ታጠቅ ዙርጋ ፤ 11December 2019

ጠቅላይ ምኒስተር አብይ አህመድ የአገራችን በትረ አገዛዝ ቁንጮ ከሆኑበት ግዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ በምን ዓይነት መልክአ ምድራዊ የአስተዳደር መዋቅር እና ሕገመንግሥት ይተዳደር ? በሚል አበይት ሃሳብ ላይ በዋናነት የሁለት ጎራ ውይይትና ክርክር እየተደመጠ ነው።

የኢትዮብሄርተኞችና ዲሞክራቶች ክርክርና አመኔታ ዜጋ ተኮር (ዲሞክራሲያዊ) ህብረ ብሄር ብሄረሰባዊ ሕገ መንግሥት (democratically federated states –Nation or Democratic United States of Ethiopia) ይኑረን ሲሆን፤

የጠባብ ወይም የአክራሪ ወይም የጽንፈኛ ብሄርተኞች ክርክርና አመኔታ ወያኔ ለሃያ ሰባት ዓመታት በገዛበተን የብሄር ቋንቋ ተኮር እና በአፓርታይድ ፌደሬሸን እንድተዳደር የሚል ነው ።

ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ለመብት ታጋዮች፣ፀሃፊዮች ወዘተርፈ ከላይ ካስቀመጥኳቸ መርህ፣አስተያየት፣አሳብ፣እይታ ወዘተርፈ ጋር በተያያዘ ፦ ዜና ሲያቀርቡ፣ ሲያውያዩ፣ ሲገልጹ፣ ሲያስረዱ፣ሲጽፉ ወዘተ..በደፈናው እገሌ ፌደራሊስት ነው፣ እነእገሌ ፌደራሊስቶችን ተቀላቀሉ፣ እገሌ የፌደራሊስቶች ፖለቲካ ያቀነቅናል ወዘተ..ሲሉ ይደመጣሉ ።

የትኛው ፌደራሊስት እንደሆነ ተለይቶ ይነገር/ይገለጽ ባይነኝ። ዲምክራቲክ ወይስ የብሄር ቋንቋ መአከል ያደረገ ፌደራሊስት? በተለይም ፖለቲካዊ ቋንቋዎችና ጽንሰ አሳቦችን ለይቶ ማወቅ ለሚቸግራቸውና የአገራችንን ፖለቲ አዘውትሮ ለማይክታተሉ በጣም አሳሳች ነው ። ስለሆነ ይታረም ባይነኝ ። በአገላለጹ ግራ የተጋቡ ኢትዮጵያውያን ስለነገሩኝ ነው ይህንን ማሳሰቤ የጻፍኩት።