ የሚያሳይ ዝግጅት ሲተላለፍ ወደ መጨረሻው አካባቢ ደርሸ ተመልክቸ ነበር፡፡

በዚህ ዝግጅት ላይ ይሄው በእግዚአብሔር ስም የሚነግድና ለሆዱ ያደረ የአገዛዙ ካድሬ የአገዛዙን ጥቅም ለመጠበቅ ምዕመናን በዜግነታቸው ሀገራቸውን፣ በክርስቲያነታቸው ደግሞ ቤተክርስቲያንን ከአላውያን ገዥዎች፣ ከመናፍቃን ጳጳሳትና ከከሀድያን እንዳይጠብቁ ወይም የመጠበቅ ግዴታቸውን እንዳይወጡ አድርጎ ለማፍዘዝ ለማደንዘዝ ታሪክንና የእግዚአብሔርን ቃል እያጣመመ፣ እያሳከረና ጥያቄውን የጠየቁትን ሰዎች ለማሸማቀቅ እየሞከረና እየወቀሰ ያልቀባጠረው ነገር የለም ነው የምላቹህ!!!

በጣም ተናድጀ ይሄንን ጽሑፍ ለመጻፍ ፈለኩና ሙሉ ዝግጅቱን ከዩቲዩብ አካውንታቸው ገብቸ ለመመልከት ፈልጌ ወዲያውኑ የቴሌቪዥናቸውን የዩቲዩብ አካውንት ገብቸ ብበረብር ብበረብር ይሄንን ዝግጅት ፈጽሞ ላገኘው አልቻልኩም፡፡ እንዲሁ ከሚቀር ብየ ይሄ ሆዱን አምላኪ ቆሻሻ ቅጥረኛ ከተናገረው አንድ ሁለቱን ነገር አንሥቸ ብቻ ልናገር፡፡

ይመስለኛል የተጠየቀው ጥያቄ ከወቅታዊ ችግር አኳያ ቤተክርስቲያን ጥቅሟንና መብቷን ለማስከበር በሚጠበቀው ደረጃ ምላሽ አለመስጠቷና አለመንቀሳቀሷን የሚነቅፍ ጥያቄ መሰለኝ የተጠየቀው፡፡ እሱም ሲመልስ ቤተክርስቲያን ጉዳዩን የያዘችበት መንገድ ትክክል መሆኑን ቤተክርስቲያን እንደ የፖለቲካ ፓርቲ በየጉዳዩ እየተነሣች አቲካራ ውስጥ መግባት እንደሌለባትና ዝም ማለትን ወይም calm መሆንን መምረጧ ትክክል መሆኑን፡፡ ጭምታ፣ ዝምታ፣ calmness የቤተክርስቲያኗ ባሕልና ክርስትናም ይሄ መሆኑን፡፡ ቤተክርስቲያን ተልእኮዋ ሰማያዊ በመሆኑ እንደ ምድራውያን ጦር ሰብቄ ሠራዊት አዝምቸ!” በሚባል ነገር ላይ ፈጽሞ መገኘት የሌለባት መሆኑን ትንሽም እንኳ ሳያፍር ተናገረ!!!

እኔ የምለው ይሄ ካድሬ ገድላትንና ስንክሳርን ተመልክቶ አያውቅም ልበል??? ነው ወይስ በገድላትና በስንክሳር አያምንም??? አሃ! ለካ እሱ በእግዚአብሔር ስም እያጭበረበረ ሆዱን የሚሞላ ኢአማኒ ካድሬ ነው፡፡ ስለዚህም ገድላትና ስንክሳርን ቢያነብም እና የቤተክርስቲያኗ ባሕልና ክርስትና እሱ ከገለጸው በፍጹም የተለየ ቢሆንም እያጣመመ ለቅጥረኝነቱ እንዲመች አድርጎ እያወራ እየቀባጠረ ሆዱን ይሞላል፣ ጥቅሙን ያሳድዳል እንጅ እውነቱን አይገልጥም ማለት ነው!!!

አፈሩን ይብላውና ኢአማኒ ቢሆንስ ታዲያ ከቶ ለየትኛው ዕድሜ፣ ለየትኛውስ ዘመን ብሎ ነው የዚህን ያህል ዘግጦና ረክሶ ግፈኛውንና ፀረ ቤተክርስቲያኑን አገዛዝ ለማገልገልና ጥቅሙን ለማስከበር የዚህን ያህል የሚማስነው በሞቴ??? አቤ….ት መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከእንዲህ ዓይነት ክስረት ይሰውረን! ይጠብቀን! ይታደገን! ወገኖቸ!!!

ወገኖቸ እውነቱ ይሄ ቆሻሻ ቅጥረኛ እንዳለው ሳይሆን በተቃራኒው ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ዕድሜ ዘመኗን ያሳለፈችው በህልውናዋና በጥቅሟ ላይ ፈተና ካመጡባት ከአላውያን ነገሥታት፣ ከመናፍቃን ጳጳሳትና ከከሀድያን ጋር ስትጋደል፣ ድሃ ከሚበድሉና ፍርድ ከሚያጓድሉ ግፈኞች ጋር ስትፋለም፣ በፍልሚያውም ልጆቿ ሐዋርያት፣ ሊቃውንት፣ ቅዱሳን፣ ሰማዕታት እንደ ጎመን እየተቀረደዱ፣ እንደ ሽንኩርት እየተላጡ፣ እንደ እህል እየተፈጩ፣ እንደ ጥዋፍ እየነደዱ በሰማዕትነት ሲያልፉና ከአምላካችን የሰማዕትነትን ክብር ሲቀዳጁ፣ ምእመናንም ይሄንን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ስትሰብክ ስታስተምር ነው ዕድሜ ልኳን የኖረችው!!!

ከወንጌል እስከ የሐዋርያት ሥራና መልእክታት፣ ከገድላትን እስከ ስንክሳር ስትመለከቱ መጻሕፍቱ የሚያረጋግጡላቹህ እውነት ይሄንን ነው እንጅ ቅጥረኛው ብርሃኑ እንደተናገረው ቤተክርስቲያን እየተፈተነች፣ ጥቅሟና ህልውናዋ አደጋ ላይ እየወደቀ፣ ድሃ እየተበደለ ፍርድ እየተጓደለ እየተመለከተች ፈጽሞ ዝም ማለቷን፣ መጨመቷንና calm መሆኗን አይደለም!!!

እጅግ የሚገርማቹህ ደግሞ ይሄ ቆሻሻ ቅጥረኛ እንዲህ ብሎ አላበቃም፡፡ ከግብር አባቱ ከሰይጣን እንደተማረው ጥቅስ እየጠቀሰ ለማሳሳት ሲሞክር አገዛዙ ክፉ ቢሆንም ከእሱ መራቅ እንደማይገባና ከእሱ ጋር ተባብሮ መሥራት፣ እሱን ማገልገል የሚገባ መሆኑን ለማሳመን ብሎ የአብድዩንና የንጉሡን አክዓብን ግንኙነት፣ የዮሴፍንና የዳንኤልን ሕይዎት ሁሉ ያለ ዐውዱና ያለ ቦታው ምሳሌ አድርጎ በመጥቀስ ምእመናንን ለማሳሳት እስከመጣር ነው የደረሰው፡፡ ይሄ ቅጥረኛ ይህችኑ ነገር በሚሌኒየሙ ዝግጅት ላይም መናገሩን ሰምቻለሁ፡፡ አይገርማም??? እጅግ አያሳዝንም???

ሰው ለሆዱ ብሎ የቱንም ያህል ቢቀስጥ ወይም ለማጭበርበር ቢፈልግ የዚህን ያህል ርቀት ተጉዞ ይቀስጣል፣ ያጭበረብራል፣ ቃለ እግዚአብሔርንም ለቆሻሻ ጥቅሙና ዓላማው ሲል እያጣመመ መጠቀሚያ በማድረግ እራሱን ያረክሳል ብላቹህ ትጠብቃላቹህ ወገኖቸ??? እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!!! ከምኑ ዘመን ደረስን በእግዚአብሔር???

እግዚአብሔር አብድዩን በአክዓብ ቤት፣ ዮሴፍን በፈርኦን ቤት፣ ዳንኤልን በናቡከደነፆር ቤት ያስገባበት ወይም ያስቀመጠበት በቅዱስ ቃሉ እንደተገለጠው የራሱ ዓላማ ስላለው እንጅ ይሄ ጭንጋፍ ቅጥረኛ እንደሚለው የእነዚያን አላውያን መንግሥታት እንዲያገለግሉ እንዳልሆነ መገንዘብ የሚሳነው ክርስቲያን የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም እነዚያን ነገሥታት ማገልገል ለጥፋት ሥራቸው ተባባሪ መሆንና ዕዳ በደላቸውን መሸከም ነውና!!!

አንድ በስም ብቻ ሳይሆን በግብርም ክርስቲያን ነኝ!” ወይም የግብርም ክርስቲያን መሆን እፈልጋለሁ!” የሚል ሰው እንዴት ነው ፀረ ቤተክርስቲያን ለሆነ አገዛዝ ተቀጥሮ አገዛዙ ያዘዘውን እየሠራና የአገዛዙ የጥፋት ሥራ ተባባሪ ሆኖ እያለ እኔ የስም ብቻ ሳይሆን የግብርም ክርስቲያን ነኝ!” ሊል የሚችለው በሞቴ???

እኛስ የምናውቀው ተጠንቀቁ፤ ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ ብሎ አዘዛቸው!” ማርቆስ 8:15 የሚለውን የጌታን ቃል ነው!!! ሐዋርያትም ከውሾች ተጠበቁ፥ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ፥ ከሐሰተኛም መገረዝ ተጠበቁ!” ፊልጲ 3:2 እያሉ ማስተማራቸውን ነው የምናውቀው!!!

በነገራችን ላይ ይሄንን የሚለው ብርሃኑ አድማሴ ብቻ አይደለም በሙሉ የማኅበሩ አባላትም እንጅ፡፡ ዋናዋናዎቹ ሳይቀሩ እንዲህ ከማለትም አልፈው ለአገዛዙ ታማኝ ሆነው ለማገልገል ቃለ መሐላ እየፈጸሙ ከቤተመንግሥት አሳላፊነት እስከ አንባሳደርነት ተሹመው በርካታ የማኅበሩ አገልጋዮች በየመንግሥት መሥሪያቤቱ ተሹመው ይሄንን የቤተክርስቲያን ጠላት አገዛዝ በማገልገል ላይ እንደሚገኙ የምታውቁት ጉዳይ ነው፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን መጨረሻ ይሄ መሆኑ ነው እጅግ አሳዛኙ ነገር!!!

እንግዲህ ለሆዳችን፣ ለጥቅማችን ተገዝተን ነው የአገዛዙ አገልጋይ የሆንነው!” ላለማለት ነው ይሄ ሁሉ መቀባጠር፡፡ ነገር ግን ሰውን ማታለል ቢችሉ እግዚአብሔርን ማታለል የሚችሉ ይመስላቸዋል እንዴ??? ለነገሩ ሲያምኑበት አይደል!!!

እውነቴን ነው የምላቹህ ብዙዎቹ የማኅበሩ አንጋፋ አገልጋዮች በእውቀት የረቀቁ፣ የመጠቁ፣ የተመራመሩ መስሏቸው ባላዩት ባልጨበጡት እግዚአብሔር ማመን ጅልነት ሆኖ የሚታያቸው ሆነዋል፡፡ የሚያምነውንም ሰው እንደ መሐይም የሚቆጥሩ ሆነዋል!!!

ነገር ግን የሚታወቁት በአማኝነታቸውና በአገልጋይነታቸው ስለሆነና ከዚህ ብዙ ከቆዩበት ሕይዎት ወጥተው እንደ አዲስ እራሳቸውን ገልጠው በኢአማኒነት መታወቅ በማኅበራዊ ሕይዎት ችግር ስለሚፈጥርባቸው እንዲህ ከማድረግ ይልቅ ዕውቅናና ተአማኒነት ባተረፉበት የአገልጋይነት ማንነታቸው ጅልነት ሆኖ የታያቸውን ሃይማኖትን ጥቅም ማሳደጃ መሣሪያ ማድረግን መርጠው አማኝ መስለው እያሳመሩ በመተወን የተሰማሩት!!!

ለዚህም ነው ጥቂት እንኳ እግዚአብሔርን ሳይፈሩና ሳያፍሩ ቅዱሱን የእግዚአብሔርን ቃል ያለቦታውና ያለዐውዱ ፍጹም ነውረኛ በሆነ መንገድ እየጠቀሱ ጥቅማቸውን ለማስጠበቂያነት ሲጠቀሙበት የምትመለከቷቸው!!! አያሳዝንም???

ይሄ ቆሻሻ በዚህ አላበቃም ሕዝቡ በስውርም በምንም እየተደራጀ በመታገል ሀገሩንና ሃይማኖቱን ካንዣበበብን ጥፋት የመታደግ ስልትና ጥበብ የተሞላበት አኪያሔድ እንዳይጠቀም ለማከላከልና አንድን ተልእኮ ለመፈጸም ሲፈለግ ከባለጋራ ወይም ከጠላት ዕውቅና የተሰወረ የትግል ወይም የአሰላለፍ ስልትና ጥበብ መጠቀም ክርስቲያናዊ ተግባር እንዳልሆነ አድርጎ ምእመናንን ለማሳሳት ለማደንቆር ሲፈልግ ምን አለ መሰላቹህ፦

በአድዋ ጦርነት ወቅት አለ ቅጥረኛው፡፡ በአድዋ ጦርነት ወቅት አርበኞች ወራሪውን ጣልያንን እንዴት አድርገው ማጥቃት እንደሚኖርባቸው የውጊያ ስልት ሲቀይሱ ፊትአውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ቀበኝ በግራና በመሀል ጦር በማሰለፍ የመሀሉ ውጊያ እንዲገጥም አድርገን አቅቶት የሸሸ በማስመሰል ጣሊያን የሚሸሸውን የእኛን ጦር ተከትሎ ወደመሀል ሲገባ በግራና በቀኝ ያለው ጦር ከኋላው በመክበብ ጣሊያንን እንፍጀው!’ የሚል ምክር ሲያመጡ ዐፄ ምኒልክ ፊታውራሪ ገበየሁን ይሄንን ምክር እንዴት ታየዋለህ?’ ብለው ሲጠይቋቸው ፊታውራሪ ገበየሁ አይ እንዲህማ አይሆንም ጣሊያን ጠላቴ ቢሆንም በጀርባው አልወጋውም በወንድነት በጀግንነት ፊትለፊት ነው መውጋት ያለብኝ!’ አሉ!” በማለት የፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ስልታዊ የማጥቃት ስልትን “unfair unjust የሆነ ማሽንክ የክፋት አስተሳሰብ!” እያለ በማውገዝ የፊታውራሪ ገበየሁን አስተሳሰብ ደግሞ ይሄ የchristian virtue ነው፡፡ ጀግና ፊትለፊት ነው ሊዋጋ የሚገባው!” በማለት ቤተክርስቲያን ይሄኛውን አስተሳሰብ እስከ የገጠር የልጆች የባድማ የትግል ጨዋታ ድረስ እንዲዘልቅና የሕዝቡ አስተሳሰብ እንዲሆን አድርጋ መሥራቷን ተናገረ፡፡ አይገርምም??? አያሳዝንም???

ለመሆኑ ግን ፊታውራሪ ገበየሁ የአድዋው ጦርነት ላይ ነበሩ እንዴ??? “ለጌታየ ለምኒልክ የጦር ድግስ አላቆየውም!” ብለው አይደለም እንዴ በአንባላጌው ጦርነት በጀግንነት ሲዋጉ የተሠውት???

ይሄ ቅጥረኛ በዚህ አስተሳሰብ አነጋገሩ ክርስቶስን እየነቀፈ፣ እየተቃወመ፣ እየተቃረነ፣ እየተጻረረ መሆኑን ያውቅ ይሆን??? ቤተክርስቲያን ክርስቶስ ወይም እግዚአብሔር ለምን የሰው ሥጋን ተዋሕዶ ከሰው መወለድ እንዳስፈለገው አመሥጥራ ስታስተምር ሰይጣን በሥጋ ከይሲ ተሰውሮ አባታችን አዳምንና እናታችን ሔዋንን እንዳሳተ ሁሉ ጥበብን በጥበብ ለመመለስ ክርስቶስም ደካማ በሆነው የሰው ልጅ ሥጋ ተሰውሮ ሰይጣንን ድል ነሳው!” ብላ የምታስተምረውን ትምህርት እኮነው እየተጻረረ፣ እያወገዘ፣ እየነቀፈ ያለው ይሄ ቆሻሻ፣ ደንቆሮ፣ ቅጥረኛ???

በተጨማሪም ክርስቶስ በመስቀል ላይ እያለ አምላክ ሆኖ ሳለ አቅም እንዳነሰውና እንደደካማ ሰው አምላኬ አምላኬ ስለምን ተውከኝ፣ ተጠማሁ…!” እያለ 13ቱን አጽራራተ መስቀል መናገሩ ክርስቶስ ደካማና ሰው መስሎ በመቅረብ ወይም ለአቅርቦተ ሰይጣን ማለትም ሰይጣንን አታሎ በማቅረብ ሰይጣን እንደለመደው ሰው ነፍሱ ከሥጋው ስትለይ ነፍሱን በሲዖል ሥጋውን በመቃብር ለመቆራኘት ፈልጎ ሲጠጋ በነፋስ አውታር ወጥሮ ይዞ ለ5500 ዘመን በሲኦል ያጋዛቸውን ነፍሳት ተረከበው!” የሚለውን የቅድስት ቤተክርስቲያንን አስተምህሮ እኮነው ይሄ ቆሻሻ ደንቆሮ እየተቃወመ፣ እያወገዘ፣ እየተፃረረ ያለው??? ቢያምንበት ኖሮ ይነቅፍ፣ ይቃወም፣ ያወግዝ ነበረ ወይ??? ስለዚህ አያምንበትም!!! ከላይ እንዳልኳቹህ የእግዚአብሔርን ቃል ለጥቅሙ የሚሸቃቅጥ ኢአማኒ መልቲ ቀሳጢ ነው ማለት ነው እሱ!!!

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጣዖት አምላኪ መስሎ ቤተ ጣዖት ገብቶ ጣዖት አምላክያንን መስበኩና ማሳመኑ ትክክል አይደለም ማለቱ ነው እንግዲህ፡፡ ክርስቶስ በወንጌል እንደ እባብ ብልህ እንደ ርግብ የዋህ ሁኑ!” ማቴ. 1016 ሲል ምን ማለቱ ነው የሚመስለው ለመሆኑ???

እጅግ በጣም የገረመኝ ሌላው ነገር ደግሞ እሱ የሚያወግዘውን ክርስቲያን ሆኖ ጦር አዝምቶ ጠላትን በመውጋት ጠላትን የመደምሰስንተጋድሎ የፈጸሙትን ሮማውያን ቅዱሳን ሰማዕታትን እነ ቅዱስ ፋሲለደስን፣ እነ ቅዱስ ቴዎድሮስን፣ እነ ቅዱስ ፊቅጦርን፣ እነ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወዘተረፈ መጥራቱ ነው!!!

ክርስቲያን እንዲህ ሊያደርግ አይገባም!” እያለ እነሱ ያደረጉትን በተለያየ መድረክ እያወገዘ፣ እየነቀፈ፣ እየኮነነ እየተናገረ ለማምታታት ደግሞ የእነኝህን ስለ ክርስትና ከአላውያን ነገሥታት ጋር ሲዋጉ በሰማዕትነት ያለፉ ቅዱሳን ሰማዕታት የተዋሕዶ አርበኞችን ስም ደግሞ ይጠራል፡፡ ተግባራቸውን ካወገዘ፣ ከተቃወመ፣ ክርስቲያኖች እንደ እነሱ እንዳያደርጉ ከከለከለ እንዴት ነው እንደገና ደግሞ ቅዱሳን!” እያለ ስማቸውን ሊጠራ የሚችለው??? እንዲህ ዓይነት እፍረተቢስ፣ ዓይን ያወጣ፣ ነውረኛ ማጭበርበርና ማምታታት ከዚህ ጋኔናም ቅጥረኛ በስተቀር እኔ በሌላ ሰው ላይ ማየቴን እርግጠኛ አይደለሁም!!!

አየ አንች ቤተክርስቲያን ሰው ይቀበርብሻል???” አሉ አበው!!! እጅግ ያሳዝናል!!! ከዚህ ይሰውረን ወገኖቸ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው